የተፈጠርነው ለእግዚአብሔር ክብር ነው፡፡ የተፈጠርነው
እግዚአብሔርን እንድንከተል ነው፡፡ የተፈጠርነው እርሱን እንድናመልክ እና እንድናገለግለው ነው፡፡
ታዲያ እንዴት እንደምናገለግለው የሚወስነው እርሱ
እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ የእኛ ድርሻ እርሱን መስማት እና በቅርበት መከተል ብቻ ነው፡፡ እርሱን ለማስደሰት እርሱን በየእለቱ እና
በየሰአቱ መስማት እና መከተል አለብን፡፡
እርሱ ሲነሳ አብረን ልንነሳ ፣ እርሱ ሲራመድ
አብረን ልንራመድ ፣ እርሱ ዝም ሲል አብረን ዝም ልንል እንዲሁም እርሱ ሲናገር አብረን ልንናገር ለእርሱ ክብር እንኖራለን፡፡
ለራሳችን ምኞት እና ፍላጎት ሞተናል፡፡ ለራሳችን
አላማ እና ግብ ሞተናል፡፡ ለራሳችን ጥበብ እና ማስተዋል ሞተናል፡፡
ህያው የሆንነው ለእርሱ ምኞት እና ፍላጎት ብቻ
ነው፡፡ የእርሱ አላማን ለማሳካት በህይት እንኖራለን፡፡ በእርሱ ጥበብና መስተዋል ብቻ ላይ እንደገፋለን፡፡
እርሱ አላማውን የሚያስብበት የእርሱ አእምሮ
ነን፡፡ እርሱ ፍላጎቱን የሚፈፅምበት የእርሱ እጅ ነን፡፡ እርሱ የሚጓዝበት የእርሱ እግር ነን፡፡ እርሱ የሚናገርነት የእርሱ አፍ
ነን፡፡
እርሱ የሚኖርብን እንደመሆናችን መጠን እርሱ
ሲነሳ እንነሳለን፡፡ እርሱ ሲራመድ አብረንው እንራመዳለን፡፡ እርሱ ሲያርፍ ደግሞ አብረነው እናርፋለን፡፡
እርሱ ሲራመድ አብረን መራመድ እንደሚያስፈልገን
ሁሉ እርሱ ሲያርፍ አብረን ማረፍ ግዴታችን ነው፡፡ እርሱ ሲናገር አብረን ለመናገር እንደምንወስነው ሁሉ እርሱ ዝም ሲል ባይገባንም
አብረነው ዝም ለማለት መጨከን አለብን፡፡ እርሱ ሲራመድ በደስታ አብረነው እንደምንራመድ ሁሉ እርሱ ቁጭ ሲል አብረነው መቀመጥን
መለማመድ አለብን፡፡
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ወደ ገላትያ ሰዎች 2፡20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት
#ልብ #ማመን
#ቃል #ክርስቶስ
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ማሰላሰል #ማድረግ
#መከተል #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment