ለአንድ ነገር በጣም መጓጓት ለነገሩ ያለንን የእውቀት ማነስ ሊያሳይ ይችላል:: ለአንድ ነገር ያለን መጓጓት ግምት አሰጣጣችን መዛባቱን ከማሳየቱም
በላይ ይፍጠንም ይዘግይም እንደሚያሳዝነን እርግጥ ነው::
ከሰማይ በታች የሚያጓጓ ነገር የለም:: ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም:: አዲሱ ነገር ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው:: አዲሱ ነገር በፍቅር መኖር ነው:: አዲሱ ነገር ጌታንና ሰውን መውደድ ነው:: አዲሱ ነገር ጌታን መከተልና ማምለክ ነው:: 
ከጌታ ውጭ በጣም የሚያጓጓ ምንም ነገር የለም:: 
የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፤ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም። መጽሐፈ መክብብ 1:9
ሰው ሰውን የማገልገል ሀላፊነቱን ከተረዳው ስለ ስልጣን በጣም አይጓጓም:: 
ሰው ከዝነኝነት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሀላፊነት ከተረዳ የዝነኝነት ጥቅም ያን ያህል አያጓጓውም:: 
ሰው ሀይሉን በሚገባው ቦታ ላይ ብቻ የማዋል ከፍተኛ ሀላፊነት እንደተጫነበት የሚርዳ ሰው ሃይል እና ስልጣን  ለማግኘት
አይቸኩልም:: ስልጣን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የማገልገል ሃላፊነትም እንደሆነ የተረዳ
ሰው ስልጣንን ያን ያህል አይመኝም፡፡ 
የትዳርን ጥቅሙን ብቻ ሳይሆን ሃላፊነቱንም በሚገባ የተረዳ ሰው ተግዳሮቱን እንዳልተረዳው ሰው የብቸኝነት ጊዜውን ሳያጣጥል አክብሮ በሚገባ ይጠቀምበታል::
ከሚጠብቀው ነገር ውስጥ ጥቅም ብቻ የሚጠብቅና ሃላፊነቱን የማይረዳ ሰው በራሱ ይሰናከላል:: እያንዳንዱ ጥቅም ከሃላፊነት ጋር ይመጣል:: 
እያንዳንዱ አገር የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የማይረዳ ሰው አገር በመለውጥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከተግዳሮት ለማረፍ እጅግ ይጓጓል:: 
ለነገ ከመጠን በላይ የሚጓጓው እያንዳንዱ ቀን ከራሱ ጭንቀት ጋር አብሮ እንደሚመጣ
የማያውቅ ሰው ብቻ ነው:: 
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6:34፤ 
ከእግዚአብሄር ውጭ ሙሉ ትኩረታችንን ሊወስድ የሚገባው ምንም ነገር ሊኖር አይገባውም፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ በጣም የምንጓጓለት ነገር ከመጠን በላይ ስላጋነንነው
ያስቀይመናል፡፡  
ለእግዚአብሄር ብቻ መስጠት ያለብንን ትኩረት ለሌላ ለምንም ነገር በመስጠት እግዚአብሄርን አንስቀናው ::
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa 
ለተጨማሪ
ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ
#ጌታ #ዘላለማዊ #አዲስ #ልብ #ሰማይ #ዘላለም #ጌታ #ከፀሐይበታች #ያልፋሉ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:
Post a Comment