ሰው የተፈጠረው ሁሉንም እንዲያውቅ ሳይሆን በማያውቀው
ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር እንዲታመን ነው፡፡
ሰው ግን ብዙ ጊዜ በሚያውቀው ላይ ከመትጋት እና
በማያውቀው ነገር ሁሉ ላይ ሁሉን በሚያውቀው በእግዚአብሄር ከመታመን ይልቅ የሚያውቅውን ትቶ የማያውቀውን ለማወቅ ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው፥ እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፤ እነርሱ ግን ብዙ ብልሃትን ፈለጉ። መጽሐፈ መክብብ 7፡29
አዳምና ሔዋን በሚያውቁት ሁሉ ከመኖርና በማያውቁት
ሁሉ በየዋህነት በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ይልቅ የማያውቁትን ለማወቅ ለምን የሚል የማይመለስ አጓጉል ጥያቄ መጠየቅ በመጀመራቸው
ከህይወት መንገድ ወደቁ፡፡
ሰው የተፈጠረው በቀላሉ የሚያውቀውን እየተገበረ
የማያውቀውን ሁሉን በሚያውቀው በእግዚአብሄር ላይ እየተደገፈ እንዲኖር ነው፡፡
ኢዮብ ህይወቱ ላይ በደረሰው ነገር ለምን የሚል
ጥያቄ ይዞ ተነሳ፡፡ እግዚአብሄ ግን ያሆነው ነገር ለምን እንደሆነ ከመመለስ ይልቅ የእዮብን መረዳት ነው የፈተነው፡፡
እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦ ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው? እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር። መጽሐፈ ኢዮብ 38፡1-4
ብዙ ጊዜ ለምን የሚል ጥያቄ እግዚአብሄርን የምንጠይቀው
ቢመልስልንና ምክኒያቱን ቢነግረን የምንረዳ ስለሚመስለን ነው፡፡
እግዚአብሄር ለምን የሚለውን ጥያቄ የማይመልስልን
ፍጥረቱ ስለሆንን ሁሎዩንም እንደማንረዳ አበጥሮ ስለሚያቀን ነው፡፡ እግዚአብሄር ለምን የሚለውን ጥያቄ የማይመልስልን የእግዚአብሄርን
አሰራር ሁሉ መረዳት ከቻልን እኛ ራሳችን እግዚአብሄ ሆንን ማለት ነው፡፡
የሚያስፈልጉን የተገለጡ ነገሮች አሉ፡፡ እግዚአብሄር
የማይነግረን ነገሮች ደግሞ አሉ፡፡
ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ኦሪት ዘዳግም 29፡29
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት
#ቤተክርስትያን #መታመን
#መደገፍ #እምነት #ለምን #አማርኛ #ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ተስፋ
#አሁን #ጌታ
#ሰላም #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment