ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ያዕቆብ 4፡8
እግዚአብሄር ሲጠራንና የተስፋ ቃል ሲገባልን ሁለት ሃሳቦች በልባችን ይነሳሉ፡፡
አንደኛው እግዚአብሄርን ለማገልገል እድሉን አገኘሁ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ የሚል ሃሳብ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ህዝብ ለማገልገል እግዚአብሄር ታማኝ አደርጎ ስለቆጠረን ደስ ይለናል፡፡ ያለንን ለእግዚአብሄር ህዝብ ማካፈል እንደ እድል እንቆጥረዋለን፡፡ የእግዚአብሄር መጠቀሚያ መሆንንና እግዚአብሄርን ማገልገልን እንደ ትልቅ መብት እናየዋለን፡፡ ሰማይና ምድር የሰራው እግዚአብሄር ሊጠቀምብን
ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ስለወደደ ልባችን በደስታ ይሞቃል፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡12
እግዚአብሄር ሲጠራን በልባችን የሚነሳው ሌላኛው ሃሳብ ደግሞ በቃ አሁን እጠቀማለሁ የሚል ነው፡፡ በጥሪያችን ስም ዝነኛ መሆን ፣ በጥሪያችን ተጠቅመን እግዚአብሄ የሰጠንን ሃይልን ለፈለግነው ነገር ማዋል ፣ ተሰሚነታችንን ተጠቅመን የግል ጥቅማችንን ማሳደድ ፣ እግዚአብሄር ለአገልግሎት የሰጠንን ተቀባይነት ለራሳችን ጥቅም ማዋል ፣ ባለን ጥሪ ተጠቅመን ሀብታም መሆንና የአግልግሎታችንን ክብር ወደ እኛ ማዞር ሃሳብ ይነሳል፡፡
እግዚአብሄር ታዲያ እንዲህ ይላል ሁለት ሃሳብ ያለችሁ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ጠራን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የሚለቀን ልባችንን ስናጠራ ብቻ ነው፡፡
ልባችን ሲጠራ እግዚአብሄርን የምናገለግለው እግዚአብሄር ብቻ ስለሆነ ብቻ ስለሆነ ይሆናል፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው የእግዚአብሄርን ህዝብ ለመጥቀም ብቻ ሲይሆናል፡፡ የእግዚአብሄርን ቤት የምንሰራው ለራሳችን ቤትን ለመስራት አይሆንም፡፡ የእግዚአብሄን ህዝብ የምናገለግለው እግዚአብሄር ወደአየላቸው ተራ እንዲደርሱ በቅንነት ለመርዳት እንጂ ኑሮዋችንን ለመስራት አይሆንም፡፡ ልባችንን ስናጠራ እግዚአብሄር ወዳየልን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንለቀቃለን፡፡
ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ያዕቆብ 4፡8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ሃሳብ #መነሻሃሳብ #ልብ #ንፁህ #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment