Popular Posts

Thursday, October 3, 2024

ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ክፍል 3

 


እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2 


አንደ ክርስትያን የመጀመሪያው ጥሪያችን ጸሎት ነው። ለክርስትያን ለመንግስት መጸለይ በምንም መልኩ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አማራጭ አይደለም።  


የነገስታት አና የመኳንንት የፖለቲካ አቋም እንድንጸልይላቸው እንጂ እንዳንጸልይላቸው ሊያደርገን አይገባም ።  


ክርስትያኖችም ብንሆን የመቃወምም ሆነ የመደገፍም የግል የፖለቲካ አቋም ሊኖረን ይችላል። አንድን የፖለቲካ አቋም መቃወምም መደገፍም ማንም የማይሰጠን ማንም የማይከለክለን ከእግዚአብሄር የተቸረን የህሊና ነጻነታችን ነው።  


ብንደግፍም ብንቃወምም የፖለቲካ አቋማችን ለመንግስታት ግን ከቀዳሚው ጥሪያችን ክመጸለይ ግን ሊያግደን አይገባም።  


በስልጣን ላይ ያለውን የፖለቲካ ድርጅት ብንደግፍም ብንቃወምም ክርስትያናዊ ሃላፊነታችን ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ መጸለይ ነው። 


የትኛውም የፖለቲካ አቋማችን ላለመጸለይ ፈቃድ ሊሰጠን አይችልም።  


እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2 


#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት 


No comments:

Post a Comment