Popular Posts

Thursday, October 12, 2017

እግዚአብሔር አዋቂ ነውና

አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3
እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው ነገር ብዙ ነገር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ከሰው ኩራትን አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ሰው በእርሱ አሰራር እንዲታመን ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሄር በፍትህ ምድርን እያስተዳደር እንዳይደለ ያክል ሰው እንዲናገር አይፈልግም፡፡ የምድር ነገር ከእግዚአብሄር ቁጥጥር ውጭ እንደወጣ አድርጎ ሰው እንዲናገር እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ሚክያስ 6፡8
ሰው ቢያንስ ምድርን እያስተዳደር ያለው እግዚአብሄር አዋቂ ነው ብሎ ነገሮችን በእግዚአብሄር ካልተወ ነገሮች ትክክል አይሆኑም፡፡  እኔ ሁሉን አላውቅም እግዚአብሄር ግን ሁሉን ያውቃል ብሎ በእግዚአብሄር ካልተደገፈ ምንም ቢወጣና ቢወርድ ሰው አይሳካለትም፡፡
የእግዚአብሄርን ክንድ በህይወትዋ ያየችው ሃና ትመክራለች፡፡ እግዚአብሄር በፍትህ ምድርን ያስተዳደራል፡፡ እግዚአብሄር ስራውን ይመዝናል፡፡ እግዚአብሄር የተጎዳን እንዴት እንደሚክስ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር የደከመን እንዴት እንደሚግደግፍ ያውቃል እግዚአብሄር ያጣን እንዴት እንደሚሞላ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር የተዋረደን አንዴት እንደሚያነሳ ያውቃል፡፡ በዚህ የተጎዳውን በዚያ እንዴት እንደሚክሰው እግዚአብሄር ያውቃል፡፡
ሰው ሁሉን የሚያይ ምድርን በፍትህ የሚያስተዳደር እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ እንዲቆጣ እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ነው የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። የሚለው፡፡ ያዕቆብ 1፡20 ሰው እግዚአብሄር እንደሌለ አድርጎ የህይወትን አቅጣጫ ሁሉ ሊጣጠር ከሞከረ በከንቱ ይደክማል፡፡ መዝሙር 127፡1
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። 1 ሳሙኤል 23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አዋቂ ####ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment