Popular Posts

Saturday, October 7, 2023

ባህልና ሃይማኖት

 

ባህል የአንድ የተወሰነ ህዝብ ወይም ማህበረሰብ ሀሳቦች፣ ልማዶች እና ማህበራዊ ባህሪ መገለጫ እንደሆነ ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ይናገራል።

ባህል በጣም ጠቃሚና እንደ ህብረተሰብ የህይወትን ተግዳሮት ተቋቁሞ ለማለፍ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ባህል እና ሃይማኖት ፈፅሞ የተለያዩ አይደሉም፡፡ ባህል ደግሞ ብዙውን ጊዜ ከሃይማኖት ጋር ይቀላቀላል፡፡ ባህል ከሃይማኖት ጋር ሲቀላቀል የባህሉ ባለቤት ህብረተሰብ ሃይማኖትን እንደባህል እንዲወሰድ እና ተቀባይነት እንዲኖረው ተፅእኖ ያደርጋል፡፡

በዚህ ተፅእኖ ውስጥ ወድቀን የትኛውም ባህል ከሃይማኖት ከበለጠንም ባህሉ ራሱ ሃይማኖት ሆኖብናል ማለት ነው፡፡ ተቀባይነት ያላቸው ባህሎች በሃይማኖት ተቀባይነት ያላቸው ባህሎች ብቻ ናቸው፡፡ በሃይማኖት ተቀባይነት የሌላቸው ባህሎች በሃይማኖተኛው ዘንድ ተቀባይነት ሊኖራቸው አይገባም፡፡

ክርስትና ከሃይማት ጋር የተገናኙትን ባህሎች አይቀበልም፡፡ ክርስትና የሚቀበላቸው እና የማይቀበላቸው ባህሎች አሉ፡፡ ክርስትና የሚቀበለው ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር የማይጋጨውን ባህል ብቻ ነው፡፡ ባህልን ለመቀበል እና ለመጣል ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር መሄዱ ወይም አለመሄዱን በመመልከት ነው፡፡

ከሃይማኖት ጋር የማይጋጩ ባህሎችን መከተል እንደ ህብረተሰብ ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ሰው ባህሉን መውደድ ምንም ችግር የለውም፡፡ ባህሉ ከባህልነት ድንበር አልፎ ሃይማኖት ውስጥ ከገባ ግን ተቀባይነት ያጣል፡፡

ለምሳሌ በክርስትና ስለባህል ብሎ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰውን ክርስቶስ ኢየሱስን የማያከብር መንፈስን መከተል አደገኛ ነው፡፡  ባህሉን ስለወደድን ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ መንፈስን ማክበር በእሳት እንደመጫወት አደገኛ ነገር ነው፡፡

ከመፅሃፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ሌላን መንፈስ ወደ ማምለክ እና ወደ መከተል ከሚመራ ባህል ውጭ ያለው ማንኛውም ባህል ሁሉ መልካም ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ባህል #ሃይማኖት #መንፈስ #ወንጌል #ቅዱስመንፈስ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #ሰይጣን #ክርስቶስ



No comments:

Post a Comment