ያዕቆብ
ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡27-28
እስራኤል
ህይወቱ ቅርፅ አልባ ስለሆነበት መንገዴ ከእግዚአብሄር ተሰውራለች ሲል እንመለከተዋለን፡፡ እስራኤል ህይወቱ የተበታተነ እና የተወሳሰበ
ስለሆነ ከዚህ ቅርፅ አልባ ህይወቱ ሊወጣ እንደማይችል አስቧል፡፡ እስራኤል ጥያቄው ውስብስብ በመሆኑ ሊፈታ እንደማይችል ተስፋ ቆርጧል፡፡
እስራኤል በህይወቱ ካሉ መልሶች ይልቅ ጥያቄዎቹ በዝተዋል፡፡
አሁንም
እያንዳንዳችን አንዳንዴ ህይወታችን እንደተበታተነ ቅርፅ አልባ እንደሆነና የህይወታችንን መንገድ ማንበብ እንደማንችእል ይሰማናል፡፡
አንዳንዴ የህይወታችን ክር እንደተበተበና ውሉ እንደጠፋ እንደተወሳሰበ ይሰማናል፡፡
አንዳንዴ
የህይወታችንን መንገድ ጫፉ እንደማይያዝ መጀመሪያውና መጨረሻው እንደማይታወቅ ይሆናል፡፡ የህይወታችንን እንቆቅልሽ መጀመሪያውንና
መጨረሻ ማገናኘት ያቅተናል፡፡
ይህ
ስሜት መርገም አይደለም፡፡ ይህ ስሜት ለእርዳታ እግዚአብሄርን እንድንፈልግ ትሁት የሚያደርግን ተፈጥሮአዊ ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት
ህይወታችንን በራሳችን እንደማንወጣው የሚያስታውሰን ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት ህይወታችን በእግዚአብሄር እንጂ በእኛ እንዳልተያዝ
የሚያስታውስን ስሜት ነው፡፡
የሕያዋን
ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት። መጽሐፈ ኢዮብ 12፡10
ትንፋሽህንና
መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም። ትንቢተ ዳንኤል 5፡23
ህይወታችንን
ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ማወቅ የለብንም፡፡ የምናውቃቸው ነገሮች አሉ የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሁሉንም ካወቅን እግዚአብሄር
እንጂ ሰው ልንሆን አንችልም፡፡ ሁሉንም ነገር ካወቅን በእግዚአብሄር ላይ መታመን አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም ነገር ማድረግ ከቻልን
የእግዚአብሄር እርዳታ አያስፈልግም፡፡
ምሥጢሩ
ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ኦሪት
ዘዳግም 29፡29
ሁሉን
በሚያውቅ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ያለብን እኛ እውቀት ሁሉ ስለሌለን ነው፡፡
የእግዚአብሄር
አምላካዊ መልስ ግን እንዲህ ይላል፡፡
እግዚአብሔር
የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡27-28
አንተ
አላወቅክም ማለት እግዚአብሄር አላወቀም ማለት አይደለም፡፡ አንተ የህይወትህ ንድፍ ዲዛይን የለህም ማለት እርሱ የለውም ማለት አይደለም፡፡
አንተ
የሚያስፈልግህ አንድ ነገር በምታውቅው እርምጃ እየወሰድክ በማታውቅው በሚያውቀውና ማስተዋሉ በማይመረመረው እግዚአብሄር ላይ መደገፍ
ነው፡፡ እንደ እርሱ እንድትበረታ ፣ እንደ እርሱ እንድታስተውል ፣ እንደ እርሱ እንድታውቅና እንደ እርሱ እንድትራመድ የሚያስፈልግህ
እርሱን በመተማመን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔርን
በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ
ኢሳይያስ 40፡31
እግዚአብሄር
እንዲህ ይላል፡፡
እኔ
አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና። ትንቢተ ኢሳይያስ 41፡13
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ራእይ #እይታ #መጠበት #መተማመን #እምነት #ያድሳሉ #ይወጣሉ #አይደክሙም #አይታክቱም #እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment