Popular Posts

Thursday, September 12, 2024

መስከረም አንድን ከጷጉሜ አምስት የሚለየው


ህይወት በፍጹም ከባድ ሸክም መሆን የለበትም። 

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። የማቴዎስ ወንጌል 11፥28-30 

ህይወትን ታዲያ መልካም የሚያደርገው ወደ ክርስቶስ መምጣታችን ነው። ክርስቶስ ከሌለበት መስከረም 1 ይልቅ ክርስቶስ ያለበት ጷጉሜ 5 ይሻላል የሚባልው ለዚያ ነው።

ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል። መጽሐፈ ምሳሌ 17፥1

ካለ ክርስቶስ ከምንኖረው መስከረም አንድ ይልቅ በክርስቶስ የተገለጠውን የእግዚአብሄርን ፍቅር ተቀብለን የምንኖርበት ጷጉሜ 5 ይሻላል።

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፥36

ክርስቶስ በህይወታችን ካለ የህይወት ከፍታው እና ዝቅታው ሁሉ ይጣፍጣል። ክርስቶስን ካልተከተልን ግን መስከረም አንድ ትርጉም የለሽ የከባድ ሸክም ሕይወት ይሆናል።

ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። መዝሙረ ዳዊት 84፥10

ቀኑን ወሩን እና አመቱን የሚያቀለው የሚያደርገው እና የሚጠቅመው ብቸኛው ነገር በክርስቶስ መሆን ብቻ ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፥15 

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


No comments:

Post a Comment