Popular Posts

Monday, February 3, 2020

ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች - የመንፈሳዊነት መመዘኛ



አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።ትንቢተ ኢሳይያስ 6፡3
የመንፈሳዊነት አንደኛው መመዘኛ በሚታየው ሳይሆን በማይታየው መመላለስና መኖር ነው፡፡ የሚታየውን የሚያይ ሰው የሚታየው ሁሉ ያስጨንቀዋል ያውከዋል፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
የሚታየውን የማያይ ሰው ይልቁንም የማይታየውን የሚያይ ሰው በመንፈስ የሚመላለስ መንፈሳዊ ሰው ነው፡፡
መንፈሳዊ ሰው ከምድር ውጥንቅጥና መከራ በላይ የእግዚአብሄርን ክብር ያያል፡፡ መንፈሳዊ ሰው በስጋ አይን ከሚየታየው ተግዳሮት በላይ የእግዚአብሄርን ንጉስነት እና ሃያልነት ያያል፡፡
መንፈሳዊ ሰው እየጠፋ ያለውን ነገር ሳይሆን እየታደሰ እየከበረ ያለውን ነገር ይመለከታል፡፡
ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡16
መንፈሳ ሰው ፈተናውን ሳይሆን በፈተናው የሚገኘውን ጥቅም ያያል፡፡ መንፈሳዊ ሰው ከፈተና እና ከሃዘን ውስጥ የእግዚአብሄርን ድንቅ አሰራር ያያል፡፡  
በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡6-7
መንፈሳዊ ሰው ከከበበው ከጠላት ሃይል በላይ ከእርሱ ጋር ያለውን የእግዚአብሄርን ሰራዊት ያያል፡፡
እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡16
መንፈሳዊ ሰው የምድር ነገር ሁሉ ሲጮህ በዝምታ ካለማቋረጥ የሚሰራውን የእግዚአብሄርን ስራ ይረዳል፡፡
ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነው፥ ሕግህንም ሻሩት። መዝሙረ ዳዊት 119፡126
ሌሎች ሰዎች ሁሉ የተሸነፉ በሚመስላቸው ጊዜ መንፈሳዊ ሰው ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር የሚሰራውን ስራ አውቆ በመረዳት ያርፋል፡፡
እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።  ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡21
ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።ትንቢተ ኢሳይያስ 63
Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ሃይል #ዘላለም #ጥበብ #የእግዚአብሄርመንግስት #ንጉስ #እርሾ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment