Popular Posts

Monday, October 23, 2017

ህይወትን ፍፁም የሚያደርጉ አምስቱ የእግዚአብሄር አቅርቦቶች

በህይወት ለማግኘት የምንፈልገውና እንዲሆንልን የምንጥራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ህይወት በራሱ ፍፁም አይደለም ጉድለት አለው፡፡ ህይወት በራሱ ፍፁም አይደለም፡፡ ህይወትን ምንም ሳይጎድለው ፍፁም የሚያደርገው የእግዚአብሄር አሰራር ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። 2ኛ ዜና 16፡9
ህይወትን ፍፁም የሚያደርገው አምስቱ የእግዚአብሄር አሰራሮችን እንመልከት
1.      ስንደክም የሚያበረታን የእግዚአብሄር ሃይል
ሰው በሃይሉ አይበረታም፡፡ ሰው ይደክማል፡፡ ሰው በራሱ መሄድ የሚችለው ትንሽ ነው፡፡ ሰው በራሱ ሃይል ብቻ ከታመነ እግዚአብሄር በህይወቱ ያቀደውን ከፍ ያለ ሃሳብ መፈፀም ይሳነዋል፡፡ ሰው በእግዘአብሄር ሃይል ላይ ከተደገፈ ግን የእግዚአብሄርን ሃሳብ በህይወቱ አገልግሎ ማለፍ ይችላል፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9
2.     ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርግ የእግዚአብሄር ሞገስ
ሰው በተፈጥሮው ሰውን ለመውደድ ብዙ መመዘኛዎች አሉት፡፡ ሰው ግን ካለምክኒያት እንዲወደን የሚያደርግ የእግዚአብሄር አሰራር ነው፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያየው ቦታ እንድንደርስ ሞገስን ይሰጠናል፡፡ ሰዎች ፊታችንን ሲቀበሉና ሃሳባችንን ሲሰሙና ሲቀበሉ ስናይ የእግዚአብሄርን ድንቅ አሰራር እንመለከትበታለን፡፡
እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ። ኢሳይያስ 55፡5
በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤ ሮሜ 1፡5
ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡12
3.     አስተዋይ የሚያደርግ የእግዚአብሄር ጥበብ
የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን ፈፅመን እግዚአብሄርን በምድር ላይ እንድናከብረው እግዚአብሄር ብርሃንን ይሰጠናል፡፡ እግዚአብሄር ከአስተማሪዎቻችን ይልቅ ጥበበኛ ያደርገናል፡፡ የምናልፈው ከማይመስለን ከባድ ፈተና ሊታደገን እግዚአብሄር መረዳትን በመስጠት መውጫውን ያዘጋጃልናል፡፡ አስበን የማናውቅውን ጥልቀ ነገር መረዳትን ይሰጠናል፡፡ በጥናትና በአእምሮ እውቀት የማይመጣ መገለጥ በህይወታችን ሲመጣ እግዚአብሄር በህይወታችን ሊሰራ ላለው ተልእኮ አስፈላጊ ስለሆነ በቀላሉ ለመረዳት የማይቻለውን የመንፈስን ነገር መረዳትን እናገኛለን፡፡
እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው። የሰሎሞንም ጥበብ በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ጥበብና ከግብጽ ጥበብ ሁሉ በለጠ። 1ኛ ነገሥት 4፡29-30
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡5
4.     የእግዚአብሄር አቅርቦት

እግዚአብሄር ወደጠራን ጥሪ መግባት እንድንችል ይኖረናለ ብለን የማንገምተውን የገንዘብ አቅርቦት እግዚአብሄር ወደእኛ ሲያመጣ የእግዚአብሄርን አሰራር እናይበታለን፡፡
በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡8-9
5.     ከሃዘን በላይ የሚያደርገን ሰላምና ደስታ

በምድር ላይ የሚያሳዝኑ ብዙ ነገሮች ይገጥሙናል፡፡ ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር እያለ ከሃዘን በላይ እንድንኖር የሚደርገን የእግዚአብሄር ስጦታ ደስታ ነው፡፡ ሊሰብረን የመጣው ሃዘን እንደፈሳሽ ውሃ ያልፋል፡፡ ሊያስቆመን የመጣው ሃዘን በልባችን ባለው ደስታ ይዋጣል፡፡ ልባችን ሊሰብር የመጣው ሃዘን አቅም ያጣል፡፡
እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። ዮሃንስ 16፡22
በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡8
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል  #በረከት #ስኬት #ጥበብ #ማስተዋል #ሞገስ #አቅርቦት #ሃይል #ፀጋ #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment