እንደ መፅሃፍ ቅዱስ እውነተኛው አዲስ አመት
መቼ ነው ብለን መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡
እውነተኛው አዲስ አመት መቼ እንደሆነ በሚገባ
ካልተረዳን አዲስ አመት ባልሆነ ቀን ላይ በከንቱ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ አዲስ አመትን በትክክለ ካልተረዳነው አሮጌ በሆነ ነገር
ላይ አለአግባብ አተኩረን አዲሱን እናጣዋለን፡፡ አዲስ አመትን በትክክል ካልተረዳነው ጉልበታችንን በማይጠቅም ነገር ላይ እናባክናለን፡፡
ሰው አዲስ አመት የሚሆንለት የእግዚአብሔር ቃል
ሰምቶ በቃሉ ነፃ የወጣ እለት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለ የአዲስ አመት ተስፋ ከንቱ ተስፋ ነው፡፡
እስራኤላዊያን የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ይሁንላችሁ
የተባሉት የእግዚአብሔር ትእዛዝ ሰምተው ከግብፅ ነፃ የወጡበትን ቀን ነው፡፡
ሰው የሚታደሰው እና የሚለወጠው የእግዚአብሔርን
አላማ በህይወቱ ያደረገ እለት ነው፡፡ ሰው አዲስ አመት የሚሆንለት እግዚአብሔር የታዘዘ እለት ነው፡፡
እግዚአብሔርም
በግብፅ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ። በዚያም ቀን እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብፅ ምድር አወጣ። ኦሪት ዘጸአት 12፡1-2፣
50-51
ሰው እግዚአብሔር ያለውን የታዘዘበት ጳጉሜ
5 አዱስ አመት ነው ሰው ደግሞ እግዚአብሔርን ሰምቶ በቃሉ ነፃ ያለወጣበት መስከረም አንድ አዲስ አመት አይደለም፡፡
በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአዲስ
አመት ቀን ማድረግ እንችላለን፡፡ በምናደርገው ነገር መስከረም አንድን ጨምሮ እያንዳንዱን ቀን የአሮጌ አመት ቀን ልናደርገው እንችላለን፡፡
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት
#ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ
No comments:
Post a Comment