Popular Posts

Saturday, September 2, 2023

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል ክፍል 4

 

እውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል . . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 534-5

እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በመልኩ እና በአምሳሉ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው መኖሪያ የሚሆን ስጋን አስቀድሞ አዘጋጀለት፡፡ ሰው ምንም እንኳን በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል ቢፈጠርም በምድር ላይ ለመኖር እና የእግዚአብሔርን አላማ ለማስፈፀም ከምድር ጋር የሚስማማ መኖሪያ ቤት ስጋ አስፈልጎት ነበር፡፡ በምድር ላይ ለመኖር ስጋ ግዴታ ነው፡፡

ኢየሱስ ከሃጢያታችን ሊቤዠን በመስቀል ላይ ሲሰቀል ዋጋ የከፈለው ለነፍሳችን ብቻ አልነበረም፡፡ የነፍሳችን መዳን ወሳኝ ነገር ነበር፡፡ ካለነፍስ መዳን ማንኛውም የስጋ ፈውስ ትርጉም የለውም፡፡ ነፍሳችን  በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ ተቤዠቶ ስጋችን ካልተፈወሰ ለመንግስተ ሰማያት ህይወት ብቁ እንሆናለን፡፡ የመንግስተ ሰማያት ህይወት መግባት የሚጠይቀው የነፍስ መዳንን ብቻ ነው፡፡

እውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል . . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡4-5

ነገር ግን በምድር ላይ ቆይተን የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ግን የስጋችን ፈውስ ወሳኝ ነው፡፡ ካለስጋ ፈውስ በነፍስ መዳን ብቻ እግዚአብሔር እንዳየልን በምድር ላይ መቆየት እና የእግዚአብሔርን የመንግስት ስራ መስራት አንችልም፡፡

ኢየሰስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለው ስለፈውሳችን የተገረፈው ለዚህ ነው፡፡

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1 የጴጥሮስ መልእክት 224

የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን ክፍል እንደሆነ ሁሉ የስጋ ፈውስ የመቤዠታችን አንዱ አካል ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም #ደዌ #ወንጌል #ፈውስ #ጤንነት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #በመገረፉ #ቁስል #ተፈወሳችሁ


No comments:

Post a Comment