ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ ከአካልም ብልቶችያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብርይጨመርላቸዋል፤ ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ብልቶች እርስበርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን፥ ለጎደለው ብልት የሚበልጥክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው። 1ኛ ቆሮንጦስ 12:22-25
I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ሃሎዊን Halloween የሚባለው በአል በኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ በተለያ የ መልኩ ይከበራል ፤ ባብዛኛው ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ባህል የሚ ከ ብረው ይህ የሃሎዊን በአል ሰዎች ቢገባ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ...
-
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁ...
-
Dhalachuun Yesus Raawwii Raajichaa Ture Kanaafis Waaqayyo ofii isaatii milikkita isiniif in kenna; kunoo, durbi in ulfoofti, ilmas in deess...
-
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 በመጽሃፍ ቅዱስ ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ኢየሱስ መወለድ ትንቢትን የተናገ...
-
https://youtu.be/VhF0pSsp14I በቃልኪዳን መነጽር ህይወታችን ማየት አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ሬማ እምነት አገልግሎት በርሚንግሃም ቤተክርስትያን
Thursday, September 28, 2023
Wednesday, September 27, 2023
Monday, September 25, 2023
The Bottom Line
Our lives should be lived with the intent of fulfilling God's purpose for us, rather than simply existing. That is the final conclusion.
What you do after eating is more important than what you consume, in my opinion.
In comparison to the reason you drive, the car you drive doesn't really matter.
Driving the most expensive car in the world is vanity if you don't truly pursue God's purpose for your life.
To complete God's purpose in our lives, the purpose of our lives is by far more significant than what we wear.
Even if you are the most attractive person alive and fall short of God's plan for your life, you have failed.
If you are the strongest human being but have failed to use your influence to fulfil God’s purpose in your life, your strength is nothing.
If you are the most intelligent person on the planet, but you do not use your knowledge for God's purposes in your life, then your life has failed.
Man is created for God's purpose and for his glory. Every provision and opportunity is meant for the purpose of fulfilling God’s purpose for our lives.
Abiy Wakuma Dinsa #purpose #success #prosperity #vanity #wisdom #might #riches #God #Jesus
Thursday, September 21, 2023
የንጉሱ አስደናቂ ታሪክ
ከአሥራ
ሁለት ወር በኋላ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ ይመላለስ ነበር። ንጉሡም፦ ይህች እኔ በጕልበቴ ብርታት ለግርማዬ ክብር የመንግሥት መኖሪያ እንድትሆን ያሠራኋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችምን? ብሎ ተናገረ። ቃሉም ገና በንጉሡ አፍ ሳለ ድምፅ ከሰማይ ወደቀና፦ ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ፦ መንግሥት ከአንተ ዘንድ አለፈች ተብሎ ለአንተ ተነግሮአል፤ ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፤ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው። በዚያም ሰዓት ነገሩ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ፤ ጠጕሩም እንደ ንስር፥ ጥፍሩም እንደ ወፎች እስኪረዝም ድረስ ከሰዎች ተለይቶ ተሰደደ፥ እንደ በሬም ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ። ዘመኑም ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዓይኔን ወደ ሰማይ አነሣሁ፥ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም ባረክሁ፥ ለዘላለምም የሚኖረውን አመሰገንሁ አከበርሁትም፤ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና፥ መንግሥቱም ለልጅ ልጅ ነውና። በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም። በዚያን ጊዜም አእምሮዬ ተመለሰልኝ፥ ለመንግሥቴም ክብር ግርማዬና ውበቴ ወደ እኔ ተመለሰ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቶቼም ፈለጉኝ፥ በመንግሥቴም ውስጥ ጸናሁ፥ ብዙም ክብር ተጨመረልኝ። አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፥ ታላቅም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ ነውና፥ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና። ትንቢተ ዳንኤል 4:29-37
Thursday, September 14, 2023
የእግዚአብሔር #ጸጋ ተገልጦአል
ሰዎችን
ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ወደ ቲቶ 2፡11-13
ሰዎች
ካሉበት ከማንኛውም ጥፋት የሚያድናቸው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጦዋል፡፡
የሰው
ማንኛውም ችግር እና ጥፋት ምንጩ ሃጢያት ነው፡፡ ሃጢያት ሰውን ከእግዚአብሔር ክብር አዋርዶ እንደሚጠፋ እንስሳት አስመስሎታል፡፡
ሰው
ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። መዝሙረ ዳዊት 49፡12
ሃጢያት
ሰውን ሁሉ ያዋርዳል ያሳንሳል ያጎሳቁላል፡፡ በአጠቃላይ ሃጢያት ሰውን ባሪያ ያደርጋል፡፡
ኢየሱስ
መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።የዮሐንስ ወንጌል 8፡34
ሰውን
ከሃጢያት እስራት ነፃ ማውጣት የሚችል ጉልበት ያለው የእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር
ፀጋ ጉልበት ሃጢያትን ያስክዳል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ሃያል የሆነውን አለማዊ ምኞትን ያስንቃል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ እግዚአብሔርን
የመምሰል ሃይልን ይሰጣል፡፡ ፀጋ በፅድቅ እንድንኖር አቅም ይሰጠናል፡፡
ሰዎችን
ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም
የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም
በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ወደ ቲቶ 2፡11-13
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #ሃይል #ወንጌል #ፅድቅ #ሃጢያት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #አቅም #ጉልበት
Sunday, September 10, 2023
እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 5
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ
ቢሆን አዲስ
ፍጥረት ነው፤
አሮጌው ነገር
አልፎአል፤ እነሆ፥
ሁሉም አዲስ
ሆኖአል። 2ኛ
ወደ ቆሮንቶስ
ሰዎች 5፡17
የሰውን ማንነቱን ፣ ተፈጥሮውን ፣ ባህሪውን
፣ ተስፋውን ፣ ግቡን የሚለውጠው እና የሚያድሰው አዲስ ፍጥረት መሆኑ ነው፡፡ ሰው አዲስ ፍጥረት ካልሆነ አዲስ ወር አዲስ አመት
በመጣ ቁጥር አዲስ ነገር መጠበቅ ተመሳይ ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት እንደመጠበቅ ከንቱ ነው፡፡
አዲስ ዘመን እንዲሆን አዲስ ሰው ይጠይቃል፡፡
አዲስ ዘመን ቢመጣም ሰውየው አዲስ ካልሆነ ዋጋ የለውም፡፡
ኢየሱስ አዲስ ነገር በአዲስ መያዣ ውስጥ መቀመጥ
እንዳለበት ከዚህ በታች ባሉት ጥቅሶች በማብራሪያ ያስተምራል፡፡ አዲስ አመት አዲስን ሰው ይጠይቃል፡፡ አዲስነት እንዲሰምር ሁለቱም
አዲስ መሆን አለባቸው፡፡ አንዱ ብቻ አዲስ ሆኖ ሌላው አሮጌ ከሆነ አይሰራም፡፡
በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። የማርቆስ ወንጌል 2፡21-22
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን
#አመት #ወንጌል
#አዲስአመት #ለውጥ
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
#እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ
Saturday, September 9, 2023
እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 4
አዲስ አመት በእውነት አዲስ አመት እንዲሆንልን
መለወጥ እና አዲስ ሰው መሆን ያለብን እኛ ነን፡፡ እኛ ክርስቶስን በማመን አዲስፍጥረት ካልሆንን በስተቀር የትኛውም አዲስ አመት
አሮጌ እንጂ አዲስ ሊሆንልን አይችልም፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡15
ሰው
በክርስቶስ ኢየሱስ አዲሱን ሰው ክርስቶስን እስካልለበሰ እና አሮጌውን ሰው እስካላስወገደ ድረስ አዲስ አመት በራሱ የሚያመጣለት
ምንም አዲስ ነገር አይኖርም፡፡
ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡22-24
ሰው
እውነተኛውን አዲስ አመትን የሚለማመደው ክርስቶስን የህይወቱ አዳኝና ጌታ ካደረገ ቀን ጀምሮ ነው፡፡
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን
#አመት #ወንጌል
#አዲስአመት #ለውጥ
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
#እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ
Friday, September 8, 2023
እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 3
ሁላችንም ከአዲስ አመት ውስጥ ብዙ ነገር እንመኛለን
እንጠብቃለን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰው ከአዲስ አመት የሚጠብቃቸው ነገሮች የሚገኙት በአዲስ አመት ውስጥ ሳይሆን በአዲስ ሰው ውስጥ
ነው፡፡
ሰው በአዲስ አመት ውስጥ የሚጠብቀው የብልፅግና
ዘመን የሚመጣው በንስሃ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ እንጂ ዘመን ሲለዋወጥ በምኞት ብቻ አይደለም፡፡
እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20
በህይወታችሁ
ከሚገጥመን ማንኛውም የመልካም ምኞት መግለጫ ሁሉ በላይ የመፅናናት ዘመን የሚያመጣልን ከሃጢያታችን ተመልሰን በክርስቶስ ኢየሱስ
ማመናችን ብሎም ክርስቶስን መከተላችን ነው፡፡
ክርስቶስ
ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለው እና ከሞት የተነሳው በእርሱ የሚያምኑት የመፅናናት ዘመን እንዲመጣላቸው እና እንዲባረኩ
ነው፡፡
ለእናንተ
አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው። የሐዋርያት ሥራ
3፡19-26
የሰላም እና የብልፅግና ዘመን የሚመጣው ሰው
በሃጢያት ምክኒያት ከተለያየው ከእግዚአብሔር ጋር በንስሃ ታርቆ ሰላም ሲሆን ብቻ እንጂ በአዲስ አመት ውስጥ አይደለም፡፡
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት
#ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ
Thursday, September 7, 2023
እውነተኛው አዲስ አመት ክፍል 2
እንደ መፅሃፍ ቅዱስ እውነተኛው አዲስ አመት
መቼ ነው ብለን መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡
እውነተኛው አዲስ አመት መቼ እንደሆነ በሚገባ
ካልተረዳን አዲስ አመት ባልሆነ ቀን ላይ በከንቱ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ አዲስ አመትን በትክክለ ካልተረዳነው አሮጌ በሆነ ነገር
ላይ አለአግባብ አተኩረን አዲሱን እናጣዋለን፡፡ አዲስ አመትን በትክክል ካልተረዳነው ጉልበታችንን በማይጠቅም ነገር ላይ እናባክናለን፡፡
ሰው አዲስ አመት የሚሆንለት የእግዚአብሔር ቃል
ሰምቶ በቃሉ ነፃ የወጣ እለት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለ የአዲስ አመት ተስፋ ከንቱ ተስፋ ነው፡፡
እስራኤላዊያን የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ይሁንላችሁ
የተባሉት የእግዚአብሔር ትእዛዝ ሰምተው ከግብፅ ነፃ የወጡበትን ቀን ነው፡፡
ሰው የሚታደሰው እና የሚለወጠው የእግዚአብሔርን
አላማ በህይወቱ ያደረገ እለት ነው፡፡ ሰው አዲስ አመት የሚሆንለት እግዚአብሔር የታዘዘ እለት ነው፡፡
እግዚአብሔርም
በግብፅ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ። በዚያም ቀን እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብፅ ምድር አወጣ። ኦሪት ዘጸአት 12፡1-2፣
50-51
ሰው እግዚአብሔር ያለውን የታዘዘበት ጳጉሜ
5 አዱስ አመት ነው ሰው ደግሞ እግዚአብሔርን ሰምቶ በቃሉ ነፃ ያለወጣበት መስከረም አንድ አዲስ አመት አይደለም፡፡
በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአዲስ
አመት ቀን ማድረግ እንችላለን፡፡ በምናደርገው ነገር መስከረም አንድን ጨምሮ እያንዳንዱን ቀን የአሮጌ አመት ቀን ልናደርገው እንችላለን፡፡
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት
#ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ
Wednesday, September 6, 2023
እውነተኛው አዲስ አመት
ሁልጊዜ አዲስ አመት ሲመጣ ደስ ይለናል፡፡ አዲስ
አመት ተስፋን ይዞ ይመጣል፡፡ ዘመን ሲለወጥ ያለፈውን እንድንረሳ ያደርገና ብለን ስለምናስብ ለአዲስ አመት እንጓጓለን፡፡ በአዲስ
አመት ያለፈውን ደስ የማያሰኘውን ነገር ሁሉ እንዳለፍነው ስለሚሰማን በተስፋ እንጠብቀዋለን፡፡
ይህን ሁሉ መጠበቅ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን
ይህን ሁሉ የምንጠብቀው በአዲስ አመት ብቻ ከሆነ ትክክል አይሆንም፡፡
እንደ እውነቱ ቀን እድልን የሚሰጥ እንጂ በራሱ
እድል አይደለም፡፡ ቀን በሚሰጠው እድል የሚጠቀም ሰው አለ ቀን የሚሰጠውን እድል የሚያባክን ሰው ደግሞ አለ፡፡ በቀን ውስጥ ምንም
አዲስ ነገር የለም፡፡ ቀን ያው ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ሮብ ፣ሃሙስ ፣ አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ነው፡፡
ቀኑን ልዩ የሚያደርገው በቀኑ ውስጥ የምናደርገው
ነገር እንጂ ቀኑ ራሱ አይደለም፡፡ ቀኑ ውስጥ የምናደርገው ነገር ከተለየ የምናገኘው ውጤት ይለያል፡፡ በቀን ውስጥ የምናደርገው
ነገር ግን ካልተለየ እና ተመሳሳይ ከሆነ የምናገኘው ውጤት ተመሳሳይ ይሆናል፡፡
ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡5
በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአዲስ
አመት ቀን ማድረግ እንችላለን፡፡ በምናደርገው ነገር እያንዳንዱን ቀን የአሮጌ አመት ቀን ልናደርገው እንችላለን፡፡
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን #አመት #ወንጌል #አዲስአመት
#ለውጥ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
Sunday, September 3, 2023
Saturday, September 2, 2023
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል ክፍል 4
እውነት ደዌያችንን ተቀበለ
ሕመማችንንም ተሸክሞአል
. . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥
ስለ በደላችንም
ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም
ተግሣጽ በእርሱ
ላይ ነበረ፥
በእርሱም ቍስል
እኛ ተፈወስን።
ትንቢተ ኢሳይያስ
53፡4-5
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በመልኩ እና በአምሳሉ
ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው መኖሪያ የሚሆን ስጋን አስቀድሞ አዘጋጀለት፡፡ ሰው ምንም እንኳን በእግዚአብሔር መልክ እና
አምሳል ቢፈጠርም በምድር ላይ ለመኖር እና የእግዚአብሔርን አላማ ለማስፈፀም ከምድር ጋር የሚስማማ መኖሪያ ቤት ስጋ አስፈልጎት
ነበር፡፡ በምድር ላይ ለመኖር ስጋ ግዴታ ነው፡፡
ኢየሱስ ከሃጢያታችን ሊቤዠን በመስቀል ላይ ሲሰቀል
ዋጋ የከፈለው ለነፍሳችን ብቻ አልነበረም፡፡ የነፍሳችን መዳን ወሳኝ ነገር ነበር፡፡ ካለነፍስ መዳን ማንኛውም የስጋ ፈውስ ትርጉም
የለውም፡፡ ነፍሳችን በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ ተቤዠቶ ስጋችን
ካልተፈወሰ ለመንግስተ ሰማያት ህይወት ብቁ እንሆናለን፡፡ የመንግስተ ሰማያት ህይወት መግባት የሚጠይቀው የነፍስ መዳንን ብቻ ነው፡፡
እውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል
. . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል
እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡4-5
ነገር ግን በምድር ላይ ቆይተን የእግዚአብሔርን
ስራ ለመስራት ግን የስጋችን ፈውስ ወሳኝ ነው፡፡ ካለስጋ ፈውስ በነፍስ መዳን ብቻ እግዚአብሔር እንዳየልን በምድር ላይ መቆየት
እና የእግዚአብሔርን የመንግስት ስራ መስራት አንችልም፡፡
ኢየሰስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለው
ስለፈውሳችን የተገረፈው ለዚህ ነው፡፡
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ
እንድንኖር፥ እርሱ
ራሱ በሥጋው
ኃጢአታችንን በእንጨት
ላይ ተሸከመ፤
በመገረፉ ቁስል
ተፈወሳችሁ። 1ኛ
የጴጥሮስ መልእክት
2፡24
የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን
ክፍል እንደሆነ
ሁሉ የስጋ
ፈውስ የመቤዠታችን
አንዱ አካል
ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም
#ደዌ #ወንጌል
#ፈውስ #ጤንነት
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
#በመገረፉ #ቁስል
#ተፈወሳችሁ
Friday, September 1, 2023
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል ክፍል 3
እውነት ደዌያችንን ተቀበለ
ሕመማችንንም ተሸክሞአል
. . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥
ስለ በደላችንም
ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም
ተግሣጽ በእርሱ
ላይ ነበረ፥
በእርሱም ቍስል
እኛ ተፈወስን።
ትንቢተ ኢሳይያስ
53፡4-5
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ጠንካራ እና ብርቱ
አድርጎ ነው፡፡ ሰው ሲፈጠር በሽታ እና ደዌ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ለሰው መልካምነት የሚሰራ ነበር፡፡ የተለያዩ
ድካሞች በሰው ላይ ስልጣን ያገኙት ሰው በእግዚአብሔር ላይ ካመፀ በሃላ ነበር፡፡
ሰው እግዚአብሔርን በሚታዘዝበት ጊዜ ሁሉ ምድር
እና በምድር ያሉ ነገሮች ሁሉ ይታዘዙለት እና ይገዙለት ነበር፡፡ ሰው በሃጢያት ከመውደቁ በፊት በሰው ላይ የሚያምፅ አንድም ነገር
አልነበረም፡፡
ሰው በእግዚአብሔር ላይ ሲያምፅ ነገሮች ሁሉ
በሰው ላይ አመፁ፡፡ ሰው እግዚአብሔርን መታዘዝ ሲያቆም ነገሮች ሁሉ መታዘዛቸውን አቆሙ፡፡ ሰው ነገሮች ሁሉ የተነሱበት በእግዚአብሔር
ላይ ከተነሳ በኋላ ብቻ ነው፡፡
ምድር
ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ ኦሪት
ዘፍጥረት 3፡17-18
ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ ኦሪት ዘፍጥረት 4፡12
አሁንም
እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ከሃጢያት ሲበዠን ከበሽታም ተቤዠቶናል፡፡ ክርስቶስ ለነፍሳችን ሃጢያት ዋጋ ከፍ ለስጋችን ፈውስ ዋጋ
ባይከፍል ኖሮ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን አላማ በጥንካሬ እና በብርታት መፈፀም አንችልም ነበር፡፡
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ
በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡24
የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን
ክፍል እንደሆነ
ሁሉ የስጋ
ፈውስ የመቤዠታችን
አንዱ አካል
ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም
#ደዌ #ወንጌል
#ፈውስ #ጤንነት
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
#በመገረፉ #ቁስል
#ተፈወሳችሁ