ፖለቲካ የአገር አስተዳደር ሙያ ነው፡፡ ማንኛውም
ሙያ በመልካም ሰው እጅ በአግባብ እንደሚያዝ ሁሉ ፖለቲካም ለህዝብ ጥቅም በአግባብ ሊያዝ ይችላል፡፡ ፖለቲከኝነት ብቻ ሳይሆን ማንኛውም
ሙያ ደግሞ አላግባብ እንደሚያዝ ሁሉ ፖለቲካም አላግባብ ሊያዝ ይችላል፡፡
ብዙ ጊዜ ፖለቲካን ከክፋት ፣ ከውሸት ፣ ከማጭበርበር
እና ከራስ ወዳድነት ጋር ብቻ እናያይዘዋለን፡፡ እውነት ነው ሁሉም አይሁኑ እንጂ ክፉ ፣ ውሸታም ፣ አጭበርባሪ ፣ ራስ ወዳድ ፖለቲከኞች
አሉ፡፡
ነገር ግን ደግሞ ህዝብን በቅንነት የሚያገለግሉ
መልካም ፣ እውነተኛ ፣ የሚያገለግሉትን ህዝብ የሚወዱ ብዙ ፖለቲከኞች አሉ፡፡
ፖለቲከኝነት ስለአንድ አገር ወይም ህዝብ ባለ
ራእይነት ይጠይቃል፡፡ አንድ ፖለቲከኛ ህዝብ እንዴት በሰላም እንደሚተዳደር እና ወደ ስኬት እና ብልፅግና እንደሚደርስ የሚታየው
ሰው መሆን አለበት፡፡ አንድ አገር ወይም ህዝብ እንዴት እንደሚተዳደር ፣ በሰላም እንደሚኖር ፣ እንደሚሰራ እና እንደሚያድግ ማቀድ
፣ መመሪያ ማውጣት ብሎም ህዝብን ማስተማር እና ማንቀሳቀስ የአንድ ፖለቲከኛ ሃላፊነት እና ሸክም ነው፡፡
እግዚአብሔር ህዝብን ስለሚወድ መልካም ፍትሃዊ
ፖለቲከኞችእን ይሰጣል፡፡ ሰይጣን ደግሞ አለማው መስረቅ ማደር እና ማጥፋት ስለሆነ ፖለቲከኛ ሰዎችን ስግብግብ ክፉ ለህዝብ ሰላምም
ይሁን ብልፅግና ግድ የሌላቸው ሊያደርጋቸው ይጥራል፡፡
ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መጽሐፈ መክብብ 10፡16-17
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ፖለቲካ
#አስተዳደር #መመሪያ
#ወንጌል #ቅዱስመንፈስ
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሀገር
#ንጉስ #ክርስቶስ
No comments:
Post a Comment