Popular Posts

Wednesday, January 13, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #ሰባት የእግዚአብሔር መንግሥት ደስታ

 

አቢይ የጥሞና ቃል #ሰባት የእግዚአብሔር መንግሥት ደስታ

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1417

የእግዚአብሄር መንግስት ሁለንተናዋ ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው፡፡ 

የእግዚአብሄር መንግስት አንዱ ውበትዋ በመንፈስ ቅዱስምሆነ ደስታ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት የመኖር አንዱ እድል ደስታ በሌለበት አለም ደስታን ማግኘት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት አንዱ ጥቅም በሁኔታዎች ያልተደገፈ ደስተኝነት ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት መልክ ከምንም ነገር ጋር ባልተያያዘ መልኩ በጌታ ደስ መሰኘት ነው፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡4

አለም በሚያሳዝን ነገር በተሞላች አለም ውስጥ ሃይላችንን የሚመጣው ከእግዚአብሄር ደስታ ብቻ ነው፡፡

እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው። መጽሐፈ ነህምያ 8፡10

እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በክርስቶስ በኩል ስለሰጠኽኝ ደስታ አመሰግናለሁ፡፡ የደስታዬ ምንጭ አንተ ብቻ ስለሆንክ ደስታዬ በምንም ነገር ስለማይለዋወጥ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና


No comments:

Post a Comment