Popular Posts

Thursday, September 19, 2024

ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ?

 

እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? ኦሪት ዘፍጥረት 3:11
ክርስቶስን ስንከተል ራቁታችንን እንደሆንን ፥ ለእግዚኣአብሄር መኖር እንደማንችል ፥ የሚጎድለን ነገር እንዳለ ፥ እግዚአብሄር እንዳልተደሰተብን ፥ ከእግዚአብሄር ደረጃ እንደወድቅን የሚከሰን ከሳሽ ዲያቢሎስ በዙሪያችን ይዞራል። እንደማንበቃ ሊያሳምነን የማይፈነቅልው ድንጋይ የለም።
ጠላታችንን አምነን ራሳችንን መኮነን ከጀመርን ጠላት የመስረቅ ፥ የማረድ እና የማጥፋት አላማውን ያሳካል።
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
እግዚአብሄር ስለእኛ የሚለው ላይ ብቻ ማተኮር ትተን በራሳችን ማስተዋል ስንደገፍ በሆነው ባልሆነው ራሳችንን አላግባብ በመኮነን ከእርምጃችን እንዘገያልን።
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3፥5
የሰይጣን ስልጣን እንደሆን በክርስቶስ የመስቀል ስራ ሙሉ ለሙሉ ተሽሮዋል።
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
ሰይጣን ለጊዜው ያለው ብቸኛ መሳሪያ ወንድሞችን በሆነው ባልሆነው መክሰስ እና የሚታለሉለትን ሽባ ማድረግ ነው።
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና። የዮሐንስ ራእይ 12፥10
የሰይጣንን ክስ ካልሰማነው ብቻ እግዚአብሄር በምድር ያዘጋጀልንን መልካሙን ስራ ሰርተን በምድር ክርስቶስን እናከብራልን። 
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
#እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት #ሀበሻ #ዕራቁት


Thursday, September 12, 2024

መስከረም አንድን ከጷጉሜ አምስት የሚለየው


ህይወት በፍጹም ከባድ ሸክም መሆን የለበትም። 

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። የማቴዎስ ወንጌል 11፥28-30 

ህይወትን ታዲያ መልካም የሚያደርገው ወደ ክርስቶስ መምጣታችን ነው። ክርስቶስ ከሌለበት መስከረም 1 ይልቅ ክርስቶስ ያለበት ጷጉሜ 5 ይሻላል የሚባልው ለዚያ ነው።

ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል። መጽሐፈ ምሳሌ 17፥1

ካለ ክርስቶስ ከምንኖረው መስከረም አንድ ይልቅ በክርስቶስ የተገለጠውን የእግዚአብሄርን ፍቅር ተቀብለን የምንኖርበት ጷጉሜ 5 ይሻላል።

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፥36

ክርስቶስ በህይወታችን ካለ የህይወት ከፍታው እና ዝቅታው ሁሉ ይጣፍጣል። ክርስቶስን ካልተከተልን ግን መስከረም አንድ ትርጉም የለሽ የከባድ ሸክም ሕይወት ይሆናል።

ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። መዝሙረ ዳዊት 84፥10

ቀኑን ወሩን እና አመቱን የሚያቀለው የሚያደርገው እና የሚጠቅመው ብቸኛው ነገር በክርስቶስ መሆን ብቻ ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፥15 

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


Wednesday, September 11, 2024

መልካም አዲስ ዘመን

በአጠቃላይ ዘመኑ ክፉ እንደሆን መጽሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ካለ ጌታ ኢየሱስ አዳኝነት ክፉው ዘመን በራሱ አዲስ ይሆናል ብለን ከጠበቅን እንሳሳታለን። ጌታ በህይወታችሁ ሳይኖር ህይወታችሁ አዲስ ይሆናል የሚላችሁ ካለ ያሳስታችሁዋል እንጂ አይጠቅማችሁም። 
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥15-16
አዲሱን አመት በእውነት አዲስ የሚያደርገው ስለሃጢያታችን የሞተልንን ክርስቶስን ተቀብልን በአዲሱ የክርስቶስ ጥበብ ስንመላለስ ብቻ ነው። 
አለም በክፉ ተይዞዋል።  
ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።1ኛ የዮሃንስ መልእክት 5፡19
በክፉ ከተያዘው የአለም አስራር ነጻ ወጥተን በነጻነት መኖር የምንችለው በአዲሱ የእግዚአብሄር ጥብብ ስንመላለስ ብቻ ነው። 
ክፉውን ዘመን የምንገዛው በእግዚአብሄር ጥበብ ብቻ ነው እንጂ ዘመኑ ስለትለወጠ ብቻ ክፉው ዘመን መልካም አይሆንም። ዘመኑን አዲስ የሚያደርገው የምንኖርበት ጥበባችን ክርስቶስ ሲሆን እና ይህን ክፉ ዘመን ስንለውጠው ብቻ ነው። 
መልካም አዲስ ዘመን 
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


 

Tuesday, September 10, 2024

መልካም አዲስ መንፈስ

 

ክርስቶስን እንደ አዳኝ እና ጌታ ስንቀበል የእግዚአብሄር መንፈስ በእኛ ውስጥ መኖር ይጀምራል። ታዲያ ህይወታችንን አዲስ የሚያደርገው በክርስቶስ የምንቀበለው አዲስ መንፈስ ነው።

የክርስቶስ መንፈስ በውስጡ የማይኖር ሰው የክርስቶስ ወገን አይደለም።

እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፥9

ከሃጢያታችን አጥቦ ለእግዚአብሄር ልጅነት ያበቃን የእግዚአብሄር መንፈስ ነው።

እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ወደ ቲቶ 3፥5

ህይወታችንን የሚያድሰው የእግዚአብሄር መንፈስ ብቻ ነው።

አዲስ አመትን መጠበቅ መልካም ነው እውነትኛ አዲስ አመት የሚገኘው በክርስቶስ ህይወት ብቻ ነው። አሁንም ክርስቶስን ብንቀበል አዲስ ቀን አዲስ ወር አዲስ አመት በአጠቃላይ አዲስ ህይወት ይሆንልናል።

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት


Monday, September 9, 2024

መልካም አዲስ ህይወት

 


ስለ ሃጢያታችን በመስቀል ላይ የሞተውን ኢየሱስን ስንቀበል እግዚአብሄር ይቀበለናል ከሞት ወደ ህይወት እንሸጋግራልን የዘላለም ህይወት እናገኛለን። በልጁ ካላመንን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእኛ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አናይም።
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፥36
ክርስቶስን ካልተቀበልን ልጁ ኢየሱስ በሕይወታችን ስለሌለ ከእግዚአብሄር ርቀን ከእግዚአብሄር ህይወት እንጠፋልን። አዲሱን አመት አዲስ የሚያደርገው በክርስቶስ የተቀበልነው አዲስ ህይወት እንጂ ያው የተለመደው የወር መለዋወጥ አይደለም።
እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፥11-12
እንዲያው በነጻ የተሰጠንን የዘላለም ህይወት ስጦታ በልጁ በኢየሱስ ስንቀበል ብቻ በልጁ አዲስ ህይወትን እንቀበላለን።
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


Saturday, September 7, 2024

መልካም አዲስ ልብ

 

ለህይወት መለወጥ የልብ መለወጥ ወሳኝ ነው። ካለልብ መለወጥ የሚደረግ ማንኛውም ወግ የሃይማኖት መልክ እንጂ እውነተኛ መንፈሳዊነት ሊሆን አይችልም።
ሰው ክርስቶስን ስለሃጢያቱ እንደሞተ ሲቀበል አዲስ ልብን እና አዲስ መንፈስን ያገኛል።
ዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። ትንቢተ ሕዝቅኤል 36፥26-27
በእግዚአብሄር መንፈስ ልባችን ካልተለወጠ በስተቀር በራሳችን እውቀትና ሃይል እግዚአብሄር አምላክን ማምለክ እና ማስደሰት ዘበት ነው።
ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። ወደ ዕብራውያን 8፥10
ምንም ዘመኑ ቢለውጥ በአሮጌ ማንነት አዲስ አመት ይሆንልኛል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥17
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


መልካም አዲስ ቤተሰብ


አዲሱን አመት በእውነት አዲስ የሚያደርገው በአዲሱ የእግዚአብሔር በተሰብ ውስጥ መሆናችን ነው። ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ አዳኝ ካልተቀበልን በስተቀር የእግዚአብሔር ልጆች መሆን በፍጹም አንችልም።
እውነት ነው ሰይጣን የፈጠርው አንድም ሰው የለም። ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር ፍጥረት ነው። ሁሉም ግን የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።
በሃጢያት ውድቀት ምክኒያት ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ክብር ጎድለዋል። በሃጢያት ውድቀት ምክኒያት ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ለዘላለም ተለያይቶዋል። ስለዚህ ክርስቶስን የተቀበለ ሰው ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር ፍጥረት ስለሆነ ብቻ  ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይሆንም። 
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። የዮሐንስ ወንጌል 1፥12-13
የእግዚአብሔር ልጅነት ክርስቶስን ለተቀበሉ ሰዎች ብቻ የተሰጠ ስልጣን እንጂ ለሁሉም አይደለም። 
ክርስቶስ ስለ መዳናችን የሃጢያታችን እዳ ሁሉ ከፍሎዋል፤ አሁንም ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፋችን ብንመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልባችን ብናምን ከመቅጽብት እንድናለን።
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።ወደ ሮሜ ሰዎች 10፥9-10
ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የሞተልንን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር በቤተሰብ ውስጥ እንግባ።
መልካም አዲስ ቤተሰብ መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


 

Friday, September 6, 2024

መልካም አዲስ መንግስት


ክርስቶስ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ እና እንደሞተ ብናምን እንዲሁም ሞትንም ድል አድርጎ በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ ብንመሰክር ከጨለማ ሥልጣን በመዳን ወደ እግዚአብሔር የፍቅሩ ልጅ መንግሥት እንፈልሳለን።

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፥13-14

ክርስቶስ ኢየሱስን ታችን አድርገን ከመቀበላችን በፊት ሁላችንም በሰይጣን መንግስት ግዛት ስር ነበርን። ኢየሱስን በተቀበልንበት ቅጽበት ከጨለማው ስልጣን አምልጠን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተዘዋውረናል።

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፥1-3

ክርስቶስን ሳንቀበል በጨለማው መንግስት ውስጥ እየኖሩ ቀኑ በመለወጡ ብቻ እውነተኛ አዲስ አመት ይሆንልናል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው። አዲሱን አመት እውነተኛ አዲስ አመት የሚያደርገው በክርስቶስ በመሆን ወደ እግዚአብሔር የፍቅር መንግስት መፍለስ ብቻ ነው።

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት 


 

Thursday, September 5, 2024

መልካም አዲስ ፍጥረት

 

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥17
መልካም አዲስ አመት
አዲሱ አመት 2017 አመተ ምህረት ሊገባ ጥቂት ቀናቶች ቀርተዋል፤  
አዲስ አመት መልካም ቢሆንም እንኳን ካለ አዲስ ፍጥረትነት መልካምነቱ ለምንም አይጠቅምም። 
በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፥15 
ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ እና አዲስ ፍጥረት ካልሆነ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይም ሆን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 3፥3
ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ እና በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ካልሆነ በቀር አዲሱ አመት እውነተኛ አዲስ አመት ሊሆንለት በፍጹም አይችልም።
አዲሱ አመት እውነተኛ አዲስ አመት እንዲሆንልን ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የሞተልንን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል አዲስ ፍጥረት እንሁን።
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥21
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
 #ሀበሻ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #አበሻ #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አዲስአመት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፀሎት