Popular Posts

Sunday, February 16, 2020

እውነትን ግዛ



እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡23
እውነት የእግዚአብሄር የጥንቱ የቀደመው ሃሳብ ነው፡፡ እውነት የእግዚአብሄር ኦሪጅናል ሃሳብ ነው፡፡ እውነት የእግዚአብሄር የመጀመሪያው እቅድ ነው፡፡
ኢየሱስ ስለእግዚአብሄር የጥንቱ የመጀመሪያው ሃሳብ ከጥንት ግን እንደዚህ አልነበረም በማለት ስለመጀመሪያው የእግዚአብሄር ሃሳብ ስለ ወሳኝነት እውነት ይናገራል፡፡ ስለምንም ነገር ክርክርር ሲነሳ የጥንቱ የእግዚአብሄር ሃሳብ ከፍተኛው ባለስልጣን ነው፡፡ እውነት ለምንም ነገር መነሻ ማጣቀሻ ነው፡፡ የጥንቱ የእግዚአብሄር ሃሳብ ለየትኛውም ትምህርት ማስተያያ ማጣቀሻ ነው፡፡
እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። የማቴዎስ ወንጌል 19፡8
ከምንም ነገር በላይ እውነት ሃያል ነው፡፡ ጥበበኛ ሰው ማደረግ የሚችለው የተሻለ ነገር ከእውነት ጋር መወገን ብቻ ነው፡፡ ሰው ምንም ጠቢብ ቢሆን ከእውንት ጋር ተጋፍጦ አይበረክትም፡፡ ሰው ምንም ሃያል ቢሆን ከእውነት ተቃራኒ ጎን ቆሞ አይሳካለትም፡፡ ሰው ምንም ምንም ባለጠጋ ቢሆን እውነተን ተቃውሞ አይጸናም፡፡ ሰው ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም አይችልም፡፡
 ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8
ሰው ስለስኬቱ እግዚአብሄርን መፈለግ አለበት፡፡ ሰው ስለመከናወኑ የእግዚአብሄርን ሃሳብ መፈለግ እና ማግኘት አለበት፡፡ ሰው እንዲከናወን የጥንቱን የእግዚአብሄርን ሃሳብ መፈለግ ግዴታ ነው፡፡ ሰው እውነትን መፈለግ አለበት፡፡ ሰው እውነትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ መክፈል አለበት፡፡ ሰው እውነትን ለማግኘት እውነትን ለመኖርና በእውነት ለመፅናት ዋጋ መክፈል አለበት፡፡ ሰው ስለምንም ነገር ዋጋ ባይከፍል ስለእውነት ዋጋ መክፈል አለበት፡፡ ስለእውነት የሚከፈለው ዋጋ ለምንም ከሚከፈለው ዋጋ ይሻላል፡፡
እውነት እውነተኛ መዝገብ ነው፡፡ እውነት እውነተኛ ሃብት ነው፡፡ ሰው ያለውን ነገር ሁሉ እውነትን ለመግዛት ቢከፍል አይቆጭም፡፡
ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ። የማቴዎስ ወንጌል 13፡44
ሃብት የሚመስሉ ብዙ ሃብቶች አሉ፡፡ እውነት ግትን እውነተኛ ሃብት ነው፡፡ እውነት የማይጠፋ የማይለውጥ ዘላቂ ሃብት ነው፡፡
እውነትን ለማግኘት የሚከፈለው ዋጋ ሁልጊዜ አመርቂ ውጤትን ያስገኛል፡፡ የእግዚአብሄርን እውነት ለማግኘት ኢንቨስት የምናደርገው ኢንቨስትመንት ሁሉ አትራፊ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ እውነት ከለም መሬቶች ሁሉ ለም የሆነ ብዙ ፍሬን የሚያስገኝ ለም መሬት ነው፡፡
ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት። የማቴዎስ ወንጌል 13፡46
እውነት የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእውነት መገኛ እና ምንጭ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ ያለው እውነት ነው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ ያላለው እውነት አይደለም፡፡
በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።  የዮሐንስ ወንጌል 17፡17
የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። መዝሙረ ዳዊት 119፡160
በህይወታችን ማድር የምንችለው የተሻለ ነገር ስለሆነ የእግዚአብሄርን ቃል እውነት እንፈልግ እናግኝ እንለማመድ እንፅናበት፡፡  
እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። መጽሐፈ ምሳሌ 2323
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እውነት #ቃል  #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት

No comments:

Post a Comment