Popular Posts

Saturday, January 2, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #ሶስት የሰው ሁለንተናው

 

አቢይ የጥሞና ቃል #ሶስት የሰው ሁለንተናው

የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14

እግዚአብሄር የደስታችን ተቃዋሚ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ስናጠፋ እየተከታተለ በትንሽ በትልቁ የሚኮረኩመን አምላክ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ባሪያ አሳዳሪ አይደለም፡፡ 

እግዚአብሄር እርሱን በመፍራት እስከተመላስን ድረስ በራሳችን መንገድ ደስ ሲለን ደስ ይለዋል፡፡ በመጨረሻ ወደፍርድ እንደሚያመጣን እያወቅን እስከኖርን ድረስ እግዚአብሄር በእኛ የእለት ለእለት ደስታ ውስጥ ጣልቃ አይገባም፡፡ እግዚአብሄር ጥቃቅንዋንም ነገር "አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ " በማለት አያስጨንቀንም፡፡

እግዚአብሄርን ማስደሰት ውስብስብ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን ለማስደሰት የስነመለኮት ዲግሪ አያስፈልገንም፡፡

የሰው ዋናው ሃላፊነት እግዚአብሄር ወደፍርድ እንደሚያመጣው በማሰብ የሚያደርገውን ነገር ሁሉ እግዚአብሄርን በመፍራት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ የእውቀት ሁሉ ፍፃሜ እግዚአብሄር ያያል ይፈርዳል በሚል መረዳት ህይወትን መምራት ነው፡፡

ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣው በማወቅ እርሱን በመፍራት እስከተመላለስን ድረስ ህይወትን እንድንደሰትበት እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና


No comments:

Post a Comment