መጽሐፍ፦
በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡11
የሚያምን
አያፍርም
ስለዚህ
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ የሚያምን አያፍርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 28፡16
የሚያምን
አይታወክም
በእግዚአብሔር
የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው። መዝሙረ ዳዊት 125፡1
የሚያምን
አያቅተውም
ኢየሱስም፦
ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። የማርቆስ ወንጌል 9፡23
የሚያምን
አይፈራም
ኢየሱስ
ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። የማርቆስ ወንጌል 5፡36
የሚያምን
አይጠፋም
በእርሱ
የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። የዮሐንስ ወንጌል 3፡16
የሚያምን
አያፈገፍግም
ጻድቅ
ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም። ወደ ዕብራውያን 10፡38-39
የሚያምን
ከተስፋው አይጎድልም
በእምነትና
በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። ወደ ዕብራውያን 6፡11-12
የሚያምን
ሞቶ አይቀርም
ኢየሱስም፦
ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ የዮሐንስ ወንጌል 11፡25
የሚያምን
አይረገምም
እግዚአብሔር
ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው። መዝሙረ ዳዊት 34፡8
በእርሱ
የሚያምን ሁሉ አያፍርም
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ስፋት
#እርካታ #ፍሬያማነት #ክንውን #አሸናፊነት #በጎነት #ቅን #እምነት #ፅድቅ #ደስታ #ሰላም #ኢየሱስ #ጌታ #ሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment