Popular Posts

Friday, January 1, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #ሁለት

 


አቢይ የጥሞና ቃል #ሁለት

የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር

የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። የሉቃስ ወንጌል 10፡42

እግዚአብሄርን ማስደሰት ይቻላል፡፡ የተፈጠርንበትን የእግዚአብሄርን አለማ በምድር ላይ ፈፅመን ጌታን ማክበር ይቻላል፡፡

ጌታን በህይወታችን አስከብረን ለማለፍ የሚያስፈልገው በጣም ብዙ እና ውስብስብስን ነገር አይደለም፡፡

ብዙ ሰዎች እግዚአብሄር ያልጠየቀውንና የማይፈልገውን በማድረግ ሊያስደስቱት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማትና ከመታዘዝ ውጭ ያለ ማንኛውም ስራ ብክነት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገውን ስንሰጠው እንጂ በራሳችን አነሳሽነት የምንሰጠውን ስጦታ አይፈልገውም፡፡     

ጌታ ከእኛ የሚፈልገው ጥቂትና አንድ ነገር ነው፡፡

ጌታ ከእኛ የሚፈልገው በህይወታችን ለቃሉን የመጀመሪያውን ስፍራ እንድንሰጥ ብቻ ነው፡፡ ለቃሉ የመጀመሪያውን ስፍራ ስንሰጥ ቃሉን እንፈልጋለን እንታዘዛለን፡፡

ሌሎች ሀብቶች ሊመጡ ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ ከእኛ መቼም የማይወሰድ ሃብት ቃሉን ሰምቶ መታዘዝ ነው፡፡ ቃሉን ሰምተን በመታዘዝ ብቻ እግዚአብሄር በህይወታችን የሚፈልገው ነገር ሁሉ ማድረግ እንችላን፡፡ ቃሉን ሰምተን በመታዘዝ ብቻ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሄርን የሚያህል አምላክ ማስደሰት እንችላለን፡፡

እግዚአብሄር ሆይ በድጋሚ ለቃልህ ራሴን እሰጣለሁ፡፡ ቃልህን እፈልጋለሁ እታዘዛለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም አሜን

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና

No comments:

Post a Comment