Popular Posts

Friday, December 29, 2023

Faith is a Lifestyle

 


Faith is a Lifestyle 

Faith is not a one-time activity; it is a way of life. 

If one wants to succeed in life, faith must be their way of living. Understanding faith is necessary. 

One also needs to put effort into achieving it. In order to keep our faith healthy and safe, we must tend to its seeds. It must be gradually grown. 

So every day practice is required. 


Some individuals try to force faith to work once in a while and then forget about it. They attempt to live their lives as they like and only turn to their faith when they feel it is necessary. That isn't how faith functions. Everyday faith practice is required. Our lives must regularly remain in the context of the word that inspires faith. 

 

Samson didn't mean business. He wanted to unleash his power one day when he realised his enemies were encircling him. But he was unable to. It had been a long time since he had left the atmosphere. He was unable to control God's strength as he would have desired. Because he was not living the lifestyle, he was unaware that the power of God had long since abandoned him. He paid the ultimate price for neglecting this constant practice.

Faith is a lifestyle. It is only when we practice it regularly that it is strengthened. And it will be ready when we need it the most. 


Abiy Wakuma Dinsa 

ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9

 


Friday, October 13, 2023

የዝምታ ጥበ

 


የተፈጠርነው ለእግዚአብሔር ክብር ነው፡፡ የተፈጠርነው እግዚአብሔርን እንድንከተል ነው፡፡ የተፈጠርነው እርሱን እንድናመልክ እና እንድናገለግለው ነው፡፡

ታዲያ እንዴት እንደምናገለግለው የሚወስነው እርሱ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ የእኛ ድርሻ እርሱን መስማት እና በቅርበት መከተል ብቻ ነው፡፡ እርሱን ለማስደሰት እርሱን በየእለቱ እና በየሰአቱ መስማት እና መከተል አለብን፡፡

እርሱ ሲነሳ አብረን ልንነሳ ፣ እርሱ ሲራመድ አብረን ልንራመድ ፣ እርሱ ዝም ሲል አብረን ዝም ልንል እንዲሁም እርሱ ሲናገር አብረን ልንናገር ለእርሱ ክብር እንኖራለን፡፡

ለራሳችን ምኞት እና ፍላጎት ሞተናል፡፡ ለራሳችን አላማ እና ግብ ሞተናል፡፡ ለራሳችን ጥበብ እና ማስተዋል ሞተናል፡፡

ህያው የሆንነው ለእርሱ ምኞት እና ፍላጎት ብቻ ነው፡፡ የእርሱ አላማን ለማሳካት በህይት እንኖራለን፡፡ በእርሱ ጥበብና መስተዋል ብቻ ላይ እንደገፋለን፡፡

እርሱ አላማውን የሚያስብበት የእርሱ አእምሮ ነን፡፡ እርሱ ፍላጎቱን የሚፈፅምበት የእርሱ እጅ ነን፡፡ እርሱ የሚጓዝበት የእርሱ እግር ነን፡፡ እርሱ የሚናገርነት የእርሱ አፍ ነን፡፡

እርሱ የሚኖርብን እንደመሆናችን መጠን እርሱ ሲነሳ እንነሳለን፡፡ እርሱ ሲራመድ አብረንው እንራመዳለን፡፡ እርሱ ሲያርፍ ደግሞ አብረነው እናርፋለን፡፡

እርሱ ሲራመድ አብረን መራመድ እንደሚያስፈልገን ሁሉ እርሱ ሲያርፍ አብረን ማረፍ ግዴታችን ነው፡፡ እርሱ ሲናገር አብረን ለመናገር እንደምንወስነው ሁሉ እርሱ ዝም ሲል ባይገባንም አብረነው ዝም ለማለት መጨከን አለብን፡፡ እርሱ ሲራመድ በደስታ አብረነው እንደምንራመድ ሁሉ እርሱ ቁጭ ሲል አብረነው መቀመጥን መለማመድ አለብን፡፡

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ወደ ገላትያ ሰዎች 2፡20

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #ክርስቶስ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ                                     


Wednesday, October 11, 2023

የፓለቲከኝነት ሙያ

ፖለቲካ የአገር አስተዳደር ሙያ ነው፡፡ ማንኛውም ሙያ በመልካም ሰው እጅ በአግባብ እንደሚያዝ ሁሉ ፖለቲካም ለህዝብ ጥቅም በአግባብ ሊያዝ ይችላል፡፡ ፖለቲከኝነት ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ሙያ ደግሞ አላግባብ እንደሚያዝ ሁሉ ፖለቲካም አላግባብ ሊያዝ ይችላል፡፡

ብዙ ጊዜ ፖለቲካን ከክፋት ፣ ከውሸት ፣ ከማጭበርበር እና ከራስ ወዳድነት ጋር ብቻ እናያይዘዋለን፡፡ እውነት ነው ሁሉም አይሁኑ እንጂ ክፉ ፣ ውሸታም ፣ አጭበርባሪ ፣ ራስ ወዳድ ፖለቲከኞች አሉ፡፡

ነገር ግን ደግሞ ህዝብን በቅንነት የሚያገለግሉ መልካም ፣ እውነተኛ ፣ የሚያገለግሉትን ህዝብ የሚወዱ ብዙ ፖለቲከኞች አሉ፡፡

ፖለቲከኝነት ስለአንድ አገር ወይም ህዝብ ባለ ራእይነት ይጠይቃል፡፡ አንድ ፖለቲከኛ ህዝብ እንዴት በሰላም እንደሚተዳደር እና ወደ ስኬት እና ብልፅግና እንደሚደርስ የሚታየው ሰው መሆን አለበት፡፡ አንድ አገር ወይም ህዝብ እንዴት እንደሚተዳደር ፣ በሰላም እንደሚኖር ፣ እንደሚሰራ እና እንደሚያድግ ማቀድ ፣ መመሪያ ማውጣት ብሎም ህዝብን ማስተማር እና ማንቀሳቀስ የአንድ ፖለቲከኛ ሃላፊነት እና ሸክም ነው፡፡

እግዚአብሔር ህዝብን ስለሚወድ መልካም ፍትሃዊ ፖለቲከኞችእን ይሰጣል፡፡ ሰይጣን ደግሞ አለማው መስረቅ ማደር እና ማጥፋት ስለሆነ ፖለቲከኛ ሰዎችን ስግብግብ ክፉ ለህዝብ ሰላምም ይሁን ብልፅግና ግድ የሌላቸው ሊያደርጋቸው ይጥራል፡፡

ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መጽሐፈ መክብብ 10፡16-17

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፖለቲካ #አስተዳደር #መመሪያ #ወንጌል #ቅዱስመንፈስ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሀገር #ንጉስ #ክርስቶስ


 

Saturday, October 7, 2023

ባህልና ሃይማኖት

 

ባህል የአንድ የተወሰነ ህዝብ ወይም ማህበረሰብ ሀሳቦች፣ ልማዶች እና ማህበራዊ ባህሪ መገለጫ እንደሆነ ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ይናገራል።

ባህል በጣም ጠቃሚና እንደ ህብረተሰብ የህይወትን ተግዳሮት ተቋቁሞ ለማለፍ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ባህል እና ሃይማኖት ፈፅሞ የተለያዩ አይደሉም፡፡ ባህል ደግሞ ብዙውን ጊዜ ከሃይማኖት ጋር ይቀላቀላል፡፡ ባህል ከሃይማኖት ጋር ሲቀላቀል የባህሉ ባለቤት ህብረተሰብ ሃይማኖትን እንደባህል እንዲወሰድ እና ተቀባይነት እንዲኖረው ተፅእኖ ያደርጋል፡፡

በዚህ ተፅእኖ ውስጥ ወድቀን የትኛውም ባህል ከሃይማኖት ከበለጠንም ባህሉ ራሱ ሃይማኖት ሆኖብናል ማለት ነው፡፡ ተቀባይነት ያላቸው ባህሎች በሃይማኖት ተቀባይነት ያላቸው ባህሎች ብቻ ናቸው፡፡ በሃይማኖት ተቀባይነት የሌላቸው ባህሎች በሃይማኖተኛው ዘንድ ተቀባይነት ሊኖራቸው አይገባም፡፡

ክርስትና ከሃይማት ጋር የተገናኙትን ባህሎች አይቀበልም፡፡ ክርስትና የሚቀበላቸው እና የማይቀበላቸው ባህሎች አሉ፡፡ ክርስትና የሚቀበለው ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር የማይጋጨውን ባህል ብቻ ነው፡፡ ባህልን ለመቀበል እና ለመጣል ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር መሄዱ ወይም አለመሄዱን በመመልከት ነው፡፡

ከሃይማኖት ጋር የማይጋጩ ባህሎችን መከተል እንደ ህብረተሰብ ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ሰው ባህሉን መውደድ ምንም ችግር የለውም፡፡ ባህሉ ከባህልነት ድንበር አልፎ ሃይማኖት ውስጥ ከገባ ግን ተቀባይነት ያጣል፡፡

ለምሳሌ በክርስትና ስለባህል ብሎ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰውን ክርስቶስ ኢየሱስን የማያከብር መንፈስን መከተል አደገኛ ነው፡፡  ባህሉን ስለወደድን ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ መንፈስን ማክበር በእሳት እንደመጫወት አደገኛ ነገር ነው፡፡

ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ሌላን መንፈስ ወደ ማምለክ እና ወደ መከተል ከሚመራ ባህል ውጭ ያለው ማንኛውም ባህል ሁሉ መልካም ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ባህል #ሃይማኖት #መንፈስ #ወንጌል #ቅዱስመንፈስ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #ሰይጣን #ክርስቶስ



Thursday, October 5, 2023

ሁለቱ አይነት መንፈሶች

 

በአለም ላይ ብዙ የመንፈስ አሰራሮች ቢኖሩም ግን በአለም ላይ በዋነኝነት ሁለት አይነት መንፈሶች ብቻ ይገኛሉ፡፡ ሁለቱ አይነት መንፈሶች የእግዚአብሔር መንፈስ እና የሰይጣን መንፈስ ናቸው፡፡ ከሁለቱ መንፈሶች ውጭ ያለ ገለልተኛ መንፈስ የለም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ የሰይጣን መንፈስ ነው፡፡ የሰይጣን መንፈስ ከሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም፡፡

ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።1 የዮሐንስ መልእክት 4፡1

መንፈስ ወይም ከእግዚአብሔር ወይም ደግሞ ከሰይጣን ነው፡፡ ልእለ ተፈጥሮአዊ ብቻ ስለሆነ አንድን የመንፈስ አሰራር ከእግዚአብሔር ከመሰለን እንስታለን፡፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ያልሆነ አሰራር አለ፡፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ያልሆነው ሁሉ ከሰይጣን የሆነ አሰራር ነው፡፡ በልእል ተፈጥሮ ሃይል የሚሰራ ቅዱስ እና ክፉ መንፈስ አለ፡፡ ማንኛውም ድንቅ ታእምር በቅዱስ መንፈስ ካልተደረገ የተደረገው በሰይጣን መንፈስ ነው ማለት ነው፡፡

ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ። ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር።ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር። የሐዋርያት ሥራ 8፡9-11

በሽታንም ፈወሰ ፣ መስተፋቅር አሰራም ፣ የሰውን ሚስጥር ተናገረም ፣ ልጅ ትምህርት እንዲገባውም አስደረገ በእግዚአብሔር መንፈስ ካላደረገው ያደረገው በሰይጣን መንፈስ ነው ማለት ነው፡፡ የሚሰራው ታእምር በልእለ ተፈጥሮ ሃይል ስለሆነ ሊያስደንቅ ይችላል ነገር ግን ሰውየው ከእግዚአብሔር ነው ወይም የሚሰራው በእግዚአብሔር መንፈስ ሃይል ነው ማለት አይደለም፡፡

ጴጥሮስ ጠንቋዩ ስምኦን በሰይጣን አስራት ውስጥ እንደነበረ የሚናገረው ስለዚህ ነው ፡፡

እስራት   በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና፡፡ የሐዋርያት ሥራ 8፡23

እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤ የሐዋርያት ሥራ 8፡22

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #መንፈስ #ክፉመንፈስ #ወንጌል #ቅዱስመንፈስ #ጥንቆላ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #ሰይጣን #ክርስቶስ


Thursday, September 28, 2023

ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ ከአካልም ብልቶች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፤ ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን፥ ለጎደለው ብልት የሚበልጥ ክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው። 1ኛ ቆሮንጦስ 12:22-25

 ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ ከአካልም ብልቶችያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብርይጨመርላቸዋል፤ ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ብልቶች እርስበርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን፥ ለጎደለው ብልት የሚበልጥክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው። 1 ቆሮንጦስ 12:22-25

Monday, September 25, 2023

The Bottom Line

 

Our lives should be lived with the intent of fulfilling God's purpose for us, rather than simply existing. That is the final conclusion.

What you do after eating is more important than what you consume, in my opinion.

In comparison to the reason you drive, the car you drive doesn't really matter.

Driving the most expensive car in the world is vanity if you don't truly pursue God's purpose for your life.

To complete God's purpose in our lives, the purpose of our lives is by far more significant than what we wear.

Even if you are the most attractive person alive and fall short of God's plan for your life, you have failed.

If you are the strongest human being but have failed to use your influence to fulfil God’s purpose in your life, your strength is nothing.

If you are the most intelligent person on the planet, but you do not use your knowledge for God's purposes in your life, then your life has failed.

Man is created for God's purpose and for his glory. Every provision and opportunity is meant for the purpose of fulfilling God’s purpose for our lives. 

Abiy Wakuma Dinsa #purpose #success #prosperity #vanity #wisdom #might #riches #God #Jesus 

Thursday, September 21, 2023

የንጉሱ አስደናቂ ታሪክ

 


ከአሥራ ሁለት ወር በኋላ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ ይመላለስ ነበር። ንጉሡም፦ ይህች እኔ በጕልበቴ ብርታት ለግርማዬ ክብር የመንግሥት መኖሪያ እንድትሆን ያሠራኋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችምን? ብሎ ተናገረ። ቃሉም ገና በንጉሡ አፍ ሳለ ድምፅ ከሰማይ ወደቀና፦ ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ፦ መንግሥት ከአንተ ዘንድ አለፈች ተብሎ ለአንተ ተነግሮአል፤ ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፤ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው። በዚያም ሰዓት ነገሩ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ፤ ጠጕሩም እንደ ንስር፥ ጥፍሩም እንደ ወፎች እስኪረዝም ድረስ ከሰዎች ተለይቶ ተሰደደ፥ እንደ በሬም ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ። ዘመኑም ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዓይኔን ወደ ሰማይ አነሣሁ፥ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም ባረክሁ፥ ለዘላለምም የሚኖረውን አመሰገንሁ አከበርሁትም፤ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና፥ መንግሥቱም ለልጅ ልጅ ነውና። በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም። በዚያን ጊዜም አእምሮዬ ተመለሰልኝ፥ ለመንግሥቴም ክብር ግርማዬና ውበቴ ወደ እኔ ተመለሰ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቶቼም ፈለጉኝ፥ በመንግሥቴም ውስጥ ጸናሁ፥ ብዙም ክብር ተጨመረልኝ። አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፥ ታላቅም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ ነውና፥ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና። ትንቢተ ዳንኤል 4:29-37


Thursday, September 14, 2023

የእግዚአብሔር #ጸጋ ተገልጦአል

 

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ወደ ቲቶ 2፡11-13

ሰዎች ካሉበት ከማንኛውም ጥፋት የሚያድናቸው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጦዋል፡፡

የሰው ማንኛውም ችግር እና ጥፋት ምንጩ ሃጢያት ነው፡፡ ሃጢያት ሰውን ከእግዚአብሔር  ክብር አዋርዶ እንደሚጠፋ እንስሳት አስመስሎታል፡፡  

ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። መዝሙረ ዳዊት 49፡12

ሃጢያት ሰውን ሁሉ ያዋርዳል ያሳንሳል ያጎሳቁላል፡፡ በአጠቃላይ ሃጢያት ሰውን ባሪያ ያደርጋል፡፡

ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።የዮሐንስ ወንጌል 8፡34

ሰውን ከሃጢያት እስራት ነፃ ማውጣት የሚችል ጉልበት ያለው የእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፀጋ ጉልበት ሃጢያትን ያስክዳል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ሃያል የሆነውን አለማዊ ምኞትን ያስንቃል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ እግዚአብሔርን የመምሰል ሃይልን ይሰጣል፡፡ ፀጋ በፅድቅ እንድንኖር አቅም ይሰጠናል፡፡

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ወደ ቲቶ 2፡11-13

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃይል #ወንጌል #ፅድቅ #ሃጢያት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #አቅም #ጉልበት  


ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? ትንቢተ ኢሳይያስ 55:2

 


Sunday, September 10, 2023

እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 5

 

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 517

የሰውን ማንነቱን ፣ ተፈጥሮውን ፣ ባህሪውን ፣ ተስፋውን ፣ ግቡን የሚለውጠው እና የሚያድሰው አዲስ ፍጥረት መሆኑ ነው፡፡ ሰው አዲስ ፍጥረት ካልሆነ አዲስ ወር አዲስ አመት በመጣ ቁጥር አዲስ ነገር መጠበቅ ተመሳይ ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት እንደመጠበቅ ከንቱ ነው፡፡

አዲስ ዘመን እንዲሆን አዲስ ሰው ይጠይቃል፡፡ አዲስ ዘመን ቢመጣም ሰውየው አዲስ ካልሆነ ዋጋ የለውም፡፡

ኢየሱስ አዲስ ነገር በአዲስ መያዣ ውስጥ መቀመጥ እንዳለበት ከዚህ በታች ባሉት ጥቅሶች በማብራሪያ ያስተምራል፡፡ አዲስ አመት አዲስን ሰው ይጠይቃል፡፡ አዲስነት እንዲሰምር ሁለቱም አዲስ መሆን አለባቸው፡፡ አንዱ ብቻ አዲስ ሆኖ ሌላው አሮጌ ከሆነ አይሰራም፡፡

በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። የማርቆስ ወንጌል 2፡21-22

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት #ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ


Saturday, September 9, 2023

እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 4

 

አዲስ አመት በእውነት አዲስ አመት እንዲሆንልን መለወጥ እና አዲስ ሰው መሆን ያለብን እኛ ነን፡፡ እኛ ክርስቶስን በማመን አዲስፍጥረት ካልሆንን በስተቀር የትኛውም አዲስ አመት አሮጌ እንጂ አዲስ ሊሆንልን አይችልም፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡15

ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ አዲሱን ሰው ክርስቶስን እስካልለበሰ እና አሮጌውን ሰው እስካላስወገደ ድረስ አዲስ አመት በራሱ የሚያመጣለት ምንም አዲስ ነገር አይኖርም፡፡

ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡22-24

ሰው እውነተኛውን አዲስ አመትን የሚለማመደው ክርስቶስን የህይወቱ አዳኝና ጌታ ካደረገ ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት #ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ


Friday, September 8, 2023

እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 3

 

ሁላችንም ከአዲስ አመት ውስጥ ብዙ ነገር እንመኛለን እንጠብቃለን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰው ከአዲስ አመት የሚጠብቃቸው ነገሮች የሚገኙት በአዲስ አመት ውስጥ ሳይሆን በአዲስ ሰው ውስጥ ነው፡፡

ሰው በአዲስ አመት ውስጥ የሚጠብቀው የብልፅግና ዘመን የሚመጣው በንስሃ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ እንጂ ዘመን ሲለዋወጥ በምኞት ብቻ አይደለም፡፡

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20

በህይወታችሁ ከሚገጥመን ማንኛውም የመልካም ምኞት መግለጫ ሁሉ በላይ የመፅናናት ዘመን የሚያመጣልን ከሃጢያታችን ተመልሰን በክርስቶስ ኢየሱስ ማመናችን ብሎም ክርስቶስን መከተላችን ነው፡፡

ክርስቶስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለው እና ከሞት የተነሳው በእርሱ የሚያምኑት የመፅናናት ዘመን እንዲመጣላቸው እና እንዲባረኩ ነው፡፡

ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-26

የሰላም እና የብልፅግና ዘመን የሚመጣው ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከተለያየው ከእግዚአብሔር ጋር በንስሃ ታርቆ ሰላም ሲሆን ብቻ እንጂ በአዲስ አመት ውስጥ አይደለም፡፡

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት #ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ


Thursday, September 7, 2023

እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 2

 

እንደ መፅሃፍ ቅዱስ እውነተኛው አዲስ አመት መቼ ነው ብለን መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡

እውነተኛው አዲስ አመት መቼ እንደሆነ በሚገባ ካልተረዳን አዲስ አመት ባልሆነ ቀን ላይ በከንቱ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ አዲስ አመትን በትክክለ ካልተረዳነው አሮጌ በሆነ ነገር ላይ አለአግባብ አተኩረን አዲሱን እናጣዋለን፡፡ አዲስ አመትን በትክክል ካልተረዳነው ጉልበታችንን በማይጠቅም ነገር ላይ እናባክናለን፡፡

ሰው አዲስ አመት የሚሆንለት የእግዚአብሔር ቃል ሰምቶ በቃሉ ነፃ የወጣ እለት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለ የአዲስ አመት ተስፋ ከንቱ ተስፋ ነው፡፡

እስራኤላዊያን የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ይሁንላችሁ የተባሉት የእግዚአብሔር ትእዛዝ ሰምተው ከግብፅ ነፃ የወጡበትን ቀን ነው፡፡

ሰው የሚታደሰው እና የሚለወጠው የእግዚአብሔርን አላማ በህይወቱ ያደረገ እለት ነው፡፡ ሰው አዲስ አመት የሚሆንለት እግዚአብሔር የታዘዘ እለት ነው፡፡

እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ። በዚያም ቀን እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብፅ ምድር አወጣ። ኦሪት ዘጸአት 12፡1-2፣ 50-51

ሰው እግዚአብሔር ያለውን የታዘዘበት ጳጉሜ 5 አዱስ አመት ነው ሰው ደግሞ እግዚአብሔርን ሰምቶ በቃሉ ነፃ ያለወጣበት መስከረም አንድ አዲስ አመት አይደለም፡፡

በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአዲስ አመት ቀን ማድረግ እንችላለን፡፡ በምናደርገው ነገር መስከረም አንድን ጨምሮ እያንዳንዱን ቀን የአሮጌ አመት ቀን ልናደርገው እንችላለን፡፡

መልካም አዲስ አመት

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት #ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ