Popular Posts

Saturday, February 8, 2020

ኮሮና ቫይረስን እግዚአብሔር አልፈጠረውም



እግዚአብሄር ፍጥረቱን ሲፈጥር የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ጤነኛ ጠንካራ ብርቱ አምራች እንዲሆን በሰላም ፣ በብርታትና እና በጤንነት ነው፡፡
እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡31
ኢየሱስን ወደ ምድር ሲመጣ የመጣው ለሰዎች ህይወት እንዲሆናችው እንዲያውም እንዲበዛላቸው ነው፡፡
በተቃራኒው ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊታያርድና ሊያጠፋ ነው ፡፡ ሰዎች ባለማወቅ በፈቀዱለት መጠን ሰይጣን የሰው ልጆችን ሰላም ደስታ ጤንነት ብርታት ሁሉ ይሰርቃል፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
እግዚአብሄር ሰዎች በምድር እንዲኖሩ እርሱን እንዲያውቁ ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሄር በጣም መልካም ከመሆኑ የተነሳ በእምነታችው የማይፈወሱትን ሰዎች ለዶክተሮች በሰጣቸው እውቀት አማካኝነት በህክምና እንዲፈወሱ ረጅም እድሜ እንዲኖሩ ይፈልጋል፡፡
ሰይጣን እንጂ እግዚአብሄር የሰው ልጆች ጠላት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የማንም ስቃይና መከራ አያስደስተውም፡፡
የእግዚአብሄርን ልብ የምናየው ኢየሱስ በምድር ሲመላለስ እየዞረ በሃይል የታመሙትን ይፈውስ ነበር፡፡
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሐዋርያት ሥራ 10፡38
እግዚአብሄር እርሱን ለማያውቁ ሰዎችም እንኳን መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ለሰዎች ሁለተኛ እድል መስጠት ይፈልጋል፡፡ እርሱን እንዲያውቁትና እንዲድኑ እግዚአብሄር ሰዎችን ይታገሳል፡፡
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡44-45
በቻይና ላይ ብሎም በመላው አለም ላይ የመጣውን ይህን የኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክኒያት በማድረግ ለቻይና ህዝብ እንጸልይ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የቻይና ህዝብ እግዚአብሄርን እንዲያውቅ ስለቻይና ህዝብ እንማልድ፡፡
በተሰጠን በልጅነት ስልጣን ሁልጊዜ የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን የሰይጣን ዲያቢሎስን አሰራር በኢየሱስ ክርሰቶስ ስም ፀንተን እንቃወም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa  
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሄር #ጌታ #ኢየሱስ #ቃል #መዳን #መንፈስቅዱስ #ሞቱናትንሳኤ #መስቀል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ኮሮና #ኮሮናቫይረስ #ቻይና #መንግስተሰማያት #መፅሃፍቅዱስ #ፍርድ #የዘላለምህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

No comments:

Post a Comment