ህይወት ደስ ይላል፡፡ ህይወት ምን ያህል እንደሚጣፍጥ
የምናውቅው ልናጣው ስንል ነው፡፡ የህይወትን ክብር ይበልጥ የምንረዳው ከሞላ ጎደል አጥተነው ስናገኘው ነው፡፡
እግዚአብሄርን አሁን ካላመሰገነው መቼ እናመሰግነዋለን፡፡
ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል። ትንቢተ ኢሳይያስ 38፡18-19
አንድ
የእግዚአብሄር ሰው ሲናገር ለስኬት የሚያስፈልገው ቤት ብቻ ነው ይላል፡፡ ሲቀጥልም ለስኬት የሚያስፈልገው በስጋ ውስጥ መኖር ህያው
መሆን በህይወት መኖር ብቻ ነው፡፡ በህይወት የሚኖር ሰው ለስኬት ተስፋ አለው፡፡ ሰው በምድር ላይ ለስኬት ተስፋው የሚያከትመው
ከስጋ ከወጣ ብቻ ነው፡፡
አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፤ እኛ ሕያዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔርን እንባርካለን፡፡ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 115፡17-18
እግዚአብሄርን
ለማመስገን የሚያስፈልጉት ነገሮች ህያው መሆንና ህያው መሆን ብቻ ናቸው፡፡
ሃሌ
ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት። በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት። በመለከት
ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት። በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት። ድምፁ መልካም
በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት። እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ
ዳዊት 150፡1-6
እግዚአብሄርን
ለማመስገን ቀን መቅጠር አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን
ለማመስገን አንዱና ብቸኛው ቅድመ ሁኔታ ህያው መሆን በህይወት መኖር ነው፡፡ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ
ሉያ።
ነገ
ያንተ አይደለም፡፡ ዛሬን በህይወት የጠበቀህን ነገን ሊሰጥህ የሚችለውን እስትንፋስህን በእጁ የያዘውን እግዚአብሄርን ዛሬ አመስግን፡፡
አሁንም፦
ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ
የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ
ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ
ነው። የያዕቆብ መልእክት 4፡13-16
እንግዲህ
ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት። ዕብራውያን 13፡15
እስትንፋስ
ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 150፡6
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ
No comments:
Post a Comment