Popular Posts

Saturday, February 20, 2021

በእምነት ያልሆነ

 


የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 1423

ሰው የተፈጠረው በእምነት እንዲኖር ነው፡፡ ሰው በእምነት ካልኖረ የተፈጠረበትን አላማ ይስታል፡፡ ሰው በጥርጥር ከኖረ በህይወቱ ትርጕም ያለው ነገር  ማድረግ ይሳነዋል፡፡

ሰው የእግዚአብሄርን ስራ ሰራ የሚባለው ሲያምን ነው እንጂ ሃይማኖራዊ ወግና ስርአት ስላደረገ አይደለም፡፡

እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 6፡28-29

የሚጠራጠር ሰው ከእግዚአብሄር የሚያገኘው በረከት ሙሉ አይሆንም ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄርን ስለተጠራጠረ ምንም ነገር አያገኝም፡፡

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። የያዕቆብ መልእክት 1፡6-8

ሰው ካመነ በኃላ የጥርጥርን ሃሳብ እንዳያስተናገድ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሰው ካመነ በኃላ በእምነቱ መፅናት አለበት፡፡ ሰው ማመኑ ብቻ ሳይሆን በእምነት መፅናቱና አለመጠራጠሩ ወሳኝ ነው፡፡ ሰው አምኖ በኃላ በእምነቱ ባይፀናና ቢጠራጠር ወደኃላም ቢያፈገፍግ በረከት ሊያገኝ አይችልም፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ የማቴዎስ ወንጌል 21፡21

የሰው ሃላፊነቱ የእግዚአብሄርን ቃል በቀጣይነት በመስማት እምነቱን መገንባት ብቻ ሳይሆን እምነቱን ሊንድ የሚችለውን የጥርጥርን ኃሳብ አለማስተናገድ ነው፡፡  

ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡20-21

ሰው እምነትን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን እምነቱን ለመጠበቅ የእምነት ተጋድሎን መጋደል አለበት፡፡

እምነት እግዚአብሄርን እንደሚያስደስተው ሁሉ እግዚአብሄር በጥርጥር አይደሰትም፡፡  

ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም። ወደ ዕብራውያን 10፡38

የሰው እምነት እግዚአብሄርን እንደሚያስደስተው ሁሉ የሰው ጥርጥር ያሳዝነዋል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ ዕብራውያን 11፡6

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #ጥርጥር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 


No comments:

Post a Comment