እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2
ሁላችንም በእግዚአብሄርን ፈቃድ መኖር እንፈልጋለን። ፍቃዱን አገልግለን ማለፍን ዘወትር እንራባለን እንጠማለን። በተለይ በእግዚብሄር ልብ ቅድሚያ የሚሰጠውን ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
በዚህ ረገድ የአዲስ ኪዳንን አንድ ሶስተኛውን የጻፈው ሀዋርያው ጳውሎስ ከሁሉም በፊት እመክራለሁ የሚለውን ጆሮ ሰጥቶ መስማት ብልህነት ነው፡፡
ሀዋርያው ጳውሎስ ከሁሉም በፊት የሚመክረው ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲጸለይ ነው።
እንደ ክርስትያን ከሁሉ በፊት እንድናደርግ የተመከርነው ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንድንጸልይ ነው።
ክርስትያን ለሀገርና ለህዝብ የተለያዩ ሃላፊነቶች አሉበት። የትኛውም ሀላፊነት ግን ጸሎትን ሊተካው ፈጽሞ አይችልም። ክርስትያን ለሀገርና ለህዝብ ያሉበት የተለያዩ ሃላፊነቶች ከመጸለይ ሃላፊነቱ በፊት ቅድሚያ ሊሰጣችው ፈጽሞ አይችልም።
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት
No comments:
Post a Comment