አምላክ ያለው ሰው ጥቅሙ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር እረኛ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይመራል ፣ ያበረታል ያፅናናል፡፡ የእግዚአብሔር እረኝነት የሚገለጥባቸው ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን እንመልከት
1. እግዚአብሔር ይመራል
እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ህዝብ ዋነኛው ጥቅም በእግዚአብሔር ማስተዋል መጠቀም ነው፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋል አይመረመርም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፡፡ ይህ ሁሉን የሚያውቅ እግዚአብሔር መንጋ ከመሆን የተሻለ ምን ነገር አስተማማኝ ነገር ይኖራል፡፡ እግዚአብሔር ይመራናል፡፡ እግዚአብሔር ባለንበት ደረጃ ወርዶ ይናገረናል፡፡ እግዚአብሔር መረዳት በምንችልበት መጠን እና ቋንቋ ሃሳቡን ይገልጥልናል፡፡ እግዚአብሔር ከተናገረ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር እንደተረዳን እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ ይናገራል፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። መዝሙር 23፡1-3
2. እግዚአብሔር ያበረታል
እግዚአብሔር ትክክለኛውን አቅጣጫ ማሳየት ብቻ ሳይሆን በዚያ መንገድ እንድንሔድ ሃይልን ይሰጠናል፡፡ እግዚአብሔር ያበረታል፡፡ እግዚአብሔር ይደግፋል፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ኢሳያስ 40፡28-29
3. እግዚአብሔር ያፅናናል
እግዚአብሔር ልባችንን ያፅናናል፡፡ በምድር ላይ እኛን ለማሳዘን የሚመጡ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ከሁሉም በላይ እንድንምኖትር እግዚአብሔር ያፅናናል እግዚአብሔር ልባችን በደስታ ይደግፋል፡፡ ከሁኔታ ጋር ያልተያያዘ ደስታን ይሰጠናል፡፡ ከሁኔታዎች ባላይ እንድንኖር ልባችንን ያፅናናል፡፡
የርህራሔ አባት የመፅናናት ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፡፡ 1ኛቆሮንቶስ 1፥3
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ያበረታል #ያፅናናል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment