Popular Posts

Thursday, March 19, 2020

ዘመኑን ዋጁ


እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 515-16
በዘመናችን የሚሆን ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስገርመው ነገር የለም፡፡ ከመሆኑ በፊት ምን እንደሚሆን መቼ አንደሚሆን ለምን እንደሚሆን ሁሉ ያውቀዋል፡፡
አስገራሚ የሚሆነው ሁሉንም ለማናውቅ ለእኛ ነው፡፡
ይህ ነገር እንደመጣ ይሄዳል፡፡ ይህ ነገር ተራራ እንደሆነብን ይህ ነገር አለፈ እንዴ እንላለን፡፡ የማያልፍ የሚመስለው በቅርቡ እንደተረት ይወራል፡፡
የእኛ ሃላፊነት ከእንደዚህ አይነት ጊዜ ውስጥ የተሻለ ነገር ማውጣት ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት ዘመኑን ለእግዚአብሄር መንግስት መጠቀም ነው፡፡
ክፉ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ግን ክፉውን ለውጦ ለመልካምነታችን ይጠቀምበታል፡፡
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ወደ ሮሜ ሰዎች 828
ዘመኑን የምንገዛውና ለራሳችን ጥቅም የምንጠቀምበት ዘጠኝ መንገዶች
1.         እግዚአብሄርን ማመስገን
እግዚአብሄር እንከን የማይወጣለት መልካም ነው፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር ምስጋና ሊመሰገን ይገባል፡፡ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን የሚያዩ ሰዎች ሁልጊዜ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ ያመሰግኑታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1 ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 516-18
የሰው አመስጋኝነት የሚለካው በእንደዚህ አይነት ጊዜ ነው፡፡ ሰው ያለው ሃይል የሚለካው በፈተና ጊዜ ነው፡፡
በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 2410
2.         አለመፍራት
ፍርሃት ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡ በፍርሃት የምናደርጋቸው ማንኛውም ድርጊቶች ይጎዱናል እንጂ አይጠቅሙንም፡፡ በፍርሃት የምናደርጋቸው ነገሮች ስለእግዚአብሄር ልጅነታችን አይመሰክርም፡፡ በፍርሃት የምናደርጋቸው ነገሮች በተለምዶው ማድረግ የምንቻለችውን ነገሮች እንኳን እንዳናደርግ ሽባ ያደርገናል፡፡
ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች ብሎ መለሰለት። የሉቃስ ወንጌል 850
3.         አለመጨነቅ
ከጭንቀት የሚጠቀመው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ሰው ለመጨነቅ ሲፈተን ያንን ሃይል ፀሎት ላይ ማፍሰስ አለበት፡፡ ለመጨነቅ ሲፈተን ለጭንቀት የሚያባክነውን ጊዜ በፀሎት ላይ ማዋል ፍሬያማ ያደርገዋል፡፡ ለመጨነቅ ሲፈተን የጭንቀቱን ጉልበት በፀሎት ላይ ማፍሰስ ፍሬያማ ኢንቨስትመንት ነው፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 46
4.         ሌሎችን ማበረታታት
ሰዎች ተጨንቀዋል፡፡ እኛ ደግሞ ላለመጨነቅ 100% ምክኒያት አለን፡፡ እግዚአብሄር እረኛችን ነው፡፡ እግዚአብሄር ጠባቂያችን ነው፡፡ እግዚአብሄር መመኪያችን ነው፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ቃል ተበረታተን ሰዎችን ማበረታታት ሰዎች እግዚአብሄርን በእኛ እንዲያዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰዎችን ማበረታታት የእኛ መንፈስ የተለየ መንፈስ እንዳለን ያሳያቸዋል፡፡ ሰዎችን ማበተታታት ብርታት ከመስጠቱ በተጨማሪ የሌላቸውን ያንን በመንፈስ ቅዱስ የሆነ የሃይል መንፈስ እንዲፈልጉት እንዲጓጉ ያደርጋል፡፡
በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 214-16
5.         ለሌሎች መልካምን ማድረግ
ይህ ጊዜ ደግሞ ያልፋል፡፡ ሰዎች መልካም ስራችንን የሚያዩበት ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ ከመንገዳችን ወጥተን ለሰዎች መልካም ማድረግ እውነተኛ ሰዎች መሆናችንን ለማሳየት እና የቀመስነውን የእግዚአብሄር መንግስት መልካምነት እንዲቀምሱ ያበረታታቸዋል፡፡
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የማቴዎስ ወንጌል 516
6.         ለራሳችን ጊዜ መውሰድ
አንዳንድ ጊዜ ሳናስበው በጣም ባተሌ ከመሆናቸን የተነሳ እግዚአብሄር ራሱ ከእኛ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ይናፍቀናል፡፡ ታዲያ ህይወት ዝም በሚልበት ጊዜ ለመፀለይ የእግዚአብሄርን ፊት ለመፈለግ መጠቀም ዘመኑን ለመግዛት ያስችለናል፡፡ ይህንን አይነት ጊዜ በቀላሉ አናገኘውም፡፡ እግዚአብሄር በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሊያድሰን ሊለውጠን ይፈልጋል፡፡ በዚህ ጊዜ ተጠቅመን የእግዚአብሄር ቃል በሙላት እንዲኖርብን ቃሉን ማንበብና ማሰላለስ የማይገኝ እድል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚመስበው ሁኔታው ሳይሆን የሚለወጠው እኛ ነን፡፡ እምነታችን ይፈተናል ይጠራል፡፡ አመለካከታችን ይፈተናል ይለወጣል፡፡ ዋጋ አሰጣችን ይፈተናል ይለወጣል፡፡ 
ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። የሉቃስ ወንጌል 1041-42
7.         ዱለት ነው ከሚሉ ጋር ዱለት አለማለት
ሰዎች በፍርሃት ጠፋን ተቆረጥን ተፈለጥን ሲሉ እኛ መፍራት ያለብን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እኛ የምንፈራው በቂ እና ብቸኛ ፍርሃት አለን፡፡ እኛ ኮሮናን አናመልክም እግዚአብንሄርን ብቻ እናመልካለን፡፡ እኛ ኮሮናን አንፈራም እግዚአብሄርን በፍፁም ልባችን እንፈራለን፡፡ እኛ ኮሮናን አንቀድስም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄርን እንቀድሳለን፡፡ በልባችን ልዩ ስፍራ ያለው ኮሮና ሳይሆን ክርስቶስ ነው፡፡ ኮሮናንና ክርስቶስን እኩል አንፈራም፡፡ የክርስቶስን የዙፋን ቦታ ለኮሮና አንሰጠም፡፡ 
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1 የጴጥሮስ መልእክት 314
8.         ለሰዎች መፀለይ፡
ተስፋ ያለን ሰዎች ነን፡፡ ከምድር ያለፈ ተስፋ አለን፡፡ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች አናዝንም አንጨነቅም፡፡ በዚህ አጋጣሚ በህይወታችን ስላለ ተስፋ ለሌሎች በየዋህነትና በፍርሃት እንመሰክራለን፡፡
በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1 የጴጥሮስ መልእክት 315
ሰዎች እንደዚህ ጊዜ ለፀሎት ክፍት የሚሆኑበት ጊዜ ላይኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ የተጨነቁ ሰዎች ስናገኝ ለእነርሱ መፀለይ ልባቸውን ወደክርስቶስ መምራት እንዲሁም ጌታን ክርስቶስን የህይወታችንው ጌታ እንዲያደደርጉት መምራት ይጠይቃል፡፡ 
9.         ለፈውስ መፀለይ
አንደኛው የሚያምኑትን ከሚከተላቸው ምልክቶች አንዱ በበሽታ ላይ ያላቸው ሃይል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የታመመ ሰው ስናገኝ ለዚያ ሰው መፀለይ ይጠብቅብናል፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ በሃይል በእኛ የሚሰራውን የእግዚአብሄርን ክብር የምንለማመድበት መልካሚ አጋጣሚ ነው፡፡
ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። የማርቆስ ወንጌል 1617-18
እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር። የማርቆስ ወንጌል 1620
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ AbiY Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment