ነፋስን
የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። መጽሐፈ መክብብ 11፡4
ህይወት
የእምነት ጉዞ ነው፡፡ ህይወትን በሚገባ ማጣጣም ከፈለግክ በእምነት መኖር መጀመር አለብህ፡፡ በእምነት መራመድ ካልጀመርክ የህይወትን
እውነተኛውን ጣእም በፍፁም አታገኘውም፡፡ ሰው መኖር የሚጀምረው በእምነት መራመድ ሲጀምር ብቻ ነው፡፡ የሰው እውነተኛ መኖሪያ የእግዚአብሄር
ቃል እምነት ነው፡፡
እርሱም
መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4
ሰው
ዲዛይን የተደረገው ለእምነት ኑሮ ነው፡፡ ሰው የሚኖረው በእምነት ነው፡፡
እነሆ፥
ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ትንቢተ ዕንባቆም 2፡4
እምነት
የሚመጣው ከእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡
እንግዲያስ
እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17
በእግዚአብሄር
መልክና አምሳል ለተፈጠረው ክቡር ለሆነው ሰው ለሰው ልጅ ከእግዚአብሄ ቃል ያነሰ ኑሮ አይገባውም፡፡
እርሱም
መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4
የሰው
እውነተኛ እርካታ በእምነት ሲኖር ነው፡፡
ነገሮች ሆነው ከማየትህ በፊት የእግዚአብሄርን
ቃል አምነህ እርምጃ ካለወሰድክ ከእግዚአብሄር ጋር መኖር አትችልም፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር የምትገናኘው በስጋ አይን የማይታየውን
መንፈስ የሆነውን እግዚአብሄርን የምትሰማው ፣ እግዚአብሄርን የምትነካው ፣ እግዚአብሄርን የምታየው ሁሉ በእምነት ነው፡፡ የእግዚአብሄር
ነገር ሁሉ በእምነት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙረ ዳዊት 33፥4
ነገሮች ተለውጠው ደስ ለመሰኘት የምትጠብቅ ከሆነ
ደስ መሰኘቱን እርሳው፡፡ ነገሩን የሚለውጠው በእምነት እርምጃ በመውሰድ ደስ በመሰኘትህ ብቻ ነው፡፡
የምትፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ኪስህ ከገቡ በኋላ
እፎይ ለማለት እየጠበቅክ ከሆነ የማይፈፀም ተስፋ እየጠበክ ነው፡፡
ለማመን ፀሎትህ እስኪመለስ እየጠበቅክ ከሆነ ፀሎትህ
ለመፈፀም የአንተን እምነት እየጠበቀ ነው፡፡
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት
እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። የማርቆስ ወንጌል 11፡23-24
ሁሉ ደህና ነው ለማለት ነገሮች ሁሉ ተስተካክለው
እስክታይ አየጠበቅክ ከሆነ በከንቱ ትጠብቃለህ፡፡
ከመዝራትህ በፊት ሁኔታዎችን እየጠበቅክ ከሆነ
መቼም አታጭድም፡፡
ምልክት ከማየትህ በፊት ማመን አለብህ፡፡ እምነትንም
የሚያመጣው የእግዚአብሄር ቃል እንጂ ምልክት እምነትን አያመጣም፡፡ ምልክቱን የሚያመጣው እምነትህ ነው፡፡
ከውጤት እና ከምልክት በፊት የእምነት እርምጃ
ይቀድማል፡፡
እንጀራህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን
በኋላ ታገኛዋለህና። መጽሐፈ መክብብ 11፡1
አስቀድመው ምልክትን የሚፈልጉ ካላየሁ አላምንም
የሚሉ ሰዎች እግዚአብሄርን የማይፈልጉ አሿፊ ሰዎች ናቸው፡፡
ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት። ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ። የማቴዎስ ወንጌል 16፡1፣4
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት
አያጭድም። መጽሐፈ መክብብ 11፡4
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #ስብከት
#ቃል #ዝራ
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment