Popular Posts

Friday, September 8, 2023

እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 3

 

ሁላችንም ከአዲስ አመት ውስጥ ብዙ ነገር እንመኛለን እንጠብቃለን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰው ከአዲስ አመት የሚጠብቃቸው ነገሮች የሚገኙት በአዲስ አመት ውስጥ ሳይሆን በአዲስ ሰው ውስጥ ነው፡፡

ሰው በአዲስ አመት ውስጥ የሚጠብቀው የብልፅግና ዘመን የሚመጣው በንስሃ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ እንጂ ዘመን ሲለዋወጥ በምኞት ብቻ አይደለም፡፡

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20

በህይወታችሁ ከሚገጥመን ማንኛውም የመልካም ምኞት መግለጫ ሁሉ በላይ የመፅናናት ዘመን የሚያመጣልን ከሃጢያታችን ተመልሰን በክርስቶስ ኢየሱስ ማመናችን ብሎም ክርስቶስን መከተላችን ነው፡፡

ክርስቶስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለው እና ከሞት የተነሳው በእርሱ የሚያምኑት የመፅናናት ዘመን እንዲመጣላቸው እና እንዲባረኩ ነው፡፡

ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-26

የሰላም እና የብልፅግና ዘመን የሚመጣው ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከተለያየው ከእግዚአብሔር ጋር በንስሃ ታርቆ ሰላም ሲሆን ብቻ እንጂ በአዲስ አመት ውስጥ አይደለም፡፡

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት #ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ


No comments:

Post a Comment