I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Saturday, February 29, 2020
Monday, February 17, 2020
Sunday, February 16, 2020
እውነትን ግዛ
እውነትን
ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡23
እውነት የእግዚአብሄር የጥንቱ የቀደመው ሃሳብ
ነው፡፡ እውነት የእግዚአብሄር ኦሪጅናል ሃሳብ ነው፡፡ እውነት የእግዚአብሄር የመጀመሪያው እቅድ ነው፡፡
ኢየሱስ ስለእግዚአብሄር የጥንቱ የመጀመሪያው ሃሳብ
ከጥንት ግን እንደዚህ አልነበረም በማለት ስለመጀመሪያው የእግዚአብሄር ሃሳብ ስለ ወሳኝነት እውነት ይናገራል፡፡ ስለምንም ነገር
ክርክርር ሲነሳ የጥንቱ የእግዚአብሄር ሃሳብ ከፍተኛው ባለስልጣን ነው፡፡ እውነት ለምንም ነገር መነሻ ማጣቀሻ ነው፡፡ የጥንቱ የእግዚአብሄር
ሃሳብ ለየትኛውም ትምህርት ማስተያያ ማጣቀሻ ነው፡፡
እርሱም፦
ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። የማቴዎስ ወንጌል 19፡8
ከምንም
ነገር በላይ እውነት ሃያል ነው፡፡ ጥበበኛ ሰው ማደረግ የሚችለው የተሻለ ነገር ከእውነት ጋር መወገን ብቻ ነው፡፡ ሰው ምንም ጠቢብ
ቢሆን ከእውንት ጋር ተጋፍጦ አይበረክትም፡፡ ሰው ምንም ሃያል ቢሆን ከእውነት ተቃራኒ ጎን ቆሞ አይሳካለትም፡፡ ሰው ምንም ምንም
ባለጠጋ ቢሆን እውነተን ተቃውሞ አይጸናም፡፡ ሰው ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም አይችልም፡፡
ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ
ሰዎች 13፡8
ሰው
ስለስኬቱ እግዚአብሄርን መፈለግ አለበት፡፡ ሰው ስለመከናወኑ የእግዚአብሄርን ሃሳብ መፈለግ እና ማግኘት አለበት፡፡ ሰው እንዲከናወን
የጥንቱን የእግዚአብሄርን ሃሳብ መፈለግ ግዴታ ነው፡፡ ሰው እውነትን መፈለግ አለበት፡፡ ሰው እውነትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን
ዋጋ ሁሉ መክፈል አለበት፡፡ ሰው እውነትን ለማግኘት እውነትን ለመኖርና በእውነት ለመፅናት ዋጋ መክፈል አለበት፡፡ ሰው ስለምንም
ነገር ዋጋ ባይከፍል ስለእውነት ዋጋ መክፈል አለበት፡፡ ስለእውነት የሚከፈለው ዋጋ ለምንም ከሚከፈለው ዋጋ ይሻላል፡፡
እውነት
እውነተኛ መዝገብ ነው፡፡ እውነት እውነተኛ ሃብት ነው፡፡ ሰው ያለውን ነገር ሁሉ እውነትን ለመግዛት ቢከፍል አይቆጭም፡፡
ደግሞ
መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና
ያን እርሻ ገዛ። የማቴዎስ ወንጌል 13፡44
ሃብት
የሚመስሉ ብዙ ሃብቶች አሉ፡፡ እውነት ግትን እውነተኛ ሃብት ነው፡፡ እውነት የማይጠፋ የማይለውጥ ዘላቂ ሃብት ነው፡፡
እውነትን
ለማግኘት የሚከፈለው ዋጋ ሁልጊዜ አመርቂ ውጤትን ያስገኛል፡፡ የእግዚአብሄርን እውነት ለማግኘት ኢንቨስት የምናደርገው ኢንቨስትመንት
ሁሉ አትራፊ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ እውነት ከለም መሬቶች ሁሉ ለም የሆነ ብዙ ፍሬን የሚያስገኝ ለም መሬት ነው፡፡
ዋጋዋም
እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት። የማቴዎስ ወንጌል 13፡46
እውነት
የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእውነት መገኛ እና ምንጭ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ ያለው እውነት ነው፡፡ እግዚአብሄር
በቃሉ ያላለው እውነት አይደለም፡፡
በእውነትህ
ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 17፡17
የቃልህ
መጀመሪያ እውነት ነው፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። መዝሙረ ዳዊት 119፡160
በህይወታችን
ማድር የምንችለው የተሻለ ነገር ስለሆነ የእግዚአብሄርን ቃል እውነት እንፈልግ እናግኝ እንለማመድ እንፅናበት፡፡
እውነትን
ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡23
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እውነት #ቃል #ውሸት #ሀሰት
#ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት
Saturday, February 15, 2020
በእምነት ባለ ጠጎች
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? የያዕቆብ መልእክት 2፥5
በእምነት ባለጠጋ መሆን ማለት
የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ይሰጠኛል ብሎ በእግዚአብሄር መሪነት ፣ ጥበቃና አቅርቦት መታመን ማለት ነው፡፡ በእምነት
ባለጠግነት ማለት እግዚአብሄርን በቃሉ በሙላት ማመን ማለት ነው፡፡ በእምነት ባለጠግነት ማለት በነገር ሁሉ እግዚአብሄርን ማለት
ነው፡፡
ለሰው አስተማማኝ ባልሆነው በኪሱ
ውስጥ ባለው ገንዘብ ባለጠጋ ከሚሆን ይልቅ በነገር ሁሉ ለዘላለም ባለጠጋ በሆነው በእግዚአብሄር ላይ መታመን ይሻለዋል፡፡ ሰው በጊዜያዊ
ገንዘብ ባለጠጋ ከሚሆን ይልቅ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ በሆነው በእግዚአብሄርን ላይ ባለው እምነት ባለጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ
ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ
ባለ ጠጋ ነው፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡12
ለሰው በሌላ ሰው ላይ ከሚታመን
ይልቅ በእግዚአብሄር ላይ ያለውን መታመን ቢያበዛ ያዋጣዋል፡፡
እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ትታመናለህ፤ ሰው
ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል ያቈስለውማል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ
እንዲሁ ነው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 18፥21
ለሰው በሁኔታዎች ባለጠጋ ከመሆን
እና በሁኔታዎች ላይ ከሚታመን ይልቅ በሁኔታዎች በማይለውጥ እርሱ ግን ሁኔታዎችን የሚለውጥ በእግዚአብሄር ላይ በመታመን ባለ ጠጋ
ቢሆን ይሻለዋል፡፡
ለሰው በገንዘብ ባለጠጋ ከመሆን
ይልቅ በእምነት ባለጠጋ መሆን ይሻላል፡፡ ተለዋዋጭ በሆነው በማያስተማምን በአለም ሃብት ባለጠጋ ከመሆን ይልቅ በእርሱ የሚያመነ
አያፍርም በተባለለት በእግዚአብሄር ላይ ባለ እምነት ባለጠጋ መሆን ያስተማምናል፡፡
መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ
አያፍርም ይላልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡11
ሰው ምንም ማድረግ በማይችለው
በምንም አይነት በማያስመካ በሰው ጥበብ ላይ ከሚታመን ይልቅ በእግዚአብሄር ላይ ባለ እምነት ባለጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ
የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ
ኤርምያስ 9፡23-24
ሰው በሚደክመውና በሚታክተው
በራሱ ሃይል ከሚተማመን ይልቅ በማይደክመውና በማይታክተው ሰውን በሚያበረታው በእግዚአብሄር ላይ ባለው እምነት ባለጠጋ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ
ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡30-31
ሰው ከምንም በላይ እንከን የሌለባትን የእግዚአብሄርን በረከት በሚያገኝበት በእምነት ባለጠጋ መሆን ይሻለዋል፡፡
የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም። መጽሐፈ ምሳሌ 10፡22
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Friday, February 14, 2020
ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡4-7
ፍቅር
ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡4-7
Thursday, February 13, 2020
በጋብቻ እመኑ
ስለጋብቻ በእግዚአብሔር እመኑ፡፡
ጋብቻ የእግዚአብሄር እንጂ የሰው ሃሳብ አይደለም፡፡
የጋብቻን ሃሳብ ያመነጨው ሰው አይደለም፡፡ የጋብቻን ሃሳብ ያመጣው ራሱ እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው አስቀድሞ
ጋብቻን አስቦ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው ስለዚህ ነው፡፡
እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ የማቴዎስ ወንጌል 19፡4
አስቦ አስቦ ማግባት አለብኝ ብሎ ከጊዜ በኋላ
የጋብቻን አሳብ ያመጣው ሰው አይደለም፡፡ የፈጠረው ሰው ሚስት ማግባት እንዳለበትና ሰው ብቻውን መኖሩ መልካም እንዳይደለ የተናገረው
እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡
ሰው የጋብቻን ሃሳብ ባላሰበበት ጊዜ ሰው ማግባት
እንዳለበት ያሰበው እና ያቀደው ሚስትም የፈጠረለት እግዚአብሄር ነው፡፡ ከሰው በላይ ለሰው ምን እንደሚያስፈልገው የሚያውቀው እግዚአብሄር
ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም በማለት ሰው ማግባት እንዳለበት ተናገረ፡፡
በእግዚአብሄር የሚያመን ሰው በጋብቻ ማመን አለበት፡፡
በጋብቻ ከማመን ውጭ መንም አማራጭ የለም፡፡ በጋብቻ ማመን መፅሃፍ ቅዱሳዊ እውነት ነው፡፡ ሰው በሌላ ነገር ሊሳሳት ይችላል ነገር
ግን በጋብቻ አምኖ አይሳሳትም፡፡
ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ጊዜ የጋብቻ
ቃልኪዳን እስከመጨረሻው እንደሆነ ሲያስተምር ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱም የጋብቻ ሥርዓት ይህ ከሆነማ መጋባት አይጠቅምም ወደሚል መደምደሚያ
ደረሱ፡፡ ኢየሱስ ግን ሰው ጃንደረባ ካልሆነ በስተቀር በጋብቻ ማመንና ራስን መስጠት እንጂ ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌለው አስተማራቸው፡፡
ደቀ መዛሙርቱም፦ የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም አሉት። እርሱ ግን፦ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ የማቴዎስ ወንጌል 19፡10-11
ጋብቻ የእግዚአብሄር ስርአት ነው፡፡ ጋብቻ የህይወት ሃላፊነት ነው፡፡ ጋብቻ የህይወት
የቤት ስራ ነው፡፡
ጋብቻ ይጠቅማል አይጠቅምም ከሚለው ባለፈ ልናልፍበት የሚገባ የህይወት ሃላፊነት
ነው፡፡
ጋብቻ በእግዚአብሄር ዘንድ የተከበረ ነው፡፡
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን
እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ወደ ዕብራውያን 13፡4
የጋብቻ ቃልኪዳን እግዚአብሄር ራሱ የሚካተትበት ክቡር ነገር ነው፡፡
እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት
ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው። ትንቢተ ሚልክያስ 2፡14
እግዚአብሄር ከጋብቻ መቀጠል ጋር በትጋት የሚሰራው የእሱ የራሱ ተቋም ስለሆነ ነው፡፡
ትዳሩን መገንባት የሚፈልግ ሰውን እግዚአብሄር በመንፈሱ እና በሃይሉ የሚረዳው ትዳር የራሱ እቅድ ስለሆነ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከጋብቻ
መቀጠል ጋር አብሮ የሚቆመው እና መፋታትን የሚጠላው መፋታት የራሱን እግዚአብሄርን ተቋም ስለሚቃወም ነው፡፡ በትዳር ላይ ታላቁ
የእግዚአብሄር እጅ ያለበት ትዳር የእግዚአብሄር እቅድ እና አላማ ስለሆነ ነው፡፡
ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አደረጋቸው፤ ስለዚህ ሰው አባቱንና
እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም።
እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። የማርቆስ ወንጌል 10፡6-9
ትዳርን ባቀደው ፣ በመሰረተው እና በሚደግፈው
በእግዚአብሄር ስለትዳራችሁ አመኑ፡፡
ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። የዮሐንስ ወንጌል 14፡1
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት
#ጋብቻ #ትዳር
#መጋባት #ባል
#ሚስት #ፍቅር
#መውደድ #ይተዋል
#ይጣበቃል #አንድስጋ
#እውነት #ትህትና
#ትንሳኤ #ህይወት
#ወንጌል #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
Wednesday, February 12, 2020
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም
ነፋስን
የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። መጽሐፈ መክብብ 11፡4
ህይወት
የእምነት ጉዞ ነው፡፡ ህይወትን በሚገባ ማጣጣም ከፈለግክ በእምነት መኖር መጀመር አለብህ፡፡ በእምነት መራመድ ካልጀመርክ የህይወትን
እውነተኛውን ጣእም በፍፁም አታገኘውም፡፡ ሰው መኖር የሚጀምረው በእምነት መራመድ ሲጀምር ብቻ ነው፡፡ የሰው እውነተኛ መኖሪያ የእግዚአብሄር
ቃል እምነት ነው፡፡
እርሱም
መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4
ሰው
ዲዛይን የተደረገው ለእምነት ኑሮ ነው፡፡ ሰው የሚኖረው በእምነት ነው፡፡
እነሆ፥
ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ትንቢተ ዕንባቆም 2፡4
እምነት
የሚመጣው ከእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡
እንግዲያስ
እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17
በእግዚአብሄር
መልክና አምሳል ለተፈጠረው ክቡር ለሆነው ሰው ለሰው ልጅ ከእግዚአብሄ ቃል ያነሰ ኑሮ አይገባውም፡፡
እርሱም
መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4
የሰው
እውነተኛ እርካታ በእምነት ሲኖር ነው፡፡
ነገሮች ሆነው ከማየትህ በፊት የእግዚአብሄርን
ቃል አምነህ እርምጃ ካለወሰድክ ከእግዚአብሄር ጋር መኖር አትችልም፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር የምትገናኘው በስጋ አይን የማይታየውን
መንፈስ የሆነውን እግዚአብሄርን የምትሰማው ፣ እግዚአብሄርን የምትነካው ፣ እግዚአብሄርን የምታየው ሁሉ በእምነት ነው፡፡ የእግዚአብሄር
ነገር ሁሉ በእምነት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። መዝሙረ ዳዊት 33፥4
ነገሮች ተለውጠው ደስ ለመሰኘት የምትጠብቅ ከሆነ
ደስ መሰኘቱን እርሳው፡፡ ነገሩን የሚለውጠው በእምነት እርምጃ በመውሰድ ደስ በመሰኘትህ ብቻ ነው፡፡
የምትፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ኪስህ ከገቡ በኋላ
እፎይ ለማለት እየጠበቅክ ከሆነ የማይፈፀም ተስፋ እየጠበክ ነው፡፡
ለማመን ፀሎትህ እስኪመለስ እየጠበቅክ ከሆነ ፀሎትህ
ለመፈፀም የአንተን እምነት እየጠበቀ ነው፡፡
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት
እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። የማርቆስ ወንጌል 11፡23-24
ሁሉ ደህና ነው ለማለት ነገሮች ሁሉ ተስተካክለው
እስክታይ አየጠበቅክ ከሆነ በከንቱ ትጠብቃለህ፡፡
ከመዝራትህ በፊት ሁኔታዎችን እየጠበቅክ ከሆነ
መቼም አታጭድም፡፡
ምልክት ከማየትህ በፊት ማመን አለብህ፡፡ እምነትንም
የሚያመጣው የእግዚአብሄር ቃል እንጂ ምልክት እምነትን አያመጣም፡፡ ምልክቱን የሚያመጣው እምነትህ ነው፡፡
ከውጤት እና ከምልክት በፊት የእምነት እርምጃ
ይቀድማል፡፡
እንጀራህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን
በኋላ ታገኛዋለህና። መጽሐፈ መክብብ 11፡1
አስቀድመው ምልክትን የሚፈልጉ ካላየሁ አላምንም
የሚሉ ሰዎች እግዚአብሄርን የማይፈልጉ አሿፊ ሰዎች ናቸው፡፡
ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት። ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ። የማቴዎስ ወንጌል 16፡1፣4
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት
አያጭድም። መጽሐፈ መክብብ 11፡4
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #ስብከት
#ቃል #ዝራ
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Monday, February 10, 2020
Sunday, February 9, 2020
የዘላለም መነፅር
ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን እና ጌታችን
አምነን የተቀበልንና የዳንን ሁላችን ማንኛውምን ነገር በዘላለም መነፅር አይተን ካልመዘንን በስተቀር እግዚአብሄር ወደአየልን የህይወት
ግብ አንደርስም፡፡ በህይወታችን የሚቀርብልንን ምርጫዎች በዘላለም መነፅር አይተን ካልመዘንን እንሳሳታለን፡፡
ህይወት በምርጫ የተሞላ ነው፡፡ ትክክለኛ ምርጫን
ለመምረጥ የከበረውን ከተዋረደው መለየት ግዴታ ነው፡፡
የከበረውን ከተዋረደው ለመለየት ነገሮችን እውነተኛ
መልካቸውን የሚያሳይ መነፅር ማግኘት ወሳኝ ነው፡፡ በምድራዊ መነፅር ነገሮችን የምናይ እና የምንወስን ከሆንን እግዚአብሄር ካዘጋጀልን
የክብር ህይወት እንጎድላለን፡፡ እግዚአብሄር እንደሚያያቸው በሰማይ መነፅር በትክክል አይተን ከወሰንን ህይወታችን ያብባል፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። ትንቢተ ኤርምያስ 15፡19
የምንወስነው ውሳኔ በእግዚአብሄር ዘለዓለማዊ እቅድ
ውስጥ ያለውን ቦታ መረዳት ትክክለኛውን ውሳኔ እንድንወስን ያደርገናል፡፡
የምንወስነው ውሳኔ ለሚመጣው አለም የሚጠቅም እንደሆነ
አውቀን ካልወሰንን የምድር ልፋታችን ከንቱ ነው፡፡
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡8
በምድር
ላይ ስንኖር ከእግዚአብሄር እንደመጣን ወደእግዚአብሄር እንደምንሄድ አድርገን በዘላለም መነፅር ነገሮችን መመልከት አለብን እንጂ
እንብላ እንጠጣ ነገ እንሞታለን በማለት በምድራዊ መነፅር ብቻ ነገሮችን እንደሚያዩት ከንቱ ኑሮ መኖር የለብንም፡፡
በዘላለም
እይታ ነገሮችን ስናይ በምድር ላይ ለጌታ የምንቀበለው መከራ ዋጋ እንዳለው እንረዳለን፡፡
እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል?
ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። ፡1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡32
የምናደርገውን
ሁሉ እንደእግዚአብሄር ቃል በዘለላም መነፅር አይተን ካደረግን በከንቱ ለሚጠፋ መብል ከመስራት ይጠብቀናል፡፡
ለሚጠፋ
መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። የዮሐንስ
ወንጌል 6፡27
በዘላለማዊ
መነፅር የማያዩትን ሁሉንም ነገር በምድራዊ አስተሳሰብ የሚያስቡትን ሰዎች መፅሃፍ ቅዱስ መጨረሻቸው እንደማያምር ይናገራል፡፡
መጨረሻቸው
ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም
ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡19-20
በምድር
እንዳሉት የእግዚአብሄርን የዘላለም እቅድ እንደማይረዱት ሰዎች በምድራዊ እይታ ብቻ ኖረን ኖረን መሞት ለእግዚአብሄር ልጅ የሚገባ
አይደለም፡፡
እንግዲህ
ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን
አይደለም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡1-2
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እይታ #ተስፋ #መፀለይ #መንፈስ #በረከት #መዝገብ #ሰማይ #እንግዶች #ዘላለም #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እይታ #ምድራዊ #ሰማያዊት #ማየት #ቅርብ
Saturday, February 8, 2020
ኮሮና ቫይረስን እግዚአብሔር አልፈጠረውም
እግዚአብሄር ፍጥረቱን ሲፈጥር የፈጠረው ነገር
ሁሉ መልካም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ጤነኛ ጠንካራ ብርቱ አምራች እንዲሆን በሰላም ፣ በብርታትና እና በጤንነት ነው፡፡
እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡31
ኢየሱስን ወደ ምድር ሲመጣ የመጣው ለሰዎች ህይወት
እንዲሆናችው እንዲያውም እንዲበዛላቸው ነው፡፡
በተቃራኒው ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊታያርድና
ሊያጠፋ ነው ፡፡ ሰዎች ባለማወቅ በፈቀዱለት መጠን ሰይጣን የሰው ልጆችን ሰላም ደስታ ጤንነት ብርታት ሁሉ ይሰርቃል፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
እግዚአብሄር ሰዎች በምድር እንዲኖሩ እርሱን እንዲያውቁ
ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሄር በጣም መልካም ከመሆኑ የተነሳ በእምነታችው
የማይፈወሱትን ሰዎች ለዶክተሮች በሰጣቸው እውቀት አማካኝነት በህክምና እንዲፈወሱ ረጅም እድሜ እንዲኖሩ ይፈልጋል፡፡
ሰይጣን እንጂ እግዚአብሄር የሰው ልጆች ጠላት
አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የማንም ስቃይና መከራ አያስደስተውም፡፡
የእግዚአብሄርን ልብ የምናየው ኢየሱስ በምድር
ሲመላለስ እየዞረ በሃይል የታመሙትን ይፈውስ ነበር፡፡
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሐዋርያት
ሥራ 10፡38
እግዚአብሄር እርሱን ለማያውቁ ሰዎችም እንኳን
መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ለሰዎች ሁለተኛ እድል መስጠት ይፈልጋል፡፡ እርሱን እንዲያውቁትና እንዲድኑ እግዚአብሄር ሰዎችን
ይታገሳል፡፡
እኔ ግን እላችኋለሁ፥
በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡44-45
በቻይና ላይ ብሎም በመላው አለም ላይ የመጣውን
ይህን የኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክኒያት በማድረግ ለቻይና ህዝብ እንጸልይ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የቻይና ህዝብ እግዚአብሄርን እንዲያውቅ
ስለቻይና ህዝብ እንማልድ፡፡
በተሰጠን በልጅነት ስልጣን ሁልጊዜ የሰው ልጆች
ጠላት የሆነውን የሰይጣን ዲያቢሎስን አሰራር በኢየሱስ ክርሰቶስ ስም ፀንተን እንቃወም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሄር #ጌታ #ኢየሱስ
#ቃል #መዳን
#መንፈስቅዱስ #ሞቱናትንሳኤ
#መስቀል #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#ኮሮና #ኮሮናቫይረስ #ቻይና #መንግስተሰማያት #መፅሃፍቅዱስ
#ፍርድ #የዘላለምህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
Thursday, February 6, 2020
KEEP A-GOIN’
KEEP A-GOIN’
If you strike a thorn or rose,
Keep a-goin'!
If it hails or if it snows,
Keep a-goin'!
'Taint no use to sit an' whine
When the fish ain't on your line;
Bait your hook an' keep a-tryin'--
Keep a-goin'!
When the weather kills your crop,
Keep a-goin'!
Though 'tis work to reach the top,
Keep a-goin'!
S'pose you're out o ' ev'ry dime,
Tell the world you're feelin ' prime--
Keep a-goin'!
When it looks like all is up,
Keep a-goin'!
Drain the sweetness from the cup,
Keep a-goin'!
See the wild birds on the wing,
Hear the bells that sweetly ring,
When you feel like singin ', sing--
Keep a-goin'!
Submitted by: Lexel
Author: by Frank L. Stanton (1857-1927)
Wednesday, February 5, 2020
እግዚአብሔር አላከበደውም
እግዚአብሔር ሰውን የማይቻል ነገር ጠይቆ አያውቅም፡፡
እግዚአብሄር ከጠየቀ ይቻላል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ካዘዘ መፈፀኽ የሚቻል ትእዛዝ ነው ማለት ነው፡፡
እግዚአብሄር እርሱን መታዘዝንና ማስደሰትን ሰው
ብዙ ጊዜ እንደሚያስበው ከባድ አላደረገውም፡፡
የእግዚአብሄርን ነገር ከባድና ውስብስብ የሚያደርገው
የሰው የሃይማኖት መልክ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ሩቅና በፍፁም ሊረዱት የማይችሉት ረቂቅ የሚያደርገው የሰው ከንቱ የሃይማኖትኝነት
አስተሳሰብ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው፥ እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፤ እነርሱ ግን ብዙ ብልሃትን ፈለጉ። መጽሐፈ መክብብ 7፡29
እግዚአብሄር እርሱን መከተልን አላከበደውም፡፡ አንዳንድ ሰው በራሱ የሰው ጥበብ የእግዚአብሄርን ነገር ካላወሳሰበው በስተቀር እግዚአብሄርን ያመለከ አይመስለውም፡፡
እግዚአብሄር
የሰው ደስታ ጠላት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በትንሽ በትልቁ ማዘዝ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ሰው በነፃነት እንዲኖርና
የሚያደርገውን ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር ፍርሃት እንዲያደርገው ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው ብቸኛው ነገር እግዚአብሄር
አንድ ቀን ሰው የሚሰራውን ስራ ወደፍርድ እንደሚያመጣው በማወቅ ብቻ በነፃነት እንዲኖር ነው፡፡
የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። መጽሐፈ መክብብ 12፡13
ሰው
ሲታለል እግዚአብሄርን ለማስደስት ብዙ ነገር የሚያስፈልግ ይመስለዋል፡፡ እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው አንድ ነገር ቃሉን እንዲሰማና
እንዲከተል ብቻ ነው፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። የሉቃስ ወንጌል 10፡41-42
እግዚአብሄር
ሰው በምድር ላይ ብዙ ነገር እንዲፈልግ አልፈለገም፡፡ እግዚአብሄር ሰው እንዲፈልግ የፈለገው ብቸኛ በነገር የእግዚአብሄርን ፅድቁንና
መንግስቱን ብቻ ነው፡፡
ነገር
ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡33
እግዚአብሄር
በትላንት በዛሬና በነገ ውስጥ እንድንኖር እና ህይወታችንን እንድናወሳስብ አልጠየቀም፡፡ እግዚአብሄር በዛሬ ላይ ብቻ ኖረን እንድናስደስተው
ኑሮን ቀላል አድርጎታል፡፡
ነገ
ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡34
ሰው
እግዚአብሄር ብዙ ነገሮች የሚፈልግ ይመስለዋል፡፡ እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው የሰውም ትህትና ብቻ ነው፡፡
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ስፋት #እርካታ #ፍሬያማነት
#ክንውን #አሸናፊነት
#በጎነት #ቅን
#እምነት #ፅድቅ
#ደስታ #ሰላም
#ኢየሱስ #ጌታ
#ሃይል #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መጋቢ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
Subscribe to:
Posts (Atom)