የአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊነት ምርጫ የአሜሪካዊያንንም ይሁን ይነስም ይብዛም በአጠቃላይ የአለምን ህዝብ ትኩረት የሳበ ርእስ ነው።
እንደ ክርስትያን በፖለቲካ ምርጫ መሳተፍ ምንም የማይወጣበት ትክክል ነገር ቢሆንም በሪፐብሊካንም ይሁን በዲሞክራት ላይ ያን ያህን ልባችንን መጣል እና ተስፋ ማድረግ እንደማይገባ ማስታወስ አለብን።
ፖለቲከኞች በፖለቲካ ፖሊሲ ወይም መመሪያቸው የሚለያዩ ቢሆኑም ሪፐብሊካንም ይሁን ዲሞክራት ቢያሸንፍ እንደው ያን ያህል ስር ነቀል ልዩነት የሚያመጣ ነገር ያመጣል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።
እንደ ክርስትያን በምርጫ ካርዳችን ከምናመጣው ልዩነት በላይ ማንም ይሁን ማን ለተመርጠው እና በስልጣን ላይ ላለው መንግስት እለት ተእለት ለነገስታት እና ለመኳንንት መጸለይ ይበልጥ በዘላቂነት ልዩነት ያመጣል።
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡1-2
እኛ ራሳችን ፖለቲከኞች ብንሆን እንኳን በምርጫ ቅስቀሳም ቢሆን በምርጫ ካርዳችን ከምናመጣው ልዩነት ይልቅ በጸሎታችን የምናመጣው ልዩነት እጅግ ይበልጣል። ሪፕብሊካን ይሁን ዲሞክራት ከሁሉም በላይ የእናንተን ልመናና ጸሎት ምልጃ ይፈልጋል።
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ምርጫ #ጸሎት #ምልጃ #ምስጋና #ልመና #ክርስትያን #ፖለቲካ
No comments:
Post a Comment