Popular Posts

Wednesday, September 6, 2023

እውነተኛው አዲስ አመት

 

ሁልጊዜ አዲስ አመት ሲመጣ ደስ ይለናል፡፡ አዲስ አመት ተስፋን ይዞ ይመጣል፡፡ ዘመን ሲለወጥ ያለፈውን እንድንረሳ ያደርገና ብለን ስለምናስብ ለአዲስ አመት እንጓጓለን፡፡ በአዲስ አመት ያለፈውን ደስ የማያሰኘውን ነገር ሁሉ እንዳለፍነው ስለሚሰማን በተስፋ እንጠብቀዋለን፡፡

ይህን ሁሉ መጠበቅ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ የምንጠብቀው በአዲስ አመት ብቻ ከሆነ ትክክል አይሆንም፡፡

እንደ እውነቱ ቀን እድልን የሚሰጥ እንጂ በራሱ እድል አይደለም፡፡ ቀን በሚሰጠው እድል የሚጠቀም ሰው አለ ቀን የሚሰጠውን እድል የሚያባክን ሰው ደግሞ አለ፡፡ በቀን ውስጥ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ቀን ያው ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ሮብ ፣ሃሙስ ፣ አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ነው፡፡

ቀኑን ልዩ የሚያደርገው በቀኑ ውስጥ የምናደርገው ነገር እንጂ ቀኑ ራሱ አይደለም፡፡ ቀኑ ውስጥ የምናደርገው ነገር ከተለየ የምናገኘው ውጤት ይለያል፡፡ በቀን ውስጥ የምናደርገው ነገር ግን ካልተለየ እና ተመሳሳይ ከሆነ የምናገኘው ውጤት ተመሳሳይ ይሆናል፡፡

ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡5

በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአዲስ አመት ቀን ማድረግ እንችላለን፡፡ በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአሮጌ አመት ቀን ልናደርገው እንችላለን፡፡

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት #ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል


No comments:

Post a Comment