ክርስቶስ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ እና እንደሞተ ብናምን እንዲሁም ሞትንም ድል አድርጎ በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ ብንመሰክር ከጨለማ ሥልጣን በመዳን ወደ እግዚአብሔር የፍቅሩ ልጅ መንግሥት እንፈልሳለን።
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፥13-14
ክርስቶስ ኢየሱስን ታችን አድርገን ከመቀበላችን በፊት ሁላችንም በሰይጣን መንግስት ግዛት ስር ነበርን። ኢየሱስን በተቀበልንበት ቅጽበት ከጨለማው ስልጣን አምልጠን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተዘዋውረናል።
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፥1-3
ክርስቶስን ሳንቀበል በጨለማው መንግስት ውስጥ እየኖሩ ቀኑ በመለወጡ ብቻ እውነተኛ አዲስ አመት ይሆንልናል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው። አዲሱን አመት እውነተኛ አዲስ አመት የሚያደርገው በክርስቶስ በመሆን ወደ እግዚአብሔር የፍቅር መንግስት መፍለስ ብቻ ነው።
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት
No comments:
Post a Comment