Popular Posts

Sunday, May 8, 2022

Let's all be Mothers

 Mothers are mostly known for their compassion, love, and forgiveness. Let’s be compassionate to others. Let’s accept others as they are. Let’s not judge others with an evil heart. Let’s not judge others from a place of strength. Let’s not judge others, look them down.


Let’s also be loving. Let’s think good, speak good, and do good to others. Let’s share goodness with others.

Let’s also forgive. Let’s understand others. People don’t wrong as if they really understand what they are doing. Even if we think they do, let’s leave it to God who knows our hearts. Our responsibility is to forgive. Don’t hold anything against them. Let them live. Release them and live your life.

Motherhood is a spirit we all practice in little or much. Let’s all be mothers.

በአብዛኛው እናቶች የሚታወቁት በርህራሄ፣ በፍቅር እና በይቅርታ ነው። እኛም ዛሬ ይህንን የእናትነት ፍቅር በመያዝ ለሌሎች ርህሩህ እንሁን። ሌሎችን እንዳሉ እንቀበላቸው። በሌሎች ላይ በክፉ ልብ አንፍረድ። በራሳችን ጥንካሬ ተመክተን በሌሎች ላይ አንፍረድ። ሌሎችን ዝቅ አድርገን በመመለከት ሌሎች ላይ አንፍረድ።

የፍቅር ሰዎች እንሁን። ለሌሎች መልካም እናስብ መልካም እንናገር መልካም እናድርግ። የተፈጠርነው ለሌሎች ነውና መልካምነትን ለሌሎች እናካፍል።

እንዲሁም ይቅር እንበል። ሌሎችን እንረዳቸው። ሰዎች የሚያደርጉትን በትክክል ከተረዱት ሌላውን ሰው አይበድሉም። አውቀው እንደበደሉን ብናያስብም እንኳን ልባችንን ለሚያውቅ አምላክ እንተወው። የእኛ ኃላፊነት ይቅር ማለት ብቻ ነው:: በበደሉን ላይ ምንም ነገር አንያዝ:: እንፍታቸው እንልቀቸው ይኑሩ። እንፍታቸው በህይወት ይኑሩ።

እናትነት ሁላችንም በጥቂቱም ሆነ በብዙ የምንለማመደው መንፈስ ነው። ሁላችንም እናቶች እንሁን::

No comments:

Post a Comment