Popular Posts

Thursday, October 5, 2023

ሁለቱ አይነት መንፈሶች

 

በአለም ላይ ብዙ የመንፈስ አሰራሮች ቢኖሩም ግን በአለም ላይ በዋነኝነት ሁለት አይነት መንፈሶች ብቻ ይገኛሉ፡፡ ሁለቱ አይነት መንፈሶች የእግዚአብሔር መንፈስ እና የሰይጣን መንፈስ ናቸው፡፡ ከሁለቱ መንፈሶች ውጭ ያለ ገለልተኛ መንፈስ የለም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ የሰይጣን መንፈስ ነው፡፡ የሰይጣን መንፈስ ከሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም፡፡

ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።1 የዮሐንስ መልእክት 4፡1

መንፈስ ወይም ከእግዚአብሔር ወይም ደግሞ ከሰይጣን ነው፡፡ ልእለ ተፈጥሮአዊ ብቻ ስለሆነ አንድን የመንፈስ አሰራር ከእግዚአብሔር ከመሰለን እንስታለን፡፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ያልሆነ አሰራር አለ፡፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ያልሆነው ሁሉ ከሰይጣን የሆነ አሰራር ነው፡፡ በልእል ተፈጥሮ ሃይል የሚሰራ ቅዱስ እና ክፉ መንፈስ አለ፡፡ ማንኛውም ድንቅ ታእምር በቅዱስ መንፈስ ካልተደረገ የተደረገው በሰይጣን መንፈስ ነው ማለት ነው፡፡

ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ። ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር።ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር። የሐዋርያት ሥራ 8፡9-11

በሽታንም ፈወሰ ፣ መስተፋቅር አሰራም ፣ የሰውን ሚስጥር ተናገረም ፣ ልጅ ትምህርት እንዲገባውም አስደረገ በእግዚአብሔር መንፈስ ካላደረገው ያደረገው በሰይጣን መንፈስ ነው ማለት ነው፡፡ የሚሰራው ታእምር በልእለ ተፈጥሮ ሃይል ስለሆነ ሊያስደንቅ ይችላል ነገር ግን ሰውየው ከእግዚአብሔር ነው ወይም የሚሰራው በእግዚአብሔር መንፈስ ሃይል ነው ማለት አይደለም፡፡

ጴጥሮስ ጠንቋዩ ስምኦን በሰይጣን አስራት ውስጥ እንደነበረ የሚናገረው ስለዚህ ነው ፡፡

እስራት   በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና፡፡ የሐዋርያት ሥራ 8፡23

እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤ የሐዋርያት ሥራ 8፡22

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #መንፈስ #ክፉመንፈስ #ወንጌል #ቅዱስመንፈስ #ጥንቆላ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #ሰይጣን #ክርስቶስ


No comments:

Post a Comment