Popular Posts

Follow by Email

Monday, October 9, 2017

ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ

ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። መዝሙር 72፥18
እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው፡፡ እኛ በደከመንና ጊዜ እኛ ባቃተን ጊዜ እግዚአብሔር ተአምራትን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር የእኛን እርዳታ ሳይፈልግ ብቻውን ድንቅን ነገር ያደርጋል፡፡
እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ መዝሙር 1364
እግዚአብሔር ከሰው ችሎታ በላይ የሆኑትን ነገሮች በማድረግ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔርን እግዚአብሔር የሚያሰኘው ሃይሉ ስለማይወሰን ሁሉን ቻይ አምላከ ስለሆነ ነው፡፡
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፦ ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ጭፍራ እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል አለው። 1ኛ ሳሙኤል 14፡6
እግዚአብሔር በኃይሉ ከሰው ችሎታ በላይ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋልና በእግዚአብሔር እንታመን እግዚአብሔርን እናመስግን፡፡
እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤ ኢዮብ 36፡22
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #ተአምር #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የእግዚአብሄርችሎታ #እግዚአብሄርንሃያል #ራስንመግዛት #ልብ

No comments:

Post a Comment