Popular Posts

Thursday, September 5, 2024

መልካም አዲስ ፍጥረት

 

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥17
መልካም አዲስ አመት
አዲሱ አመት 2017 አመተ ምህረት ሊገባ ጥቂት ቀናቶች ቀርተዋል፤  
አዲስ አመት መልካም ቢሆንም እንኳን ካለ አዲስ ፍጥረትነት መልካምነቱ ለምንም አይጠቅምም። 
በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፥15 
ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ እና አዲስ ፍጥረት ካልሆነ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይም ሆን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 3፥3
ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ እና በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ካልሆነ በቀር አዲሱ አመት እውነተኛ አዲስ አመት ሊሆንለት በፍጹም አይችልም።
አዲሱ አመት እውነተኛ አዲስ አመት እንዲሆንልን ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የሞተልንን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል አዲስ ፍጥረት እንሁን።
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥21
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


No comments:

Post a Comment