የህይወት ከፍተኛው የእርካታ ደረጃ
ሰው በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል በእግዚአብሔር ክብር ተፈጥሯል::
እንደ ዝና ገንዘብ ስልጣን ያሉ ተራ ነገሮች በራሳቸው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል በእግዚአብሔር ክብር ለተፈጠረው ሰው እውነተኛና ዘላቂ የእርካታ ስሜት ሊሰውን አይችሉም::
እንደ ዝና ገንዘብ ስልጣን ያሉ ነገሮች ሰው የተፈጠረበት ሌሎችን በፍቅር የማገልገል አላማ ለማሳካት የሚጠቅሙ መሳሪያዎች እንጂ በራሳቸው የህይወት ግብ አይደሉም::
ሰው የሚረካው የተፈጠረበትን የእግዚአብሄር አላማ ሲፈፅም ብቻ ነው::
ሰው የሚረካው የተፈጠረበትን ሌሎችን የማገልገል አላማ ከግብ ሲያደርስ ብቻ ነው ::
ሰው የሚረካው የተፈጠረበትን ሌሎችን በፍቅር የማገልገል አላማ ከግብ ሲያደርስ ብቻ ነው::
በሚያደርገው ነገር ሁሉ የተሳካለት ሰው የተፈጠረበት የእግዚአብሔርን አላማ ከሳተው ውጤቱ ሁሉም ነገር በዜሮ እንደሚባዛ ውጤቱ ዜሮ ነው::
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ቆሮንቶስ 13:1-3
ሰው ብዙ ዝና ገንዘብና ስልጣን ባይኖረውም ባለው ነገር ሁሉ ተጠቅሞ ሌላውን በፍቅር የሚያገለግል ሰው ከእርሱ በላይ የተሳካለት ሰው የሌለ የመጨረሻ የተባረከ ሰው ነው::
No comments:
Post a Comment