Popular Posts

Saturday, October 5, 2024

ኢሬቻ እና ክርስትና

 

ኢሬቻ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብሄራዊ ክልላዊ መንግስቱ እንደ ብሄራዊ በአል ሲከበር ቆይቶዋል። በዚህ ጽሁፍ ኢሬቻ ባህል ነው ወይስ ሃይማኖት የሚለው ትንተና ውስጥ መግባት አልፈልግም። እሬቻ ባህል ወይስ ሃይማኖት በሚል ርእስ   ያቀረብኩትን መልክታዬን ሊንኩን ከዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ ትቼዋለሁ። 

ለአንዳንዶች በተለይ የዋቄፈና እምነትን ለሚከተሉ ሃይማኖት ብቻ እንጂ ሌላ ምንም ነገር ሊሆን አይችልም። ለሌሎች  በተለይ የዋቄፈታ እምነት ውጭ ያለን ሃይማኖት ለሚከተሉ ባህል መሆኑ ይታወቃል። 

ባጠቃላይ ኢሬቻ ባህል ነው ወይስ ሃይማኖት ነው ለሚለው ጥያቄ ጥርት ያል መልስ ለመስጠት መሞከር ለውስብስብ ጥያቄ ቀላል መልስ ለመስጠት  እንደ መሞክር ነው።  

ምክኒያቱም በሰው ልጅ ህይወት ባህል እና ሃይማኖት የሚቀላቀልበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። ሃይማኖትን የሚጎዳ ባህል እስክሆነ ድረስ ምንም ችግር የለውም።  

በዚህ ጽሁፍ ግን እንደ ክርስትያን ባህልን እስክምን ድረስ ማክበር እንችላለን ለሚለው ጥያቄ በጥቂቱ ለመመለስ መሰረታዊ ነገሮችን ለመጻፍ እሞክራለሁ። 

ክርስትያን ባህልን እስክምን መከተል ይችላል የሚለውን ከመነጋገራችን በፊት ግን ክርስትያን ከዚህ ብታች የተዘረዘሩትን ማወቅ እና መቀበል አለበት በሚለው ሃሳብ አስቅድመን መስማማት አለብን።  

  1. አንድ አውነተኛ አምላክ ብቻ እንዳለ ማመን  

በሰዎች የሚመለኩ ብዙ አማልክት ቢኖሩም እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ ነው። ስለዚህ ወደ እውነተኛው አምላክ አንድ እንጂ የሚያደርስ ብዙ መንገድ የለም።  

እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የዮሐንስ ወንጌል 17፡3 

  1. እውነተኛው አምላክ የተገለጠው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ማወቅ 

እውነተኛው አምላክ የተገለጠው ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያት እዳችንን ሁሉ በከፈለው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ማወቅ አለብን። እውነተኛውን አምላክ የምንገናኘው ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያት እዳችንን ሁሉ በከፈለው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ማወቅ። 

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡20 

አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡5 

 

  1. በአለም ላይ ሁለት አይነት መናፍስት ብቻ እንዳሉ መረዳት  

ልዕለ ተፈጥሮአዊ ሁሉ ከእግዚአብሄር አይደለም። የእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ አለ የሰይጣን እርኩስ መንፈስ አለ። ከሁልቱ ውጭ ገለልተኛ መንፈስ የለም። የእግዚአብሄር ከሆን የሰይጣን አይደለም ከእግዚአብሄር ካልሆነ የሰይጣን ነው።  

እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡12 

በዚህ ረገድ ወደ ክርስቶስ የማያሳይ መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሄር አይልም። ሠው ትኩረቱን ከክርስቶስ ላይ አንስቶ ወደ ሌላ ወደ ምንም ነገር ላይ እንዲያተኩር የሚያደርግ ማንኛውም መንፈስ ከእግዚአብሄር አይደለም።  

  1. የእግዚአብሄር እና የሰይጣን መንፈስ የሚለየው በስራው ነው። 

የአንድ አገር ባህልም ቢሆን ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር ከተጋጨ ባህሉን እንጥለዋለን እንጂ ለጊዜያዊ ባህል ብለን በእግዚአብሄር ቃል ላይ አናምጽም። ቅድሚያ የምንሰጠው የእግዚአብሄርን ቃል እንጂ ባህልን አይደለም። 

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10።10  

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

ለተጨማሪ ፅሁፎች ኢሬቻ ባህል ወይስ ሃይማኖት? 

https://www.facebook.com/notes/787041595414553/ 

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos 

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መንፈስቅዱስ #ፈትኑ #ባህል #ሃይማኖት #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #እርኩስመንፈስ #ሰይጣን #ኢሬቻ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ኦሮሞ #ዋቄፈታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

 


No comments:

Post a Comment