Popular Posts

Saturday, February 15, 2020

በእምነት ባለ ጠጎች



የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? የያዕቆብ መልእክት 25
በእምነት ባለጠጋ መሆን ማለት የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ይሰጠኛል ብሎ በእግዚአብሄር መሪነት ፣ ጥበቃና አቅርቦት መታመን ማለት ነው፡፡ በእምነት ባለጠግነት ማለት እግዚአብሄርን በቃሉ በሙላት ማመን ማለት ነው፡፡ በእምነት ባለጠግነት ማለት በነገር ሁሉ እግዚአብሄርን ማለት ነው፡፡
ለሰው አስተማማኝ ባልሆነው በኪሱ ውስጥ ባለው ገንዘብ ባለጠጋ ከሚሆን ይልቅ በነገር ሁሉ ለዘላለም ባለጠጋ በሆነው በእግዚአብሄር ላይ መታመን ይሻለዋል፡፡ ሰው በጊዜያዊ ገንዘብ ባለጠጋ ከሚሆን ይልቅ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ በሆነው በእግዚአብሄርን ላይ ባለው እምነት ባለጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡  
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡12
ለሰው በሌላ ሰው ላይ ከሚታመን ይልቅ በእግዚአብሄር ላይ ያለውን መታመን ቢያበዛ ያዋጣዋል፡፡
እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል ያቈስለውማል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 1821
ለሰው በሁኔታዎች ባለጠጋ ከመሆን እና በሁኔታዎች ላይ ከሚታመን ይልቅ በሁኔታዎች በማይለውጥ እርሱ ግን ሁኔታዎችን የሚለውጥ በእግዚአብሄር ላይ በመታመን ባለ ጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
ለሰው በገንዘብ ባለጠጋ ከመሆን ይልቅ በእምነት ባለጠጋ መሆን ይሻላል፡፡ ተለዋዋጭ በሆነው በማያስተማምን በአለም ሃብት ባለጠጋ ከመሆን ይልቅ በእርሱ የሚያመነ አያፍርም በተባለለት በእግዚአብሄር ላይ ባለ እምነት ባለጠጋ መሆን ያስተማምናል፡፡
መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡11
ሰው ምንም ማድረግ በማይችለው በምንም አይነት በማያስመካ በሰው ጥበብ ላይ ከሚታመን ይልቅ በእግዚአብሄር ላይ ባለ እምነት ባለጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24
ሰው በሚደክመውና በሚታክተው በራሱ ሃይል ከሚተማመን ይልቅ በማይደክመውና በማይታክተው ሰውን በሚያበረታው በእግዚአብሄር ላይ ባለው እምነት ባለጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡30-31
ሰው ከምንም በላይ እንከን የሌለባትን የእግዚአብሄርን በረከት በሚያገኝበት በእምነት ባለጠጋ መሆን ይሻለዋል፡፡
የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም። መጽሐፈ ምሳሌ 10፡22
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment