Popular Posts

Thursday, September 19, 2024

ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ?

 

እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? ኦሪት ዘፍጥረት 3:11
ክርስቶስን ስንከተል ራቁታችንን እንደሆንን ፥ ለእግዚኣአብሄር መኖር እንደማንችል ፥ የሚጎድለን ነገር እንዳለ ፥ እግዚአብሄር እንዳልተደሰተብን ፥ ከእግዚአብሄር ደረጃ እንደወድቅን የሚከሰን ከሳሽ ዲያቢሎስ በዙሪያችን ይዞራል። እንደማንበቃ ሊያሳምነን የማይፈነቅልው ድንጋይ የለም።
ጠላታችንን አምነን ራሳችንን መኮነን ከጀመርን ጠላት የመስረቅ ፥ የማረድ እና የማጥፋት አላማውን ያሳካል።
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
እግዚአብሄር ስለእኛ የሚለው ላይ ብቻ ማተኮር ትተን በራሳችን ማስተዋል ስንደገፍ በሆነው ባልሆነው ራሳችንን አላግባብ በመኮነን ከእርምጃችን እንዘገያልን።
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3፥5
የሰይጣን ስልጣን እንደሆን በክርስቶስ የመስቀል ስራ ሙሉ ለሙሉ ተሽሮዋል።
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
ሰይጣን ለጊዜው ያለው ብቸኛ መሳሪያ ወንድሞችን በሆነው ባልሆነው መክሰስ እና የሚታለሉለትን ሽባ ማድረግ ነው።
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና። የዮሐንስ ራእይ 12፥10
የሰይጣንን ክስ ካልሰማነው ብቻ እግዚአብሄር በምድር ያዘጋጀልንን መልካሙን ስራ ሰርተን በምድር ክርስቶስን እናከብራልን። 
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
#እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት #ሀበሻ #ዕራቁት


No comments:

Post a Comment