Popular Posts

Sunday, May 29, 2022

እግዚአብሔር እንዳለ

 

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 116

ወደ እግዚአብሄር ገብቶ ጉዳይን ለማስፈፀም የመጀመሪያው መመዘኛ እግዚአብሄር እንዳለ ማመን ነው፡፡

እግዚአብሄር እንዳለ ማለት ደግሞ አንድ ሃይል እንዳለ ማመን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ ማለት እግዚአብሄር የሚባል እንዳለ ብቻ ማለት አይደለም፡፡

እግዚአብሄር እንዳለ ማለት እግዚአብሄር የምድር እና የሰማይ ፈጣሪ ፣ ባለቤት እና አስተዳዳሪ እንደሆነ ማመን አለበት፡፡

እግዚአብሄር እንዳለ ማመን ማለት እግዚአብሄር ጀማሪ ወይም ቆርቋሪ እንደሆነ ማመን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር መሪ ነው፡፡ እግዚአብሄ የማንም ተከታይ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ለህይወታችን የራሱ ራእይ እና አላማ ያለው የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር በአላማው መሰረት በትጋት እየሰራ ምድርን እያስተዳደረ እንደሆነ ማመን ይጠይቃል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሰምር እግዚአብሄር በፍቅር በጥበብ እና በሃይል ምድርን እያስተዳደረ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡

ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። የዮሐንስ ወንጌል 1፡3

እግዚአብሄር ጀማሪ ነው፡፡ በምድር ላይ ይሁን በህይወታችሁ ውስጥ የተጀመረ ትርጉም ያለው ነገር ካለ የጀመረው እግዚአብሄር መሆኑን ማመን ይጠይቃል፡፡ አንዳንዱን ነገር እናንተ ብትተዉት እንኳን እግዚአብሄር ግን እንደ ባለቤት ከግቡ ሳያደርስ አይተወውም፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

እግዚአብሔር ምድርን ፈጥሮ አልተዋትም፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ ያሉትን ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች በትጋት ይከታተላል ይመዝናል ይቆጣጠራል ይመራል፡፡

ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8

እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል። ትንቢተ ኢሳይያስ 33፡22

አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡3

ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 5፡17

ይህን በመረዳት ወደ እግዚአብሄር የሚቀርብ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር በመልካም ግንኙነት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment