Popular Posts

Saturday, September 7, 2024

መልካም አዲስ ልብ

 

ለህይወት መለወጥ የልብ መለወጥ ወሳኝ ነው። ካለልብ መለወጥ የሚደረግ ማንኛውም ወግ የሃይማኖት መልክ እንጂ እውነተኛ መንፈሳዊነት ሊሆን አይችልም።
ሰው ክርስቶስን ስለሃጢያቱ እንደሞተ ሲቀበል አዲስ ልብን እና አዲስ መንፈስን ያገኛል።
ዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። ትንቢተ ሕዝቅኤል 36፥26-27
በእግዚአብሄር መንፈስ ልባችን ካልተለወጠ በስተቀር በራሳችን እውቀትና ሃይል እግዚአብሄር አምላክን ማምለክ እና ማስደሰት ዘበት ነው።
ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። ወደ ዕብራውያን 8፥10
ምንም ዘመኑ ቢለውጥ በአሮጌ ማንነት አዲስ አመት ይሆንልኛል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥17
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


No comments:

Post a Comment