Popular Posts

Tuesday, February 16, 2021

ፍቅርን ፍለጋ

 



ሰው የተፈጠረው ፍቅር በሆነው አምላክ እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ፍቅርን እንዲቀበልና ፍቅርን እንዲሰጥ ነው፡፡

ፍቅር የሰው መሰረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ ሰው እርሱ እንዲወደድ ይፈልፈጋል፡፡ ሰው ሌላውን መውደድ ይፈልጋል፡፡

ሰው ፍቅርን ይፈልጋል፡፡ ሰው ፍቅርን ሲያግኝ ይረካል፡፡ ሰው ፍቅርን አስካላገኘ አይረካም ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ 

ሰው ፍቅርን መፈለጉ ትክክል ነው፡፡ ሰው ፍቅርን መፈለጉ በራሱ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ሰው ፍቅርን የሚፈልግበት ቦታ ፍቅርን የሚፈልግበትን መጠን እና ፍቅርን የሚፈልግበት ሁኔታን ማወቅ አለበት፡፡

ሰው በመጀመሪያ ፍቅርን ማወቅ ያለበት ከእግዚአብሄር ጋር ነው፡፡ ሰው መጀመሪያ ፍቅርን መቀበል ያለበት ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዴት እንደሚቀበል እና ለእግዚአብሄር ፍቅርን እንደሚመልስ ማወቅ አለብት፡፡

ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዴት እንደሚቀበል ካላወቀ ለእግዚአብሄር ለራሱና ለሌሎች ያለው የፍቅር ህይወቱ የተስተካከል ሊሆን አይችልም፡፡

የትኛውም እውነተኛ ፍቅር ምንጩ ፍቅር የሆነው እግዚአብሄር ነው፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 55

ፍቅርን በእግዚአብሄር ፍቅር ያልተረዳ ሰው ፍቅር ያልሆነውን ማስመሰያውን ፍቅር በማለት በፍቅር ትርጉሙ ይሳሳታል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ያላየ እና ያላወቀ ሰው የሰውን ፍቅር ቢያይም ሊያውቀው አይችልም፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ያልቀመሰ ሰው የፍቅርን ትርጉም ሊረዳ በፍፁም አይችልም፡፡

እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። 1 የዮሐንስ መልእክት 316

ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር አቀባበሉ እና ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የፍቅር ግንኙነቱ ለእግዚአብሄርና ለሰው ያለውን ፍቅር ይወስነዋል፡፡

ሰው በእውነተኛ እርካታ የሚረካው በእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ሰው በእውነተኛ እርካታ የሚረካው በእግዚአብሄር በተወደደበት መወደድ እግዚአብሄርን ራሱን  እና ሌላውን ሲወድድ ነው፡፡

ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የፍቅር ግንኙነቱ ቦታውን ሲይዝ ሌሎች የፍቅር ግንኙነቶቹ ሁሉ ትክክለኛ ቦታቸውን የይዛሉ፡፡

ሌላው እንዲወደን የምንፈቅደው የእግዚአብሄርን ፍቅር መቀበል በተለማመድነው መጠን ብቻ ነው፡፡ ሌላውን መውደድ የምችለው እግዚአብሄር እንዴት እንደወደደን በመረዳት ብቻ ነው፡፡ ሌላውን የምናምነው የእግዚአብሄር በፍቅር ባመንነው መጠን ብቻ ነው፡፡

ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1 የዮሐንስ መልእክት 47-8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #መውደድ #ማድረግ #መስጠት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ሳምራዊ #ሌዋዊ #ካህን #ባልጀራህን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #ወንጌል #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment