Popular Posts

Thursday, July 18, 2019

የእግዚአብሔርን ባለጠግነት የምንካፈልበት ስልት



እግዚአብሄር ባለጠጋ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ የሚጎድለው የሌለ ባለጠጋ አምላክ ነው፡
እርሱ ባጠጋ ሆኖ ልጆቹ እንዲያጡና እንዲጎድላቸው የሚፈልግ አባት እንደሌለ ሁሉ እግዚአብሄር ልጆቹም ያጡትንና የጎደላቸውን ነገር ይው እንዲልምኑት ይፈልጋል፡፡ ልጆቹ ከእርሱ ባለጠግነት ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ አባት ሁሉ እግዚአብሄርም በፀሎት ከእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋይ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡
ልጆቹ ከእርሱ ባለጠግነት እንዲካፈሉ የሚፈልግ ጌታ የሰው ልጆች እንዲፀልዩ በብዙ ቦታዎች ያበረታታል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄርን ያየው አንዳች እንኳን የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው እንደሚል ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ልብ ሲተርከው ሰዎች መፀለይ እንዳለባቸው በብዙ ቦታዎች በምሳና ካለ ምሳሌ በተደጋጋሚ ሲያስተምር እንመለከታለን፡፡  
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7
ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? የሉቃስ ወንጌል 18፡1፣7-8
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16፡23-24
ኢየሱስ ስለፀሎት ያስተማረበትን ስንመለከት እግዚአብሄር ለልጆቹ ያልውን ቅናት እንመለከታለን፡፡ ልጆቹ ምን የመሰለ አባት በሰማይ እያላቸው ባለመለመናቸው ብቻ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋዮች አለመሆናቸውን አይቶ ይቀናል፡፡ ኢየሱስ ስለፀሎት ያስተማረውን ስንመለከት ልጆቹ ቶሎ ስለፀሎት ተረድተው እንዲፀልዩና ከእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋይ እንዲሆኑ የቀናላቸውን የእግዚአብሄርን ቅናት እናስተውላለን፡፡
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ የዮሐንስ ወንጌል 16፡24
እንደ እውነቱ ከሆነ መፀለይና መቀበል የሚገባንን ያህል አልተቀበልንም፡፡ የእግዚአብሄር ግምጃ ቤት ሙሉ ነው፡፡  
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-8
ብዙ ክርስትያኖች እግዚአብሄር አባታቸው ባለጠጋ ሆኖ እነርሱ ግን በጉድለት የሚኖሩበት ምክኒያት ለመፀለይ በመጀመሪያ ራሳቸውን ስለሚያዩ ነው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ እንደ ደሞዛችሁ መጠል ለምኑ ፣ እንደ ገቢያቹ መጠን ለምኑ ፣ እንደ ባንክ ሂሳባችሁ መጠን ለምኑ ያለ ይመስላቸዋል፡፡
እግዚአብሄር ግን ያው ለምኑ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚያበረታን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድንለምን ነው፡፡
ሲጀመር የሚለምን ሰው የሚለመነው ነገር ያለው ሰው አይደለም፡፡ የሚለምን ሰው የጎደለው የሌለው ሰው ነው፡፡ የሚለምን ሰው እንዲኖረው የሚፈልግ እንጂ ያለው ሰው አይደለም፡፡  
ያለመቀበላችን ምክኒያት አለመለመናችን ነው፡፡
ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡2
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ለምኑ #ፈልጉ #አንኳኩ #ይቀበላል #ያገኛል #ይከፈትለታል #ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Wednesday, July 17, 2019

በጣም የጓጓንለት ነገር ያሳፍረናል


ለአንድ ነገር በጣም መጓጓት ለነገሩ ያለንን የእውቀት ማነስ ሊያሳይ ይችላል:: ለአንድ ነገር ያለን መጓጓት ግምት አሰጣጣችን መዛባቱን ከማሳየቱም በላይ ይፍጠንም ይዘግይም እንደሚያሳዝነን እርግጥ ነው::

ከሰማይ በታች የሚያጓጓ ነገር የለም:: ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም:: አዲሱ ነገር ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው:: አዲሱ ነገር በፍቅር መኖር ነው:: አዲሱ ነገር ጌታንና ሰውን መውደድ ነው:: አዲሱ ነገር ጌታን መከተልና ማምለክ ነው::
ከጌታ ውጭ በጣም የሚያጓጓ ምንም ነገር የለም::
የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፤ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም። መጽሐፈ መክብብ 1:9
ሰው ሰውን የማገልገል ሀላፊነቱን ከተረዳው ስለ ስልጣን በጣም አይጓጓም::
ሰው ከዝነኝነት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሀላፊነትተረዳ የዝነኝነት ጥቅም ያን ያህል አያጓጓውም::
ሰው ሀይሉን በሚገባው ቦታ ላይ ብቻ የማዋል ከፍተኛ ሀላፊነት እንደተጫነበት የሚርዳ ሰው ሃይል እና ስልጣን  ለማግኘት አይቸኩልም:: ስልጣን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የማገልገል ሃላፊነትም እንደሆነ የተረዳ ሰው ስልጣንን ያን ያህል አይመኝም፡፡
የትዳርን ጥቅሙን ብቻ ሳይሆን ሃላፊነቱንም በሚገባ የተረዳ ሰው ተግዳሮቱን እንዳልተረዳው ሰው የብቸኝነት ጊዜውን ሳያጣጥል አክብሮ በሚገባ ይጠቀምበታል::
ከሚጠብቀው ነገር ውስጥ ጥቅም ብቻ የሚጠብቅና ሃላፊነቱን የማይረዳ ሰው በራሱ ይሰናከላል:: እያንዳንዱ ጥቅም ከሃላፊነት ጋር ይመጣል::
እያንዳንዱ አገር የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የማይረዳ ሰው አገርመለውጥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከተግዳሮት ለማረፍ እጅግ ይጓጓል::
ለነገ ከመጠን በላይ የሚጓጓው እያንዳንዱ ቀን ከራሱ ጭንቀት ጋር አብሮ እንደሚመጣ የማያውቅ ሰው ብቻ::
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6:34
ከእግዚአብሄር ውጭ ሙሉ ትኩረታችንን ሊወስድ የሚገባው ምንም ነገር ሊኖር አይገባውም፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ በጣም የምንጓጓለት ነገር ከመጠን በላይ ስላጋነንነው ያስቀይመናል፡፡  
ለእግዚአብሄር ብቻ መስጠት ያለብንን ትኩረትሌላ ለምንም ነገር በመስጠት እግዚአብሄርን አንስቀናው ::
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ዘላለማዊ #አዲስ #ልብ #ሰማይ #ዘላለም #ጌታ #ከፀሐይበታች #ያልፋሉ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Sunday, July 14, 2019

ዛሬ ካልሆነ መቼ?


ህይወት ደስ ይላል፡፡ ህይወት ምን ያህል እንደሚጣፍጥ የምናውቅው ልናጣው ስንል ነው፡፡ የህይወትን ክብር ይበልጥ የምንረዳው ከሞላ ጎደል አጥተነው ስናገኘው ነው፡፡
እግዚአብሄርን አሁን ካላመሰገነው መቼ እናመሰግነዋለን፡፡
ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል። ትንቢተ ኢሳይያስ 38፡18-19
አንድ የእግዚአብሄር ሰው ሲናገር ለስኬት የሚያስፈልገው ቤት ብቻ ነው ይላል፡፡ ሲቀጥልም ለስኬት የሚያስፈልገው በስጋ ውስጥ መኖር ህያው መሆን በህይወት መኖር ብቻ ነው፡፡ በህይወት የሚኖር ሰው ለስኬት ተስፋ አለው፡፡ ሰው በምድር ላይ ለስኬት ተስፋው የሚያከትመው ከስጋ ከወጣ ብቻ ነው፡፡
አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፤ እኛ ሕያዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔርን እንባርካለን፡፡ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 115፡17-18
እግዚአብሄርን ለማመስገን የሚያስፈልጉት ነገሮች ህያው መሆንና ህያው መሆን ብቻ ናቸው፡፡
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት። በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት። በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት። በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት። እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 150፡1-6
እግዚአብሄርን ለማመስገን ቀን መቅጠር አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን አንዱና ብቸኛው ቅድመ ሁኔታ ህያው መሆን በህይወት መኖር ነው፡፡ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ።
ነገ ያንተ አይደለም፡፡ ዛሬን በህይወት የጠበቀህን ነገን ሊሰጥህ የሚችለውን እስትንፋስህን በእጁ የያዘውን እግዚአብሄርን ዛሬ አመስግን፡፡
አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው። የያዕቆብ መልእክት 4፡13-16
እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት። ዕብራውያን 13፡15
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 150፡6
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

Thursday, July 11, 2019

መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች


ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡27-28
እስራኤል ህይወቱ ቅርፅ አልባ ስለሆነበት መንገዴ ከእግዚአብሄር ተሰውራለች ሲል እንመለከተዋለን፡፡ እስራኤል ህይወቱ የተበታተነ እና የተወሳሰበ ስለሆነ ከዚህ ቅርፅ አልባ ህይወቱ ሊወጣ እንደማይችል አስቧል፡፡ እስራኤል ጥያቄው ውስብስብ በመሆኑ ሊፈታ እንደማይችል ተስፋ ቆርጧል፡፡ እስራኤል በህይወቱ ካሉ መልሶች ይልቅ ጥያቄዎቹ በዝተዋል፡፡
አሁንም እያንዳንዳችን አንዳንዴ ህይወታችን እንደተበታተነ ቅርፅ አልባ እንደሆነና የህይወታችንን መንገድ ማንበብ እንደማንችእል ይሰማናል፡፡ አንዳንዴ የህይወታችን ክር እንደተበተበና ውሉ እንደጠፋ እንደተወሳሰበ ይሰማናል፡፡
አንዳንዴ የህይወታችንን መንገድ ጫፉ እንደማይያዝ መጀመሪያውና መጨረሻው እንደማይታወቅ ይሆናል፡፡ የህይወታችንን እንቆቅልሽ መጀመሪያውንና መጨረሻ ማገናኘት ያቅተናል፡፡
ይህ ስሜት መርገም አይደለም፡፡ ይህ ስሜት ለእርዳታ እግዚአብሄርን እንድንፈልግ ትሁት የሚያደርግን ተፈጥሮአዊ ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት ህይወታችንን በራሳችን እንደማንወጣው የሚያስታውሰን ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት ህይወታችን በእግዚአብሄር እንጂ በእኛ እንዳልተያዝ የሚያስታውስን ስሜት ነው፡፡
የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት። መጽሐፈ ኢዮብ 12፡10
ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም። ትንቢተ ዳንኤል 5፡23
ህይወታችንን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ማወቅ የለብንም፡፡ የምናውቃቸው ነገሮች አሉ የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሁሉንም ካወቅን እግዚአብሄር እንጂ ሰው ልንሆን አንችልም፡፡ ሁሉንም ነገር ካወቅን በእግዚአብሄር ላይ መታመን አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም ነገር ማድረግ ከቻልን የእግዚአብሄር እርዳታ አያስፈልግም፡፡
ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ኦሪት ዘዳግም 29፡29
ሁሉን በሚያውቅ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ያለብን እኛ እውቀት ሁሉ ስለሌለን ነው፡፡
የእግዚአብሄር አምላካዊ መልስ ግን እንዲህ ይላል፡፡
እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡27-28
አንተ አላወቅክም ማለት እግዚአብሄር አላወቀም ማለት አይደለም፡፡ አንተ የህይወትህ ንድፍ ዲዛይን የለህም ማለት እርሱ የለውም ማለት አይደለም፡፡  
አንተ የሚያስፈልግህ አንድ ነገር በምታውቅው እርምጃ እየወሰድክ በማታውቅው በሚያውቀውና ማስተዋሉ በማይመረመረው እግዚአብሄር ላይ መደገፍ ነው፡፡ እንደ እርሱ እንድትበረታ ፣ እንደ እርሱ እንድታስተውል ፣ እንደ እርሱ እንድታውቅና እንደ እርሱ እንድትራመድ የሚያስፈልግህ እርሱን በመተማመን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡  
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡31
እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡፡
እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና። ትንቢተ ኢሳይያስ 41፡13
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #መጠበት #መተማመን #እምነት #ያድሳሉ #ይወጣሉ #አይደክሙም #አይታክቱም #እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Tuesday, July 9, 2019

ፍቅር አይወድቅም



ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8
ፍቅር ዘላለማዊ ነው፡፡
ፍቅር የእግዚአብሄር ባህሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደማይወድቅ ሁሉ ከእግዚአብሄር የሚገኘውና በእግዚአብሄር የሚደገፈው ፍቅር አይወድቅም፡፡ እግዚአብሄር ዘላለማዊ እንደሆነ ሁሉ ፍቅር ዘላለማዊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጊዜው እንደማያልፍበት ሁሉ ፍቅር ጊዜው አያልፍበትም፡፡ እግዚአብሄር ጊዜ እንደማይሽረው ሁሉ ፍቅር ጊዜ አይሽረውም፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡7-8
ፍቅር ጊዜያዊ አይደለም፡፡
ፍቅር የአንድ ሰሞን አይደለም፡፡ ፍቅር ወረት አያውቅም፡፡ ፍቅር አይለወጥም፡፡
ፍቅር ሃያል ነው፡፡
ፍቅር የሚያሸንፈው የለም፡፡ ፍቅር ምንም ህግ አይገዛውም፡፡ ፍቅርንብ የሚከለክል ህግ የለም፡፡ ፍቅርን የሚረታ ስልጣን የለም፡፡
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22-23
ፍቅር ደካማ አይደለም፡፡
ፍቅር በሁኔታዎች የሚደገፍ ደካማ አይደልም፡፡ ፍቅር አሸናፊ ነው፡፡ ፍቅር ሁሉን ይረታል፡፡ ፍቅር እንደሁኔተው ይሚለዋወጥ አይደለም፡፡ ፍቅር የራሱ የማይለወጥ መርህ ያለው ባህሪ ነው፡፡
ፍቅር ቋሚ እና ዘላቂ ነው፡፡
ፍቅር ዘላቂ ነው፡፡ ፍቅር አይለወጥም፡፡ ፍቅር አይቆምም፡፡
ፍቅር ጊዜያዊ አይደለም፡፡
ፍቅር የውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር የመረዳት ነገር ነው፡፡ ፍቅር ስሜታዊ አይደለም፡፡ ፍቅር ዛሬ ታይቶ ነገ የሚጠፋ አይደለም፡፡ ፍቅር እስከ መጨረሻው ይሄዳል፡፡
ፍቅር ያሸንፋል፡፡ በብዙ ነገር የማይረቱ አሉ፡፡ ፍቅር የማይረታው ሰው ግን ማንም የለም፡፡ የየሰው መረዳት እንደሰው አይነት ይለያያል፡፡ ብዙ ነገርን ሊረዳ የማይችል ብዙ ሰው አለ፡፡ ፍቅርን ሊረዳ የማይችል ሰው ግን የለም፡፡ ብዙ ነገር የማይማረከው ሰው አለ፡፡ ፍቅር የማይማረከው ሰው ግን የለም፡፡
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። የዮሐንስ ወንጌል 13፡35
ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ 1 ቆሮንቶስ 138
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Friday, July 5, 2019

ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው


እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፈሩ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፤ ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 3:16-18
ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፡፡
ብዙ ጊዜ የእግዚአብሄርን ክንድ አይተናል ነገር ግን አሁን ስላለንበት ሁኔታ ደግሞ ይህንንም ሊያደርግ ይችላል ብለን እናስባለን፡፡ መልሱ ግን ያ አላልፍም ብለህ ግን ያለፍክበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፡፡ ያንን አለልፍም ብለህ ያለፍክበት ሁኔታን እንደለወጠ ሁሉ ይህንንም ሊለውጥ ይችላል፡፡ ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሄር ይቻላል፡፡  
እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ። የሉቃስ ወንጌል 18፡27
ብዙ ጊዜ ተስፋ እንድንቆርጥና ወደኋላ እንድንመለስ የሚፈትነንም በአካባቢያችን ስለሁኔታው እውነተኝነት የሚመሰክሩ ምልክቶች አለመኖራቸው ነው፡፡
እግዚአብሄር ለዚህም መልስ አለው፡፡ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችሁ ምልክቱ ስለሁኔታው እውነተኝነት የሚመሰክሩ ምልክቶች አለማየታችሁ ነው፡፡
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፡፡
የፈራችሁትም ውድቀት አይደርስባችሁም፡፡
እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።
ውድቀት አይደርስባችሁም ብቻ ሳይሆን በህይወታችሁ እውነተኛውን ድል ታገኛላችሁ፡፡ በዚህም እግዚአብሄር የልባችሁ መሻት ይሞላል፡፡
ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል።
ምክንያቱም ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፡፡
እግዚአብሄርን የሚያሳስበው ሰውን የሚያሳስበ አይደለም፡፡ ሰውን የሚያሳስብው ውሃ አለመምጣቱ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያሳስበው ነገር በእግዚአብሄር አይን ቀላል የሆነውን ነገር እግዚአብሄር ሲያደርግ ሰው ለታእምሩ አለመዘጋጀቱ ነው፡፡ የሰው ትኩረት ታእምሩ እንዴት እንደሚሆን ነው፡፡ የእግዚአብሄር ትኩረት ሰው ተአምሩን እንዴት በሚገባ እንደሚጠቀምበት ነው፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፈሩ።
እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፈሩ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፤ ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 3:16-18
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
 ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
 #ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Monday, July 1, 2019

የህይወት ከፍተኛው የእርካታ ደረጃ

የህይወት ከፍተኛው የእርካታ ደረጃ
ሰው በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል በእግዚአብሔር ክብር ተፈጥሯል:: 
እንደ ዝና ገንዘብ ስልጣን ያሉ ተራ ነገሮች በራሳቸው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል በእግዚአብሔር ክብር ለተፈጠረው ሰው እውነተኛና ዘላቂ የእርካታ ስሜት ሊሰውን  አይችሉም:: 
እንደ ዝና ገንዘብ ስልጣን ያሉ ነገሮች ሰው የተፈጠረበት ሌሎችን በፍቅር የማገልገል አላማ ለማሳካት የሚጠቅሙ መሳሪያዎች እንጂ በራሳቸው የህይወት ግብ አይደሉም::
ሰው የሚረካው የተፈጠረበትን የእግዚአብሄር አላማ ሲፈፅም ብቻ ነው:: 
ሰው የሚረካው የተፈጠረበትን ሌሎችን የማገልገል አላማ ከግብ ሲያደርስ ብቻ ነው :: 
ሰው የሚረካው የተፈጠረበትን ሌሎችን በፍቅር የማገልገል አላማ ከግብ ሲያደርስ ብቻ ነው::
በሚያደርገው ነገር ሁሉ የተሳካለት ሰው የተፈጠረበት የእግዚአብሔርን አላማ ከሳተው ውጤቱ ሁሉም ነገር በዜሮ እንደሚባዛ ውጤቱ ዜሮ ነው:: 
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1 ቆሮንቶስ 13:1-3 

ሰው ብዙ ዝና ገንዘብና ስልጣን ባይኖረውም ባለው ነገር ሁሉ ተጠቅሞ ሌላውን በፍቅር የሚያገለግል ሰው ከእርሱ በላይ የተሳካለት ሰው የሌለ የመጨረሻ የተባረከ ሰው ነው::