ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም ፣ ለምጻም ቀርቦ :- ጌታ ሆይ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና :- እወዳለሁ ንፃ አለው። ማቴዎስ 8፡1-3
ኢየሱስ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ ላለው ሰው የመለሰው መልስ እወዳለሁ የሚል ነው፡፡ ኢየሱስ ሰዎችንም መፈወስ ይወዳል፡፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምናውቀው በኢየሱስ ነው፡፡ የእግዚአብሔርንም ፍላጎት የምናየው ኢየሱስን በማየት ነው፡፡ እግዚአብሄርን የተረከልን ኢየሱስ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምናውቀው የኢየሱስን የምድር አገልግሎት በማየት ነው፡፡
መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው። ዮሃንስ 1፡18
ኢየሱስ በምድር ላይ በመጣ ጊዜምን ያደረገው ፈውስን ነው፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የታመሙትንና የተጠቁትን ይፈውስ የነበረው በታላቅ ቅናት ነበር፡፡ እግዚአብሄርም ለፈውስ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ሰጥቶ ነበር ወደ ምድር የላከው፡፡
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ዮሃንስ 10፡38
ፈውስ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡ ምንም ነገር የእግዚአብሄር ፈቃድ ባይሆን ፈውስ ግን የእግዚአብሄር ፈቃድ እንደሆነ እግዚአብሄር በሰዎች ነፃ መውጣትና መፈወስ እንደሚደሰት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ የኢየሱስንም የምድር አገልግሎት ስንመለከት እግዚአብሄር ለሰው ልጆች ፈውስና አርነት ያለውን ታላቅ ቅናት እናያለን፡፡
ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም ፣ ለምጻም ቀርቦ :- ጌታ ሆይ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና :- እወዳለሁ ንፃ አለው። ማቴዎስ 8፡1-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #እግዚአብሄር #አርነት #ነፃነት #ፈውስ #እምነት #ቁስል #ህመም #ደዌ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #በመገረፉ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment