እውነተኛ የህይወት ለውጥ የሚጀምረው
የህይወት ለውጥ ቀላል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ሰው በፈለገ
ጊዜ ህይወቱን ይለወጥ ነበር፡፡ የህይወት ለውጥ ውሳኔን የሚጠይቅ ታስቦበት በእቅድ የሚራመዱት የጉዞ ውጤት ነው፡፡
ብዙ ሰዎች መለወጥ ይፈልጋሉ ነገር ግን መለወጥ
የሚያስችላቸውን ነገር አያደርጉም፡፡ ብዙን ጊዜ ሰዎች ለውጥን የሚፈልጉት ከተሳሳተ ቦታ ነው፡፡
ሰዎች እንዳይለወጡ ምክኒያት የሆኑዋቸውን ከእነርሱ
ውጭ ነገሮች ሁሉ ላይ ያተኩራሉ፡፡ ነገር ግን በህይወታቸው እንዳይለወጡ ላደረጋቸው ሃሳብ ፣ ምርጫና ልምምድ ሃላፊነት መውሰድ በፍፁም
አይፈልጉም፡፡
ሰው ስለደረሰበት ደረጃ ራሱ በትህትና ሃላፊነት
ካልወሰደ ስለህይወቱ ሃላፊነት ወስዶ ሊለውጠው የሚችለው ሰው ስለሌለ አይለወጥም፡፡ ሰው ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጡር በመሆኑ ከተለወጠ
የሚለወጠው በራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው ስለለውጡ አስተዋፆ ሊያደርግ ይችላል እንጂ ማንም ሰው ማንንም ሰው ሊለውጥ ግን አይችልም፡፡
የህይወት ለውጥ ከሌላ ሰው እና ከአካባቢ ሁኔታ
ይመጣል ብሎ መጠበቅ ተመሳሳይ ነገርን እያደረጉ የተለየ ለውጥን እንደመጠበቅ እብደት ነው፡፡
ሰው ያለበትን ደረጃ ሲቀበል ፣ ወደአለበት ደረጃ
ስላደረሰው ስለምርጫውና ስለአስተሳሰቡ ሃላፊነት መውሰድ ሲጀምር ለውጥ መምጣት ይጀምራል፡፡
ለውጥን ከፈለገን እንደዚህ የሆንኩት እከሌ እንደዚህ
ስላደረገኝ ነው በማለት ተጠያቂነትን ማስተላፍ ማቆም አለብን፡፡ ሰው ስለውድቀታችን አስተዋእኞ አድርጎ ይሆናል እንጂ ውድቀታችን
የመጣው ከህይወታችን ባለቤት ከራሳችን ነው፡፡ አዳም ስለውድቀቱ ሃላፊነት አለመውሰዱና ጥፋቱን በሌላ ሰው ላይ ማለከኩ ከቅጣት አላዳነውምን፡፡
አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን
የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ። ኦሪት ዘፍጥረት 3፡12
ሌላ ሰው ወይም ሁኔታ ስለውድቀታችን አስተዋፆ
እንዲያደርግ የምንፈቅድለት እኛ ብቻ ነን፡፡
ስላለሁበት ደረጃ መወቀስም መመስገንም ያለብኝ
እኔ ነኝ ብሎ ሃላፊነትም መውሰድ ብስለት ነው፡፡ ሰው ሃላፊነት ሲወስድ ከገባበት ነገር የሚወጣበትን መንገድ በሃላፊነት ስለሚያቅድና
ስለሚፈፅም ህይወቱ ይለወጣል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር
#እውቀት #ቃል
#ወር #መዳን
#ውሳኔ #መልካም
#መታዘዝ #የህይወትለውጥ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ሃላፊነት #መፅሃፍቅዱስ
#መጋቢ #እምነት
#ተስፋ #ፍቅር
#ጌታ #ሰላም
#ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#አዲስፍጥረት #መናገር
#አእምሮ #ነፍስ
#ቃል #ልጅ
No comments:
Post a Comment