Popular Posts

Saturday, February 1, 2020

ራሴን አግልያለሁ



ከሌሎች ጋር ራስን ከማስተያየት ከውድድር ከፉክክር ራሴን በፈቃዴ አግልያለሁ፡፡ ከፉክክርና ከውድድር ሩጫ አቋርጩ ወጥቻለሁ፡፡  
እግዚአብሄር የፈጠረኝ በአላማ ነው፡፡ እግዚአብሄር እኔን ከመፍጠሩ በፊት እኔ ወደ ምድር እንድፈጠር ያስፈለገበት ልዩ አላማ ነበረው፡፡ እኔ በምድር ላይ መፈጠሬ የሚያመለክተው አስቀድሞ የተፈጠርኩበት የእግዚአብሄርን አላማ መኖሩን ነው፡፡
ክብሬም ሞገሴም ስኬቴም በህይወቴ ያለውን የእግዚአብሄርን አላማ መከተልና መፈፀም ነው፡፡
በህይወቴ ያለው ማንኛም ስጦታና ክህሎት በህይወቴ ያውን የእግዚአብሄን አላማ እንዳስፈፅምበት የተሰጠኝ ስጦታ ነው፡፡
በህይወቴ ያለው ማንኛውም ስጦታ እና ፀጋ በህይወቴ ላለው የእግዚአብሄር አላማ አይበዛም አያንስም፡፡ በህይወቴ ካለው ከእግዚአብሄር አላማ የሚተርፍ ምንም ነገር የለም፡፡ በህይወቴ ካለው ከእግዚአብሄር አላማ ውጭ ተርፎ የማባክነው ትርፍ ስጦታም ሆነ ጉልበት የለኝም፡፡
በህይወቴ ያለውን ስጦታ የእግዚአብሄር አላማ ባልሆነ ነገር ላይ ካዋልኩት የእግዚአብሄርን አላማ በሙላት ከመፈጸፀም እጎድላለሁ፡፡
አለም የእግዚአብሄርን ፈቃድ ስለማትከተል እንድ የቀረላት የምትከተለው ነገር ፉክክር ውድድርና ራስን ከሌላው ጋር ማስተያየት ብቻ ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስን የማይከተሉ በአለም ያሉ ሰዎችና በቤተክርስትያን ውስጥም ሆነው አእምሮዋቸው በእግዚአብሄር ቃል ያልታደሰ ሰዎች ያላቸው ብቸኛ ነገር ውድድርና ፉክጅክር ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2
እግዚአብሄር በህይወቴ ልዩ አላማ እንዳለው ተረድቻለሁ፡፡ እግዚአብሄር በህይወቴ ያለውን አላማ እኔ ካልፈፀምኩት ማንም ሊፈፅምው እንደማይችል አውቃለሁ፡፡
እግዚአብሄር የሰጠኝን ማንኛውም ስጦታ እና ጊዜ  ከእኔ የተለየ የህይወት አላማ ከተሰጠው ከጎረቤቴ ጋር ራሴን በማስተያየት በመፎካከርና በመወዳደር አላባክነውም፡፡
በህይወቴ የምሮጠው በቂ ሩጫ አለኝ፡፡ ሰው ከኋላዬ መጥቶ ቀደምኩህ ካለኝ አልፎኝ እንዲሄድ መንገድ እከፍትለታለሁ እንጂ ከሮጠው ጋር አልሮጥም፡፡ ከእርሱ ጋር እንድፎካከር ቢያነሳሳኝም አልነሳሳም ለፉክክር ሞቻለሁ፡፡ ህያውነቴ የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም እንጂ ማንንም ሰው ለመቅደም ለመብለጥና ለማስቀናት አይደለም፡፡
አላማዬ ግቤን መምታት እንጂ ከመንገዴ እና ከሩጫዬ አቋርጬ ከንቱ ውድድርና ፉክክር ውስጥ መሳተፍ  አይደለም፡፡ ፉክክር ውስጥ ለመሳተፍ አቅሙም ፍላጎቱም የለኝም፡፡ ሸክሜ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወቴ የመፈፀም እንጂ እንጂ ውድድር አይደለም፡፡
ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡4
የማተኩረው ሩጫዬን መፈጸሜን እንጂ ማንንም መቅደሜ ላይ አይደለም፡፡ የማስተያየት የፈፀምኩትን የእግዚአብሄርን ፈቃድና ልፈፅመው የሚገባኝንም የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንጂ ለምን እንደተጠራ የማላውቅውን የጎረቤቴን ስራ አይደለም፡፡
ሰዎች ስላለቻለ ነው ያቋረጠው ካሉኝ እውነት ብለዋል፡፡ አልችልም፡፡ አይጠቅመኝም፡፡ አልፈልግም፡፡
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡12
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አክሊል #ሽልማት #ትንሳኤ #ሰማይ #የማይጠፋአከሊል #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ውድድር #ፉክክር #ዋጋ

No comments:

Post a Comment