እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃምምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደጢሞቴዎስ 2:1-2
በአለም ላይ ሰዎችን ወደ መልካምነት ወደ ፍቅርና ወደ ሰላም የሚመራ የእግዚአብሔር መንፈስ አለ። በአለምላይ እንዲሁ ሰዎችን ወደ ጥፋት እና ጉስቁልና የሚነዳ የሰይጣን ክፉ መንፈስ ደግሞ አለ።
በእግዚአብሔር ቃል ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንድንፀልይላቸው የተመከርነውበስልጣን ላይ ያሉት ነገስታቱ እና መኳንንቱ በክፉ መንፈስ ተታልለው ህዝቡን እንዳያጎሳቁሉት ነው።
ከፀለይንላቸው ክፋት ይጠበቃሉ። ካልፀለይንላቸው በክፋት አገዛዝ ስር በመውደቅ ፍትህ ያዛባሉ፣ የሚመሩትንህዝብ በቅንነት ከማገልገል ይልቅ በስግብግብነት ሰላም እና እረፍት ይነሱታል።
ምክሩን ተቀብለን ከፀለይንላቸው ግን እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን መኖርእንችላለን።
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃምምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደጢሞቴዎስ 2:1-2
#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት#መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት
No comments:
Post a Comment